Select your region
and interface language
We’ll show relevant
Telegram channels and features
Region
avatar

Amhara Media Corporation

AmharaMassMedia
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
Subscribers
49 600
24 hours
30 days
-400
Post views
2 069
ER
3,29%
Posts (30d)
292
Characters in post
696
Insights from AI analysis of channel posts
Channel category
News
Audience gender
Male
Audience age
35-44
Audience financial status
Middle
Audience professions
Government & Public Sector
Summary
May 06, 17:41

https://youtu.be/GKlNisz6bBY?si=yqoIT2k5ff91i_Fm

May 06, 14:38
Media unavailable
4
Show in Telegram

ባሕር ዳር ከተማ ፋሲል ከነማን አሸነፈ።
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 30ኛ ሳምንት ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማን ከፋሲል ከነማ ያገናኘው ጨዋታ በባሕር ዳር ከተማ አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ባሕር ዳር ከተማ ፋሲል ከነማን 2ለ0 ነው ያሸነፈው። የባሕር ዳር ከተማን የማሸነፊያ ግብ አማኑኤል ገብረ ሚካኤል እና ብሩክ ሰሙ አስቆጥረዋል።
በሌላ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ሲዳማ ቡናን 1ለ0 አሸንፏል።
#AmharaMediaCorporation
#AMECO
#አሚኮ
#ዜና
#ኢትዮጵያ
#ሠላም
#አሚኮአዲስአበባ
#amecosport
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

May 06, 14:17
Media unavailable
3
Show in Telegram

በባሕር ዳር ከተማ ውስጥ የሚያለሙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ችግሮች ለመፍታት እየተሠራ ነው።
ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ያለበትን ሁኔታ ጎብኝተዋል። ምልከታ ካደረጉባቸው ፋብሪካዎች ውስጥ በናይክ ትሬዲንግ ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ስር የሚገኘው አሚን የምግብ ዘይት ፋብሪካ ይገኝበታል።
የናይክ ትሬዲንግ ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አሥኪያጅ አታላይ ወንዴ እንዳሉት ፋብሪካው በቀን እስከ 30 ሺህ ሊትር ዘይት የማምረት አቅም አለው።1 ሺህ ኩንታል ፋጉሎም ያመርታል። ለ127 ዜጎች የሥራ ዕድልም እንደሚፈጥርም ገልጸዋል። ድርጅቱ ምርቶቹን ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬን ለማዳን ይሠራል ነው ያሉት።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ፋብሪካው ወደ ምርት መሸጋገሩ በገበያ ላይ ያለውን የዘይት እጥረት ለመቅረፍ እና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ጠቁመዋል። ከአካባቢው አርሶ አደሮች የቅባት እህሎችን በመረከብ ……
https://www.ameco.et/89508/
ዘጋቢ፦ ስማቸው አጥናፍ
#አሚኮ
#ኢትዮጵያ
#investAmhara
#የዘይት_ፋብሪካ
#ባሕርዳር
#ኢትዮጵያ
ታምርት
#ኤክስፖ_2018
#Ethiopia
#AmharaMediaCorporation
#AMECO
#አሚኮ
#ዜና
#ኢትዮጵያ
#ሠላም
#አሚኮአዲስአበባ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

May 06, 13:56
Media unavailable
3
Show in Telegram

የሀገር ውስጥ ምርት መበራከት አቅርቦት እና ፍላጎት እንዲመጣጠን ያደርጋል።
አዲስ አበባ፡ ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች እና የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን ጎብኝተዋል።
በተለያዩ ዘርፎች አምራች ኢንዱስትሪዎች ይዘዋቸው የቀረቡትን ምርቶች የጎበኙት የሃይማኖት አባቶቹ በኤክስፖው የተመለከቱት ነገር እንደሀገር ኩራት እንዲሰማቸው ያደረገ መኾኑንም ገልጸዋል።
በሀገር ውስጥ ተኪ ምርትን በማምረት እና የውጭ ምንዛሬን በማስቀረት ትልቅ ፍይዳ ያላቸው ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶች ወደገበያው መቀላቀል እንደ ሀገር የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ዕድገት አመላካች መኾኑንም ተናግረዋል።
የሀገር ውስጥ ምርቶች መበራከት አቅርቦት እና ፍላጎቱ እንዲመጣጠን በማድረግ በአነስተኛ ዋጋ ምርትን ለሸማቹ ማኅበረሰብ ማድረስ የሚያስችል መኾኑንም ገልጸዋል።
ግለሰቦች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልኾኑ ተቋማት ለሀገር ውስጥ ምርት ትልቅ ቦታ በመስጠት መግዛት እንዳለባቸው እና አልፎ አልፎ የሚታዩ የግንዛቤ …
በኢትዮጵያ ታምርት 2018 ኤክስፖ ከ20 በላይ አምራቾች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፦ቤተልሄም ሰለሞን
#ኢትዮጵያ
ታምርት#ኤክስፖ_2018
#Ethiopia
#AmharaMediaCorporation
#AMECO
#አሚኮ
#ዜና
#ኢትዮጵያ
#ሠላም
#አሚኮአዲስአበባ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

May 06, 13:20
Media unavailable
5
Show in Telegram

እንሳሮ - ተፈጥሮ የቸራት የታሪክ አድባር
ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘው የእንሳሮ ወረዳ የተፈጥሮ ጥበብ እና የታሪክ ክብር መገኛ ነው። ከመንዝ እና ከጅሑር አቅጣጫ ቁልቁል የሚወርደው የጀማ ወንዝ ምድሩን እያረሰረሰ ልዩ ለምለምነትን ያጎናጽፈዋል።
የመልክዓ ምድሩ አቀማመጥ ከኮከብ መስክ እስከ ጀማ ወንዝ ድረስ እጅግ ማራኪ እና ለዕይታ የሚስብ ነው። አካባቢው የተራራማ እና የረባዳ ስፍራዎች ድብልቅ በመኾኑ ለተመልካች እርካታን ይለግሳል።
ምንም እንኳን አብዛኛው መሬት ወጣ ገባ እና ቆላማ ቢኾንም ውበቱ ግን የሰውን ህሊና የሚያድስ እና የሚመስጥ ነው። ተፈጥሮን ለማድነቅ እና ራስን ለማደስ እንሳሮን መጎብኘት ተመራጭ የሚያደርጓቸው የመስህብ የስበት ስፍራዎች በዚሁ አካባቢ ሞልተዋል።
እንሳሮ በበርካታ ተፈጥሯዊ፣ ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ የመስህብ ሀብቶች የታደለች ድንቅ ምድር መኾኗን የወረዳው ባሕል ቱሪዝም እና ስፖርት ጽሕፈት ቤት የሥነ ጽሑፍ ባለሙያ ግዛቸው ቢያዝን ተናግረዋል። የሮቢ ወንዝ የሚፈጥረው ፏፏቴ ደግሞ የጎብኝዎችን ቀልብ በመሳብ የሚታወቅ ነው። ወንዙ በጉዞው ላይ ሁለት አስደናቂ ፏፏቴዎችን እንደሚፈጥርም ነግረውናል።
ወፊ ፏፏቴ፦ ከ200 ሜትር በላይ ከፍታ ላይ ቁልቁል ይወረወራል። ስያሜውንም ያገኘው ከርዝመቱ የተነሳ ወፍ እንኳን የማይደርስበት ተብሎ …
https://web.facebook.com/share/p/1Gsw9C9r9b/
#AmharaMediaCorporation
#Discover
Amhara AMECO
#AMECO
#አሚኮ
#ዜና
#ኢትዮጵያ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

May 06, 13:14
Media unavailable
1
Show in Telegram

"የፋይዳ መታወቂያ ፕሮጀክት ስኬትማ እንዲኾን የመሪዎችን ቁርጠኝነት እና ድጋፍ ይጠይቃል" አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)
ደሴ፡ ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፋይዳ መታወቂያ ፕሮጀክት ተግባር በስኬት እንዲጠናቀቅ የመሪዎች ቁርጠኝነት እና ድጋፍ ወሳኝ መኾኑን የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ገልጸዋል።
የፋይዳ መታወቂያ ሕገ ወጥነትን እና ወንጀሎችን ለመከላከል ያለው ጠቀሜታ የጎላ ነው ብለዋል። በተለይም ግለሰቦች ማንነታቸውን ደብቀው ወንጀል የመሥራት ዕድላቸውን የሚያስቀር መኾኑን ጠቁመዋል። ፕሮጀክቱ በሀገር ደረጃ እንደ ቁልፍ ተግባር የሚወሰድ እና በሁሉም ተቋማት የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲሰፍን የሚረዳ በመኾኑ ፋይዳውን በሚገባ በመረዳት በአጭር ጊዜ ውስጥ መተግበር እንደሚገባ አሳስበዋል።
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ አርዓያሥላሴ በኢትዮጵያ የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ከ43 ሚሊዮን በላይ መሻገሩን አስታውቀዋል። አሁን ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ያለው በገጠሩ አካባቢ በግብርና ሥራ በተሰማሩ ዜጎች ላይ መኾኑንም አመላክተዋል።
የተለያዩ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የፋይዳ መታወቂያን እንደ ቅድመ-ሁኔታ የመጠየቅ በአዋጅ የተደነገገ መብት እንዳላቸው የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ እንደ ጤና፣ ግብርና፣ ቴሌኮም፣ ንግድ እና ገቢዎች ያሉ ዘርፎች አገልግሎታቸውን ከመታወቂያው ጋር እያያያዙት መኾኑን ገልጸዋል።
የብሔራዊ መታወቂያ …
https://www.ameco.et/89497/
#AmharaMediaCorporation
#AMECO
#አሚኮ
#ዜና
#ኢትዮጵያ
#ሠላም
#አሚኮአዲስአበባ
#ፋይዳ
#ብሔራዊ_መታወቂያ
#Ethiopia
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

May 06, 12:51
Media unavailable
2
Show in Telegram

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር ተወያዩ።
ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር ውጤታማ የሥልክ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

በውይይቱ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል።
በተለያዩ ዘርፎች ያለንን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ሃሳብ ተለዋውጠዋል ነው ያሉት።
#AmharaMediaCorporation
#AMECO
#አሚኮ
#ዜና
#ኢትዮጵያ
#አሚኮአዲስአበባ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

May 06, 10:26
Media unavailable
1
Show in Telegram

"ፍርድ ቤቶች በቀበሌ ቤቶች ይዞታ ላይ የመዳኘት ሥልጣን የላቸውም" የፌዴሬሽን ምክር ቤት
አዲስ አበባ፡ ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት "የፍርድ ቤቶች ሚና፣ ተግዳሮት እና መፍትሔው" በሚል መሪ መልዕክት ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ ከከፍተኛ መሪዎች እና ከሕግ እና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፤ ምክር ቤቱ ሀገራዊ አደጋዎችን የሚታደጉ እና የግለሰቦችን እንዲሁም የቡድኖችን መብት የሚያስከብሩ በርካታ የሕገ-መንግሥት ትርጓሜዎችን ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሰዋል። ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፍርድ ቤቶች ከመንግሥት የረጅም ጊዜ ይዞታዎች እና ቤቶች ጋር በተያያዘ የምክር ቤቱን ውሳኔ ያላከበሩ ብያኔዎችን እየሰጡ መኾኑን ጠቁመዋል።
አፈ-ጉባኤው እንደገለጹት፣ ፍርድ ቤቶች በየደረጃው የሚቀርቡላቸውን "የቀበሌ ቤቶች" ተብለው የሚጠሩ የረጅም ጊዜ የመንግሥት ይዞታዎች ክርክር እና አቤቱታ የመዳኘት ሥልጣን የላቸውም። አፈ ጉባኤው ዋና ዋና ምክንያቶችን ሲያብራሩ እንዳሉት ምክር ቤቱ ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር 113/16 በሰጠው ውሳኔ፤ ለረጅም ጊዜ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያሉ ቤቶች "ከአዋጅ ውጭ ተይዘዋል" የሚል ክርክር ሥልጣን ባለው አካል እስካልተረጋገጠ ድረስ፣ ቤቱ የመንግሥት እንደኾነ ተደርጎ እንደሚወሰድ አስገዳጅ ትርጓሜ ሰጥቷል።
በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሠረት የመንግሥት የተደረጉ የትርፍ ቤቶች ክርክርን....
https://www.ameco.et/89481/
ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን
#የፍትሕ_ሥርዓት
#Ethiopia
🇪🇹
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

May 06, 10:22
Media unavailable
3
Show in Telegram

ዶናልድ ትራምፕ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ መርከቦችን አጅቦ የማውጣቱ ዘመቻ ለጊዜው እንዲቆም አዘዙ።
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ዶናልድ ትራምፕ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ መርከቦችን አጅቦ የማውጣቱ ዘመቻ ለጊዜው እንዲቆም አዝዘዋል።
የአሜሪካ የጦር መርከቦች እና የንግድ መርከቦችን በወሽመጡ ውስጥ ታጅበው እንዲያልፉ የሚያደርገው ሥራ በድንገት እንዲቋረጥ ተደርጓል። ዓላማው ደግሞ ከኢራን ጋር ለሚደረገው የሰላም ስምምነት ዕድል ለመስጠት እንደኾነ ቴሌግራፍ ዘግቧል።
ትራምፕ በወሽመጡ ላይ የተጣለው ከበባ እንደቀጠለ ኾኖ የሰላም ስምምነቱን ለማርቀቅ እና ለማጽደቅ እንዲቻል የጥበቃ ዘመቻው ለጥቂት ጊዜ እንዲቆም መወሰናቸው ተመላክቷል።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ውሳኔ ያሳለፉት በሰላም ድርድሩ ላይ ትልቅ መሻሻል ታይቷል በሚል ቢኾንም ውሳኔው የመጣው ኢራን በአሜሪካ የጦር መርከቦች ላይ ሚሳይል ተኩሳ በነበረበት እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ላይም የድሮን ጥቃት በሰነዘረችበት ወቅት ነው ብሏል ዘገባው።
በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ ከበባ የኢራንን የነዳጅ ሽያጭ በእጅጉ ጎድቷል። የዓለም የነዳጅ ዋጋም....
https://www.ameco.et/89478/
#AmharaMediaCorporation
#AMECO
#አሚኮ
#ዜና
#ኢትዮጵያ
#ሠላም
#አሚኮአዲስአበባ
ዘጋቢ፦ ስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

May 06, 08:14
Media unavailable
5
Show in Telegram

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱልልታ ወረዳ የስንዴ ልማትን ጎበኙ።
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱልልታ ወረዳ የስንዴ ልማትን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የጀመርነው ጥረት በላቀ ውጤት ቀጥሏል ብለዋል።
‎ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱልልታ ወረዳ በ2 ሺህ 150 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የስንዴ ማሳን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !