Select your region
and interface language
We’ll show relevant
Telegram channels and features
Region
avatar

قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )

abu_hibetillah_asselfiy
ይህ ቻናል ቁርኣንና ሀድስን፣ [በሰለፎች አረዳድ] እንዲሁም የሰለፎች ንግግርና ምክሮችን እና የታማኝ የሱና ዑለማዎች አስተምሮቶች ፈታዋወች ሙሐደራዎች የሚለቀቅበት የሰለፉነ አስሷሊህ ዕምነት የሚብራራበት ቻናል ነው። ይ ቀ ላ ቀ ሉ https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy አስተያየትና እርማት ካላችሁ 👇 @Abu_Hibetillah_bot
Subscribers
17 461
24 hours
-1
30 days
961
Post views
1 253
ER
7,18%
Posts (30d)
142
Characters in post
810
Insights from AI analysis of channel posts
Channel category
Religion and Spirituality
Audience gender
Female
Audience age
25-34
Audience financial status
Middle
Audience professions
Education
Summary
June 21, 09:49

🌹
እውነተኛዋ ብልህ ሴት ማለት!
ብልህ ሴት ማለት እንዲሁ በውጫዊ ውበትዋ የምትደልል ወይም በጌጣጌጥ ብልጭልጭ የምትታለል ሳይሆን፤ ስብዕናዋ በሐያእ (በጥንቁቅነት) ያጌጠ፣ ልቧ በኢማን የጸናና ሕይወቷን በአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ውዴታ ላይ የመሰረተች የጽናት ተራራ ናት።
🌹
እውነተኛ ብልህነት የሚጀምረው አላህን ከመፍራት (ተቅዋ) ነው። እርሷ በሰው ዓይን ውስጥ ለመግባት አትውተረተርም፤ ይልቁንም በሰማይ መላእክት ዘንድ ስሟ እንዲታወቅ ትተጋለች። የሷ ትልቁ ሀብቷ ቁሳቁስ ሳይሆን፣ ለዲን ያላት ቀናኢነትና ለቤተሰቧ የምታበረክተው ሰላምና ስክነት ነው።
🌹
የአላህ መልክተኛ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ እንዲህ ብለዋል፦ "ዱንያ በሙሉ መጠቀሚያ (ጸጋ) ናት፤ ከዱንያ ጸጋዎች ሁሉ በላጩ ደግሞ ሷሊሕ (መልካም) ሴት ናት።" (ሙስሊም ዘግበውታል)። ብልህ ሴት ይህንን ትልቅ ማዕረግ የተረዳች ናት። እርሷ ከሌሎች ጋር አትፎካከርም፤ የሷ ተፎካካሪ የገዛ ነፍሷ ብቻ ነች።
🌹
ዛሬ ካለችበት ማንነት ነገ ይበልጥ ወደ አላህ የምትቃረብበትን መንገድ ትቀይሳለች። በንግግሯ ውስጥ ቁም ነገር፣ በዝምታዋ ውስጥ ደግሞ ተመስጦ
(ተደቡር) አለ። በሰው ሐሜትና ወሬ አትባክንም፤ ይልቁንም ምላሷን በአላህ ዚክርና በመልካም ንግግር ታርሳለች።
🌹
እርሷ ለባሏ የሰላም ወደብ፣ ለልጆቿ የጥበብ ትምህርት ቤት፣ ለወላጆቿ ደግሞ የጀነት በር ናት። ጭንቀት ሲመጣ አላህን በመለመን ታሸንፈዋለች፤ ጸጋ ሲፈስላት ደግሞ በማመስገን ትጠብቀዋለች።
🌹
እንዲህ ያለች ሴት ልክ እንደ ተደበቀ ዕንቁ ናት፤ ለማግኘት የምትከብድ፣ ካገኙዋት በኋላ ግን ሕይወትን የምታበራና ትርጉም የምትሰጥ ውድ ስጦታ ነች። አላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى እህቶቻችንን ሁሉ እንዲህ ያለውን የብልህነትና የሷሊሕነት ማዕረግ ይልግሳቸው። ቤታችንን በነሱ ኑር (ብርሃን) ይሙላልን።
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

June 21, 04:33

⚠️
ለምን እናዝናለን?
ለመሆኑ... ለምን እንከፋለን? ብለን ቆም ብለን አስበን እናውቃለን? እኛ የምንከፋውና የልብ ሰላም የምናጣው የሕይወትን አቅጣጫ መቆጣጠር ስላልቻልን ብቻ ሳይሆን፤ አላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى በቀደሩ (በውሳኔው)
የለወጣቸውንና የማይቀየሩትን ነገሮች በገዛ ፍላጎታችን ለመቀየር ስለምንታገል ነው።
⚠️
ትልቁ የሐዘናችን ምንጭ ደካማ በሆኑት ሰዎች ላይ ከመጠን በላይ ተስፋ ስለምናደርግና ነገሮች ሁሉ እኛ በወሰንነው መስመር ላይ ብቻ እንዲሄዱ ስለምንፈልግ
ነው። ነገር ግን እውነተኛው የልብ ሰላም የሚገኘው ነገሮችን ሁሉ ለባለቤቱ ለአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى አሳልፎ በመስጠት (ተወኩል) ውስጥ ብቻ መሆኑን እንዘነጋለን።
⚠️
ፍፁም የሆነ ሰላም በዚህች አላፊ ምድር ላይ እንደሌለ ስንዘነጋ፣ ሐዘናችንና ጭንቀታችን በከንቱ ይጨምራል። አላህسُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ይህችን ዓለም (ዱንያ) የፈጠራት ለደስታ መፍለቂያ ሳይሆን ለፈተና ማለፊያ አድርጎ ነው። ነቢዩ መሐመድ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ እንዳስተማሩን፤ የአማኝ ሁኔታ ሁልጊዜም
ያስደንቃል፤ በደስታ ጊዜ ያመሰግናል ፣ በመከራ ጊዜ ደግሞ ይታገሳል (ሶብር ያደርጋል)፤ ይህ ደግሞ ለእርሱ መልካም
ይሆንለታል።
⚠️
ስለዚህ የከበደን ነገር ሲገጥመን "ለምን?" ብለን ከማማረር ይልቅ፣ የልቦችን ስብራት ጠጋኝ ወደሆነው ጌታችን መሸሽ ይኖርብናል። ዛሬ ያለንበት ሐዘን ነገ ለሚመጣው ትልቅ በረካችን መታጠቢያ ሊሆን ይችላል።
⚠️
ያሳዝናል! ችግራችንን የሚያስረሳንና ተስፋ የሚያስቆርጠን ትልቁ ፈተና የልባችንን ጥንካሬና በእምነታችን ላይ ያለንን ጽናት መጠበቅ አለመቻላችን ነው። ሕይወት በፈለግነው መንገድ ስላልሄደች ብቻ ጉዟችን አብቅቷል ማለት አይደለም። ይልቁንም አላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى የዘጋብን በር ከበሩ ጀርባ ያለውን አደጋ ስለሚያውቅልንና የተሻለውን በር ሊከፍትልን ስለፈለገ መሆኑን በሙሉ ልብ ማመን ይኖርብናል።
🌹
ሰላም የሚገኘው ባለን ነገር በመርካትና በፈጣሪያችን ውሳኔ ደስተኛ በመሆን ውስጥ ነው። ልባችንን ከአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ጋር ካቆራኘን፣ በሰው ንግግር አንናወጥም፣ በማጣትም አንደሰትም። እውነተኛውና ዘላቂው ሰላም የሚጠብቀን ሐዘንና ድካም በሌለባት ጀነት ውስጥ መሆኑን አውቀን፣ ዛሬን በትዕግስትና በኢማን እናሳልፋት።
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

June 20, 15:07

🌹
እውነተኛ ፍቅር መገለጫው
🥀
ሰዎች ስለ ፍቅር ብዙ ይላሉ፤ በሺህ የሚቆጠሩ ትርጓሜዎችንም ይሰጡታል። አንዳንዱ ፍቅር ማለት ስሜት ነው ይላል፣ ሌላው ደግሞ አብሮ መኖርና ባለቤት መሆን ነው ብሎ ያምናል።
🌹
ለእኔ ግን ፍቅር ከቃላትና ከቅርበት በላይ የሆነ እጅግ የረቀቀ የልብ መስዋዕትነት ነው። እውነተኛ ፍቅር ማለት በራስህ ዓለም ውስጥ ሳይሆን፣ ለምትወደው ሰው ደስታና ሰላም ውስጥ መኖርመቻል ነው።
🌹
የእሱ መሳቅ ያንተ ፈገግታ፣ የእሱ ስኬት ያንተ እርካታ፣ የእሱ ሰላም ደግሞ ያንተ ፍፁም ስክነት በሚሆንበት ጊዜ ፍቅር ትክክለኛ ትርጉሙን ያገኛል።
🌹
ከምንም በላይ ግን ፍቅር የልብ ጀግንነት የሚጠይቀው እዚህ ጋር ነው፤ አንዳንዴ የምትወደውን ሰው አቅፈህ መያዝ ብቻ ሳይሆን፣ ለራሱ ሰላም ሲባል እጅህን መልቀቅ ትልቁ የፍቅር መገለጫ ይሆናል። ካንተ መራቅ ለሚወዱት ሰው ሰላምን የሚሰጠው ከሆነ፣ ያንተ መኖር ለልቡ ሸክም ሆኖ ካገኘኸው፣ ያኔ ራስህን ወደ ኋላ አርቀህ በሩቁ ሆኖ ደስታውን መመኘትና ለሰላሙ ዱዓ ማድረግ ከማንኛውም ቅርበት
በላይ የሆነ የላቀ ፍቅር ነው።
🌹
እውነተኛ አፍቃሪ ማለት የሚወደውን ሰው ደስታ ከገዛ ራሱ ፍላጎት በላይ የሚያስቀድም ንጹህ ልብ ያለው ብርቱ ሰው ነው።
🌹
ይህ ነው የንጹህ ልቦች ፍቅር፤ አብሮ ለመሆን ሳይሆን በሐቅ ለመዋደድ የሚደረግ የነፍስ ጉዞ። በፍቅር ውስጥ ትልቁ ድል የምትወደውን ሰው በፈለገውና ሰላም በሚያገኝበት መንገድ ላይ ደስተኛ ሆኖ ማየት ብቻ ነው። ያኔ ርቀትም ቢሆን
ትርጉም ያጣል፤ ምክንያቱም ፍቅር በአካል ሳይሆን በልብ ውስጥ የሚኖር ዘላቂ ብርሃን ነውና።
🌹
አላህ እውነተኛን ፍቅር ይወፍቀን
🥀
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

June 20, 12:41

🌹
"አላህ ይጠብቃቸውና አሉ አንዳንዴ ሰዎች፤ ምነው ከዚህ በፊት አውቄያቸው በነበር የምንላቸው! አጋጥሟችሁ አያውቅም?
🌹
"
አንዳንድ ሰዎች የፈጣሪ ስጦታዎች ናቸው!
በሕይወት ጉዟችን ላይ ብዙ ሰዎችን እናገኛለን፤ አንዳንዶቹ ደስተኛ አድርገውን ያልፋሉ፣ አንዳንዶቹ የማይረሳ ትምህርት ጥለውልን ይሄዳሉ። ነገር ግን ጥቂት በጣም ጥቂት ሰዎች አሉ— ልክ እንደ ንጹህ አየር፣ እንደ ረጋ ውኃና እንደ ማራኪ አበባ የሆኑ።
እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው? እነዚህ ሰዎች ገና ሲያወሩህ ልብህን ሰላም የሚሞሉ፣ በጭንቀትህ ጊዜ መፍትሔ ባይኖራቸው እንኳ አብረውህ በመሆን ሸክምህን የሚያቀልሉ፣ ስብዕናቸው በጨዋነትና በኢማን ያጌጠ ውድ ሰዎች ናቸው። እነሱን ስታገኝ በልብህ እንዲህ ትላለህ፦ "
ምነው ቀደም ብዬ ባገኘኋቸው ኖሮ?
እስከዛሬ የት ነበሩ?"
እነዚህ ሰዎች የአላህ ጸጋዎች ናቸው ፦ እነዚህ ሰዎች እንዲሁ በአጋጣሚ የመጡ ሳይሆኑ አላህ በሕይወትህ ላይ የላከቸው ትልቅ "ሪዝቅ" (ሲሳይ) ናቸው። በክፋትና በምቀኝነት በታወከች ዓለም ውስጥ እንደነዚህ ያሉ ቅን ልቦችን ማግኘት የታላቅ ዕድል ምልክት ነው። እነሱ ለክፋት
ክፋትን አይመልሱም፣ በሰው ስኬት አይቀኑም፣ ለሰው ልጅ ያላቸው ፍቅር ደግሞ ንጹህና ከአላህ የተቸራቸው ነው።
ወዳጄ ..! እንዲህ ያሉ ሰዎች በሕይወትህ ውስጥ ካሉ አጥብቀህ ያዛቸው። እነሱ ለዱንያህም ለአኺራህም ትልቅ ስንቅ
ናቸው። አንተም ለሰዎች እንደዚህ አይነት "ምነው ቀድመን ባወቅነው" የሚባሉ ውድ ሰው ለመሆን ጣር።
አላህ እንደነዚህ ያሉትን ቅን ሰዎች ያብዛልን፤ ያሉትንም በያሉበት ይጠብቅልን!
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

June 20, 12:32
Media unavailable
1
Show in Telegram

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
🎈
ልዩ የደዕዋ እና የኒካህ ፕሮግራም ጥሪ፦
🎊
እነሆ የፊታችን እሁድ ከምሽቱ 2:30 ጀምሮ
የወንድማችን አቡ ዑሰይሚ
ን ሙሀመድ እና የእህታችን
ኡሙ አብዲላህ ጦይባ ቢንት ሰዒድ
የኒካህ ፕሮግራም አስመልክቶ ደማቅ የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል !
🎐
ተጋባዥ እንግዶች
፦
1. ሸይኽ አወል አሕመድ
2.
ኡስታዝ ኸድር አሕመድ
3
.አቡ ዑበይዳህ
4.
አቡ ሒበቲላህ
5.አቡ ሐፍሷ
6.
አቡ ሀሳን
7.
አቡ ረያን
8. አቡ ማሒር
«
የፕሮግራም መሪ አቡ ረያን እና አቡ ማሒ
»
🔖
ፕሮግራሙ የሚተላለፍበት ቻናል፦
https://t.me/MohamedAliEdris
https://t.me/MohamedAliEdris

June 20, 06:02
Media unavailable
3
Show in Telegram

በሁሉም የኢስላም አገራት የምትገኙ የሱና ሰዎች ሆይ! የሙፍሊሲን (ኪሳራ ላይ የወደቁት) ኢኽዋኖችን ሙሓደራ (ትምህርት) እንዳትታደሙ፣ እናም በማንኛውም ነገር በኢኽዋነል ሙፍሊሲን ላይ እምነት እንዳትጥሉ እመክራለሁ።
'በተስማማንበት ነገር ላይ እንተባበር፣ በተለየንበት ነገር ላይ ደግሞ አንዳችን ሌላውን ይቅር እንበል (እንቻቻል)' እንዳትል!
ተጠንቀቅ፣ ተጠንቀቅ!
በተስማማንበት ነገር ላይ የምንተባበረው በሱና ሰዎች ላይ ለመምታት (የሱና ሰዎችን ለማጥቃት) ነው? እነሱ [የሱና ሰዎችን] ለመምታት ተስማምተዋል።
በተለየንበት ነገር ላይ ደግሞ አንዳችን ሌላውን ይቅር እንባባላለን፤ ስለዚህ ሱፊዩ፣ ሺዓው፣ ሌላስ... ምናልባትም በዕሢዩ (የበዕሥ ፓርቲ አባል)፣ ምናልባትም ዓለማዊው (ሴኩላሪስቱ)፣ ምናልባትም ሌላስ... ኢሽቲራኪዩ (ሶሻሊስቱ) አንዳችን የሌላውን ጥፋት ዑዝር እየሰጠን እንለፍ እንባባላለን?
من نصائح الشيخ العلامة مقبل بن هادي الوادعي رحمه الله
https://t.me/durusuabihizam

June 20, 05:06

በቅርቡ በወሎ ኮምቦልቻ በተካሄደው ደውራ ላይ እጅግ በርካታ መሻይኾች እና የተለያዩ የሸሪዐ እውቀትን በመማር ላይ የተሰማሩ ደረሶች ተሰባስበው ነበር። ለኔ ከተሰጠው ትምህርት በላይ ስብስቡ በጣም ደስ ብሎኛል። የነሱም ደስታ ከፊታቸው የሚነበብ ነበር። ቁርጠኝነቱ ከቀጠለ በአሁኑ ሰዓት በየአካባቢው የምናየውን ከፍተኛ የአስተማሪ እጥረት በሆነ መጠን የሚቀርፍ ግዙፍ የዒልም ሰራዊት እየመጣ እንደሆነ ይሰማኛል፣ ኢንሻአላህ። አላህ ከክፉ ጠብቆ ለሃገር፣ ለወገን የሚጠቅሙ ያድርጋቸው። እንዲህ አይነት ፕሮግራሞች በየተወሰነ ጊዜ ቢደጋገሙ ጥሩ መነቃቃት ይፈጥራሉ። ጠንካራ ትስስር እንዲኖርም ያግዛሉ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor

June 19, 22:08
Media unavailable
4
Show in Telegram

✔️
በኡስታዝ አቡ ሻኪራ
🎙
🎙
ርዕስ:- ስለ"ትዳር
🎧

June 19, 20:29

///ግጥም ለሙሽሮች///
ሙሺሪት ሙሺራዉ እኮን ደስ አላችሁ
አላህ እድሜ ሰቶ ለዚህ አበቃችሁ ፡
በደስታ ኑሩ ይስመር ትዳራችሁ ፡
ትዳር ደስ የሚል ነው የነብዩ ሱና
የመልካሞች መንገድ የሶሀቦች ፋና
((የኔዋ ሙሽራ))
እኮን አደረሰሽ የኔዋ ሙሽራ ዉስጤን
ደስ ይለዋል ስለ አንች ሲወራ ከጎንሽ
ባልሆንም ዛሬ በሰርግሽ ቀን ሁልጊዜ
አስባለሁ ስለ አንች ቀን በቀን
አብሽሪ ሙሺሪት ዛሬ ነው አለምሽ
ትዳርሽም ይስመር ኑሪልኝ ሳይከፋሽ
((ምክር ለሙሺሪት))
ሀቁን ጠብቂለት አደራ ሙሽሪት
ስበብሽ ነው እና መግቢያሽ ወደጀነት
በጥሩ እስካዘዘሽ መረሀባ እሽ በይዉ
ክብር ይገባዋል የሀላል ባልሽ ነው ፡
ወደ ቤት ሲመጣ ተዉበሽ ጠብቂዉ
ሌላ ሴት እዳያይ ባልሽን ሰትሪዉ ፡
///ምክር ለሙሽራዉ ///
ሙሺራዉ አደራ እህቴን አክብራት, ፡
አምነን ሰተንሀል የቤታችን ንግሥት "
ዉድናት ልጃችን የቤቱ አይነታ ሁሌም '
ከጎኗ ሁን እዳትገላታ ሙሺራዉ አደራ,
ሀቋን ጠብቅላት የነብዩ አደራ ትልቅ
ወስያ ናት በተሠብ ሲሰጥህ ሀላፍትና
አለብህ በአካል ልጠብቃት ልትወዳት
በልብህ የልጆህ እናት አይንህ ማረፊያ ናት
መጥፎ አትናገራት በል ተከባከባት
በተሰቦን ትታ ወደ አንተ መታለች
የህይወቷ አጋር እድትሆን መርጣለች
የቤታችን ንግሥት ለአንተ ነው የተሰጠው
ሀቋን ጠብቅላት አደራ ሙሺራዉ ፡
​በአላህ ስም ጀምሬ በከሪሙ ጌታ
በራህመቱ አዝንቦ ሰጠን ትልቅ ደስታ
ሰኢድ እና ራህማ አጣምሮ በደስታ
እንኳን ደስ አላችሁ በዛሬዋ ማታ።
​ሰኢድ ወንድማችን የሱናው አርበኛ
በሰለፎች መንገድ ነቅቶ የማይተኛ
አላህ አድሎሀል የቤት ውስጥ ጀግና
ራህማን መርጦልሃል በሱናው ጎዳና።
​ራህማ እህታችን የሀያእ ተምሳሌት
በሂጃብሽ ንግስት አንች የቤት እመቤት
ከወንድም ሰኢድ ጋር ዛሬ ስትጣመሪ
የጀነትን ሪዝቅ በጋራ ጀምሪ።
​ተውሂድ ይሁንላችሁ የቤቱ መሰረት
በሱናው ያሸብርቅ የቤታችሁ ማብራት
የሰለፎች ምክር ይሁንላችሁ መሪ
በፍቅር ተሳስራችሁ ለዘላለም ኑሩ።
​ውለዱና ክበዱ ተውሂድን አንጋቢ
ሱናን የሚወዱ ቢድዓን ሰላቢ
አላህ ያቆያችሁ በኸይር ስራ ላይ
ለአኼራ ስንቅ ጀነተል ፊረደውስ ላይ ።
​ባረከላሁ ለኩም ወባረከ አለይኩም
ወጀመዐ በይነኩማ ፊል ኸይር
እህታችሁ ኡሙ ሓቲም መኪያ

June 19, 20:19

💐
💐
💐
💐
💐
💐
💐
💐
بارك الله لكما وبارك عليکما وجمع بينکما في الخير
🌹
🌹
🌹
🌹
🌹
🌹
🌹
🌹
🌹
🌹
🌹
ዉዴ ደስ ብሎኛል ለዚህ ቀን መብቃትሽ
🌷
🌷
🌷
🌷
🌷
🌷
🌷
🌷
🌷
🌷
🌷
የሱናዋ ቆንጆ የተዉሂድ አርበኛ፣
እንኳንም ደስ አለሽ አንች ምርጧ የኛ፣
ጋብቻ ሱና ነው የሙእሚን ጎዳና ፣
የፍቅር ቃል ኪዳን ማህደረ ሰኪና፣
ትዳርሽን ያርገው ያማረ ያበበ ፣
በነብዩ ሱና ደምቆ የተዋበ፣
አልሀምዱሊላሂ ለዚህ ላደረሰሽ፣
የነዚያን እንቁዎች የሰለፎች መንገድ መርጦ ለወፈቀሽ፣
ጋብቻ ጥሩ ነው ብዙ ጥቅም አለው ፣
አዉቆ ለገባበት አሏህ ለወፈቀዉ ፣
ከሀራም መሸሻ አይንን መስበሪያ ነው ።
የባልሽንም ሀቅ ጠባቂ ያድርግሽ አላህ እንዳዘዘሽ፣
ተምሳሌትም ሁኚ ለሱና እህቶችሽ ፣
መካሪ ዘካሪ ከሀራም እንድንሸሽ፣
የትዳርን ጣዕም ለዛን ለማግኘት ፣
እኒያ እንቁ ሰለፎች ይሁኑሽ ተምሳሌት ፣
ልክ እንደታዘዝነዉ  ቀጥ በሉ በሱና ፣
መዳን የሚገኘው በተዉሂድ ነዉና ፣
ትዳራችሁ ይስመር በሰለፎች ፍና ፣
ዘላቂ ያድርገው እስከ ዳሩል ጀና ፣
ረበና ይስጣችሁ ሷሊህ ሷሊህ ልጆች ፣
የተዉሂድ አርበኛ የሽርክ  ጠላቶች ፣
ጠቃሚ የሆኑ ለኡመተል ኢስላም ፣
አጥብቀው የያዙ የአሏህን ከላም፣
➡️
እናም እህቴዋ
⬅️
በሂጃብሽ አምረሽ በሱና ድመቂ፣
በሀያዕ ታጅበሽ ከሙንከር ራቂ፣
አንዴ አድምጭኝ ዉዴ ምክር ቢጤ ልስጥሽ ፣
ዉድሽን አደራ ጠብቂዉ ከልብሽ ፣
ትዕዛዙን አክብሪ የሚልሽን ስሚዉ ፣
ረሱል እንዳሉት አንድም የጀሀነብ
አንድም ወደ ጀነት መግቢያ ሰበብሽ ነው ፣
አብሽር ሀቢቢዬ ሁሌም ከጎንህ ነኝ አለሁልህ በይዉ ፣
ትዳራችሁ ሰምሮ አብቦ ያፍራላችሁ ፣
ደግሞ የዛሬ አመት (ቢቢን) ወልዳችሁ  ለመሳም ያብቃችሁ ፣
የአላህ ቀደር ሆኖ ባልገኝ ከጎንሽ ባልሆን ካጠገብሽ ፣
በጣም ደስ ብሎኛል ለዚህ ቀን  መብቃትሽ ።
በድጋሜ መብሩክ ብያለሁ
ደስታሽ ደስታዬ ነው ዉዷ እህቴ
ከሱና እህትሽ ኡሙ ኡሠይሚን
➺➨➺➨➺➨➺➨➺➨➺