Select your region
and interface language
We’ll show relevant
Telegram channels and features
Region
avatar

Hasen Injamo

haseniye
Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው:: https://telega.io/c/Haseniye
Subscribers
15 038
24 hours
10
30 days
138
Post views
2 387
ER
15,87%
Posts (30d)
81
Characters in post
277
Insights from AI analysis of channel posts
Channel category
Business & Economy Blog
Audience gender
Male
Audience age
35-44
Audience financial status
Middle
Audience professions
Business & Management
Summary
November 02, 10:48

ሀጂ የደመወዝ መዳረሻ ከቴሌብር ብበደር ሀራም ይሆናል ወይ?
-> መድረስ ከቻልክ ችግር የለውም:: ዋናው ትደርሳለህ ወይ ነው ነጥቡ:: ከ10 ዓመታት በላይ ስናገር ኖሬያለሁ:: ይህኛው የፋይናንስ ሲስተም ሲበዛ ጨካኝ ነው:: ከወለድ ነጻ ይመጣል ብለህ አትጠብቅ:: መቼም አይመጣም:: ትናንትና እንደማይመጣው:: ከመደበኛው ቢብስ እንጂ አይሻልም:: ስለዚህ ከደመወዝ መበደሩን እርሳው:: ጉዳዩ ቤት አስይዘህ ከንግድ ብትበደርም አትደርስበትም:: በዚህ ሦስት ዓመት እኔም አንተም ፈጥነን ንብረት እንያዝ:: የማይፈራ ዑለማእ ቢኖር ጥሩ ነበር:: አንዳንዶቹ ካንተ የባሰ ቸግሯቸው ጺም እና አማማ ለባንክ እያከራዩ ናቸው:: ጭራሽ ባንተ ድህነት ላይ ፎቅ ይገነባሉ:: ፑ! ደህና የምትላቸው ዑለሞች ደግሞ ትንሽ ትንፍሽ ቢሉ በጺም አከራዮቹ ይሰ^ደባሉ:: ስ^ድቡን አይችሉትም:: እኔም ቆዳዬ አደንድኜ ሰ^ዳቢዎችን ቦልኬ ነው የተቋቋምኩት:: በዚያኛው ፌስቡክ አካውንቴ እኮ 5K የሚደርስ ተቦላኪ አለ::
መቸም ደመወዝ መዳረሻ ጠየቅኸኝም አይደል? መንግሥት እያለልህ ከመሥሪያ ቤት ጓደኛም ይሁን ከዘመድ አትበደር:: ለግለሰቦች ነውርህን ትዘከዝካለህ:: ኢማን እና ታማኝነትህን አስይዘህ ነው የምትበደረው:: ደመወዝተኛ በነበርኩ ወቅት እንዴት እንደሚጨንቅ አውቀዋለሁ:: ቴሌብር ስለኢማንህ አያገባውም:: በሰከንዶች ያበድርሃል:: ነውርህን ይሸፍንልሃል:: ከዚህ አዙሪት ግን ቶሎ ውጣ:: ጊዜ የለንም:: ሲስተሙ እየቆለፈ እየመጣ ነው::

November 02, 07:43

የኢትዮጵያ ባንኮችን ብድር ሢሦ የሚበደሩት አስር ሰዎች ናቸው:: የዓለም 75% ሀብት የተያዘው አስር ፐርሰንት በማይሞሉ ሰዎች ነው:: ይህ ለምን እንደሆነ በመ-ገንዘብ መጽሓፍ በደንብ ተብራርቷል:: እኔ ሲስተሙ ምን እንደሚመስል ከእነመፍትሔው ጽፌያለሁ:: ብዙ ጸሓፍትም ጽፈዋል:: ከየትኞቹ እንደምንሆን ውሳኔው የየግላችን ነው::

November 02, 06:09

በግል ሴቪንግ የሚንቀሳቀስ ምንጩ ያልታወቀ እንቅስቃሴ የባንክ ሲስተም Block እና Lock
🔒
እያደረገ ነው:: በዚህ ወቅት የገቢህ ምንጭ ከሁለት አቅጣጫ ብቻ እየሆነ ነው:: 1ኛ) ንግድ ፈቃድ አውጥቶ በደረሰኝ የገቡ ገቢዎች 2ኛ) ተቀጥሮ በደመወዝ እና አክሲዮን ገዝቶ በዲቪደንድ መልክ ነው የሚሆኑት ሌሎች ገቢዎች እንኳ ቋሚ ስላልሆኑ ብዙ ምድብ አናወጣላቸውም:: _____ በችርቻሮም ይሁን ጅምላ…

November 02, 06:09

በግል ሴቪንግ የሚንቀሳቀስ ምንጩ ያልታወቀ እንቅስቃሴ የባንክ ሲስተም Block እና Lock
🔒
እያደረገ ነው:: በዚህ ወቅት የገቢህ ምንጭ ከሁለት አቅጣጫ ብቻ እየሆነ ነው::
1ኛ) ንግድ ፈቃድ አውጥቶ በደረሰኝ የገቡ ገቢዎች
2ኛ) ተቀጥሮ በደመወዝ እና አክሲዮን ገዝቶ በዲቪደንድ መልክ ነው የሚሆኑት
ሌሎች ገቢዎች እንኳ ቋሚ ስላልሆኑ ብዙ ምድብ አናወጣላቸውም::
_____
በችርቻሮም ይሁን ጅምላ ንግድ ተሠማርታችሁ ግን ከኢምፖርተር የምትረከቡ ምእመናን የኢምፖርት ስልጠናው ይመለከታችሗል:: በ Less than Container Load (LCL) ሞድ ለምሳሌ 2 ሜትር ኪዩብ (CBM) መጫን ብጀምሩ ሲስተሙን ትለማመዱበታላችሁ:: (የተለያዩ መጠኖች ያሉዋቸው የመርከብ
🚢
ኮንቴይነሮች አሉ:: መደበኛዎቹን ብንወስድ ቮሊዩም ላላቸው እቃዎች ባለ68 ሜት ኪዩብ እና ለባለክብደት እቃ 28 ሜትር ኪዩብ በሚል ያዙት):: ስለዚህ በጣምራ አንዱን ሞልቶ ማምጣት ይቻላል:: ታዲያ አሁን ላይ ንግድ ፈቃድ የግድ ብሏል:: ባላችሁ ፈቃድ ላይ ኢምፖርት ታክሉበታላችሁ ከሌላችሁም ታወጣላችሁ:: ያው የራሱ ቅድመ ሁኔታዎች አሉት:: እንዴት እንደሚቀናጅ እና ፈቃድ እንዴት እንደሚወጣ ስልጠናዎቻችን ላይ አለ:: ሁሉንም በባለ ሙያ ነው:: Almost ሞልቶ ሊዘጋ ስለሆነ ግቡለት:: ዝርዝር በኮሜንት አለ:: ዊዝሆልድ የምትቆርጡ ተመዝጋቢዎች ቆርጣችሁ አስገቡና የዊዝሆልድ ደረሰኙን አምጡልን::

November 02, 03:14

የባንክ ሒሳባችሁ ከታገደ ከንግድ ፈቃድ ጋር የተያያዘ ሊሆን ስለሚችል TIN እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ይዛችሁ የከፈታችሁበት ባንክ ሄዳችሁ ማስለቀቅ ትችላላችሁ:: ምክንያቱም ከንግድ ፈቃድ ጋር ያልተያያዙ የባንክ አካውንቶች ላይ ብሮች ሲዘዋወሩ ሲስተሙ እየዘጋ ነው::
ቀጣይ አቅጣጫ የራስን እድል በራስ መወሰን እስከ መቀጠር የሚል ነው:: የቀጣሪነት ወይም የተቀጣሪነት እድላችሁን እራሳችሁ ናችሁ የምትወስኑት:: መቼለት ቴሌግራም "ቀጣሪ ወይስ ተቀጣሪ?" Live ፕሮግራሜ ይህንን የተመለከተ ነበር:: የባንኩንም አንስቼዋለሁ:: ወይ ድርጅት ከፍተህ ቀጣሪ ትሆንና እያንዳንዱ እንቅስቃሴህ በደረሰኝ ይሆናል ወይ ተቀጣሪ ሆነህ ገቢህ በፔይሮል ይሆናል:: (መ-ገንዘብ 2 ስለዚህ ጉዳይ ነው የሚያወራው)::

November 01, 10:02

የግብርና ባንክ በኢትዮ FM
📻
107 በዓብዱልቃዲር ኑረዲን ከእስከዳር ጋር

October 31, 12:30
Media unavailable
1
Show in Telegram

ዛሬ የነበረው የ Live ፕሮግራም አንኳር ነጥቦች

October 31, 10:02

Live stream finished (55 minutes)

October 31, 09:07

Live stream started

October 31, 06:35

ዛሬ ቀጣሪ ወይስ ተቀጣሪ? በሚል ርዕስ Live ይኖረናል:: ቀጣይ ሲስተሙ በዚህ እየከፈለን ስለሆነ ጎራችንን ለመለየት ይረዳናል:: ሲስተሙ እየቆለፈና እያጠበበ ነው::