Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
🔥
ተመሳሳይ ያረጁ ዜናዎችን ማንበብ ይብቃዎ! አልጎሪዝምዎን ይቀይሩ።
🇪🇹
🌍
ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም አቀፍ ዙሪያ የተሰሙ አዳዲስ ክስተቶችን በተለየ ምልከታ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ይከታተሉ። እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን በየእለቱ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ብቻ ያገኛሉ።
✅
ከሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማያገኟቸውን ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ለእርስኦ ያቀርብልዎታል።
📌
አዳዲስ መረጃዎችን በየእለቱ ለመከታተል አሁኑኑ ቻናላችንን በመቀላቀል ያልተሰሙ መረጃዎችን ይከታተሉ::
👇🏾
👇🏾
👇🏾
https://t.me/+G7KxcdEwTKBjYzg6
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በጂቡቲ የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ዛሬ ከሰአት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
#PMOEthiopia
#Djibouti
#ethiodjibouti
#diplomacy
#gazetteplus
🔥
ተመሳሳይ ያረጁ ዜናዎችን ማንበብ ይብቃዎ! አልጎሪዝምዎን ይቀይሩ።
🇪🇹
🌍
ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከአለም አቀፍ ዙሪያ የተሰሙ
አዳዲስ ክስተቶችን በተለየ ምልከታ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ይከታተሉ።
እንዲሁም ያልተጋሩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን በየእለቱ በስፑትኒክ ኢትዮጵያ ብቻ ያገኛሉ።
✅
ከሌሎች መገናኛ ብዙኃን የማያገኟቸውን ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ስፑትኒክ ኢትዮጵያ ለእርስኦ ያቀርብልዎታል።
📌
አዳዲስ መረጃዎችን በየእለቱ ለመከታተል አሁኑኑ
ቻናላችንን በመቀላቀል ያልተሰሙ መረጃዎችን ይከታተሉ::
👇🏾
👇🏾
👇🏾
https://t.me/+eM_pls45dPAyZjZi
ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር ውጤታማ የሥልክ ውይይት አድርገናል። በውይይታችን የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ የመከርን ሲሆን፣ በተለያዩ ዘርፎች ያለንን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ሃሳብ ተለዋውጠናል።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ከ80 ሺህ በላይ ወጣቶች በ“ሪሞት ጆብስ” ወይም ፍሪላንሲንግ ሥራ ተሰማርተዋል
+++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ
| በኢትዮጵያ ከ80 ሺህ በላይ ወጣቶች በ“ሪሞት ጆብስ” ወይም ፍሪላንሲንግ ሥራ ተሰማርተው ተጠቃሚ መሆናቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ አንድ ባለሙያ ባለበት ቦታ ሆኖ ስማርት ስልክ ወይም ላፕቶፕ በመጠቀም በተለያዩ የዓለም ሀገራት ተቀጥሮ መሥራት የሚያስችለው ሥርዓት ነው።
በዘርፉ ከ80 ሽህ በላይ ወጣቶች ቴክኖሎጅን በመጠቀም እዚሁ ሁነው ሌላ ዓለም ላይ የሥራ ዕድል እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡ ገቢያቸውም እያደገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በዘርፉ በሥራ ፈጠራና ክህሎት ልማት የሰው ኃይል ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ዜጎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የዲጂታል ግንዛቤን ማሳደግና የክህሎት ክፍተቶችን መሙላት ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል።
የሪሞት ጆብስ (ፍሪላንስ) ስራ የዲጂታል ክህሎትና እውቀት ያለው ሰው የሚፈልግ በመሆኑ ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል ለመፍጠር ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረጉ የሥራ ፈጠራ ሐሳቦች እንዲስፋፉ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በእየሩስ ተስፋዬ
#የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት
#ጋዜጣፕላስ
#ዲጂታል_ኢትዮጵያ
#ሪሞት_ጆብስ
#ፍሪላንሲንግ
#የሥራ_ፈጠራ
#ቴክኖሎጂ
*
#ኢትዮጵያ
"አርበኝነት ለሀገር ያለ ዋጋ የሚከፈል ከራስ ወዳድነት የነጻ መሥዋዕትነት፤ ሀገርንና ሕዝብን ብቻ ማዕከል ያደረገ፤ ለግል ወይም ለቡድን በተለየ የሚገኝ ነገር የለውም። ለሀገር ከሚገኘው ነጻነት፣ ሉዓላዊነትና ክብር ከሚደርስ የዜጋ ድርሻ በቀር"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#VictoryOverFascism
#ሚያዝያ27
#የአርበኞችቀን
#VictoryDay
#Ethiopia
#PatriotsDayEthiopia
ጥበብ ሀገር ትሠራለች፤ ሀገርም ጠቢብን ታከብራለች - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ
-በዛሬው ዕለት ለሃገር ባለውለታ ለሆኑና በጥበብ ሞያቸው ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅዖ የመታሰቢያና የክብር ሃውልት በአዲስ አበባ በተለያዩ አከባቢዎች ቆሞላቸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ሀገር ለጠቢባን የሕያው ሥራዎቻቸው ምስክር ሐውልት ታቆማለች። ጥበብ ሀገር ትሠራለች፤ ሀገርም ጠቢብን ታከብራለች ብለዋል።
ዛሬ በአርበኞች ቀን በተለያዩ መስኮች የጀግንነት ሚና የተወጡ አርበኞቻችንን በማስታወስ እየዘከርናቸው ነው ያሉት ከንቲባዋ የሀገር ባለውለታ ለሆኑና በጥበብ ሞያቸው ለኢትዮጵያ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የመታሰቢያ ሐውልት ቆሞላቸዋልም ብለዋል።
ሀገር በልማት ስራዎች፣ ድንበርን በመከላከል፣ በሰንደቅ ዓላማና በሕግ ብቻ አትገነባም። ሀገር የምትገነባው በሕዝብ የጋራ ትውስታ፣ በጋራ ስሜትና በታላላቅ የጥበብ ውጤቶችም ጭምር ነው። ይህ እውነት ዛሬ በቆሙት የሀገር ባለውለታ ታላላቅ ጠቢባን ሐውልቶች በአዲስ አበባ እውን አድርገናል ሲሉም ገልጸዋል።
ከተማ አስተዳደራችን በኮሪደር ልማትና በታላላቅ ፕሮጀክቶች ውስጥ፣ ጥበብን ማዕከል አድርጓል ብለዋል።
ዛሬ ሃውልት የቆመላቸው ለሃገራቸው ሰላም፣ ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ፣ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት፣ ለወንድማማችነትና እህትማማችነት፣ ለፍትሃዊነት፣ ለነፃነትና እኩልነት ላቀነቀኑት አንጋፋዎቹ የሀገር ባለውለታዎች ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን፣ የክብር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ፣ ማሕሙድ አሕመድ፣ ዓሊ ቢራ፣ ስብሐት ገብረእግዚአብሔርና ሐጫሉ ሑንዴሣ ናቸው።
ከእነዚህ በተጨማሪም ልናከብራቸው የሚገባን የሀገር ባለውለታዎች የሆኑ የጥበብ ሰዎች መኖራቸው ስለሚታወቅ ይህ ስራ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይደለም። ጥበብ ሀገርን ትስራለች፤ ሀገርም ጠቢብን ታስታውሳለች ብለዋል።
እነዚህ የመታሰቢያና የክብር ሃውልቶች በጥበብ ሞያቸው ለሀገር ያበረከቷቸው አስተዋጽኦ የሚዘከርበት ነው ተብሏል።
#ሀጫሉሁንዴሳ
#የጥበብኮከብ
#አዲስአበባ
#አፍሪካፓርክ
#የኢትዮጵያአሻራ
#EthiopianArt
#MusicLegend
እንኳን ለ85ኛው የዐርበኞች ድል በዓል አደረሳችሁ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
+++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለ85ኛው የዐርበኞች ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።