
ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa
👉
አዲስ pdf
عنوان:- الفصل المبين في دحض شبهات وتلبيسات محمد حامي الدين.
ርእስ:- ግልፅ የሆነ መለያ፣ የሙሀመድ ሃሚዲንን ብዥታና ማምታቻ በማጋለጥ ላይ…
📝
بقلم الشيخ الدكتور حسين بن محمد بن عبد الله الإثيوبي السلطي حفظه الله
📝
አዘጋጅ፦ ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ ቢን ዐብደላህ አል-ኢትዮጲ አስ-ሲልጢይ (ሀፊዘሁላህ)
(ዐረቢኛ የምትችሉ pdf አውርዳችሁ አንብቡት)
#join
⤵️
ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/HussinAssilty
https://t.me/HussinAssilty
قد أجاد الشيخ الدكتور حسين ـ حفظه الله ـ وأفاد في ردّه على الشيخ محمد حامي الدين، فقد كتب رسالةً قيمةً نفيسةً، نافعةً لمن أيقظه الله تعالى من نوم الغفلة والهوى والتعصب والتقليد الأعمى، وأراد الحقَّ والإنصاف.
فجزى الله الشيخ خير الجزاء، وبارك في علمه وعمله، ونفع بجهوده، وزاده الله تعالى علمًا وبصيرةً وثباتًا على الحق والسنة.
✍🏻
الشيخ محمد حيات الولوي حفظه الله
هذه النسخة أولى من النسخة الأولى
አዲስ Pdf
عنوان :- الرد المبين على محمد حامي الدين
في ثنائه على رئيس الإخوان وقائدهم سيد قطب وأمثاله
✍
للشيخ محمد بن حيات الولوي حفظه الله
ሙሀመድ ሃሚዲን የኢኽኑ'ል ሙስሊሚን መሪ የነበረውን ሰይድቁጥብን ባወደሰበት ንግግሩ ላይ የተሰጠ ግልፅ ምላሽ
https://t.me/SheikMohmmedHyatHara
https://t.me/SheikMohmmedHyatHara
✅
جزاكم الله خيرا وبارك فيكم ورفع قدركم في الدنيا والآخرة فقد اطلعت على البحث فوجدته نافعا وجامعا لانحرافات المردود عليه وزيادة على ما في الفيدو الأخير . والراد على أهل البدع مجاهد فكتب الله أجركم وسددكم وثبتكم على التوحيد والسنة حتى الممات.
✍🏻
الشيخ الدكتور حسين السلطي حفظه الله
ዘመን መለወጫና ሙስሊም
—————
ሙስሊሙን ማህበረሰብ በየትኛውም መንገድ ዘመን መለወጫ የሚባል ነገር አይመለከተውም!!።
ለዘመን መለወጫም ሆነ ለሌሎች ለከሀዲዎች በዓላቶቻቸው እንኳን አደረሳችሁ ማለት በእስልምና ሀይማኖት የማይፈቀድ (ሀራም) ነው!!
የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:-
“
በ(ከሃዲያን) ሰዎች የተመሳሰለ እርሱ ከእነሱ ጋር ነው።
" [አቢዳውድ 4033 ላይ ዘግበውታል።]
የፈረንጆችንም ሆነ የማንንም ዘመን መለወጫ ማክበር በኢስላም በጥብቅ የተከለከለ ነው!!
በእስልምና ዘመን መለወጫ የሚባል ነገር የለም።
አንድ የሰውን ህይወት ያጠፋ ሰው "እንኳን ለዚህ አበቃህ (አደረሰህ)" ተብሎ የደስታ መግለጫ እማይደረግለት ከሆነ፣ ከዚህ የከፋውን ተግባር በመፈፀም በአለማቱ ጌታ በብቸኛው አምላክ አላህ ክዶ "
እንኳን በፈጣሪህ ክደህ ያሻህን ልታመልክና ልትሰራ አደረሰህ
" ይባላልን?!
በበዓላቸው ልጆች እንዳይቦዝኑብኝ ብሎ ማረድም ሆነ ሌሎችን ከነሱ የሚያመሳስል ነገር መስራት አይፈቀድም!!። የሙስሊም ልጆችን የራሳችን የሙስሊም በዓል አለን ብሎ ማስተማር ነው!!።
እነሱ ለበዓላቸው የሰሩትን አምጥተው ቢሰጡ ተቀብሎ መብላትም አይፈቀደም!!
እነሱ ለራሳቸው ጊዜ ጥግ የደረሱ አክራሪዎች ሆነው የነሱን እምነትና ባህል የኛም እምነትና ባህል እንዲሆን ይተጋሉ!። እኛን ደግሞ የራሳችን ድንቅ ሀይማኖት አለን ብለን ቆፍጠን ስንል "
አክራሪ፣ ፀረ አንድነት፣ ፀረ ሰላም፣ ፀረ መቻቻል… ፀረ ፀረ ፀረ…
" ይሉናል።
ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሀይማኖቱን እሴት አክብሮ ሊኖር ይገበዋል። ከከሀዲዎች ጋር የጋራ በዓልም ሆነ እምነት የለንም!!። ለኛ የራሳችን እምነትና በዓል አለን!!። የምናደምቀው የራሳችን እምነትና በዓል ነው። በነሱ በዓል ጊዜ ሙስሊሙ አብሮ ግርግር እንዲፈጥር የሚያደርገው ነገር የለም።
አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-
قُلْ يَا أَيُّهَا الْكَافِرُونَ لَا أَعْبُدُ مَا تَعْبُدُونَ وَلَا أَنتُمْ عَابِدُونَ مَا أَعْبُدُ وَلَا أَنَا عَابِدٌ مَّا عَبَدتُّمْ وَلَا أَنتُمْ عَابِدُونَ مَا أَعْبُدُ لَكُمْ دِينُكُمْ وَلِيَ دِينِ
«
በላቸው፣ እናንተ ከሓዲዎች ሆይ! "ያንን የምትግገዙትን አልግገዛም፡፡እናንተም እኔ የምግገዛውን ተገዢዎች አይደላችሁም፡፡ እኔም ያንን የተገዛችሁትን ተገዢ አይደለሁም፡፡ እናንተም እኔ የምግገዛውን (አሁን) ተገዢዎች አይደላችሁም፡፡ ለእናንተ ሃይማኖታችሁ አልላችሁ፡፡ ለእኔም ሃይማኖቴ አለኝ!፡፡»
አል-ካፊሩን 1-6
ይሄው ነው! እስልምናችን መጨመላለቅንና አጎብዳጅነትን አላስተማረንም!! ሀይማኖትህን ለማስከበር ቀድመህ አንተው መርሆቹን አክብር!!።
"ይሄ እኮ የጋራ በዓል ነው፣ የሀገራችን ዘመን መለወጫ እንጂ ሌላ ነገር የለውም" እያለ ሊያጃጅልህ ሲሞክር መጃጃልህን ትተህ አትተሻሽ "አይ! እምነቴ አይፈቅድልኝም!።" በለው። የሀገራችን የካላንደር አቆጣጠር ራሱ ከየት መጣና ነው? የራሳቸው የከሀዲያን አቆጣጠር ነው። እኛ የሚወክለን አቆጣጠር ኢስላማዊ (ሒጅሪይ) ነው፣ ለሱም ቢሆን እምነታችን ዘመን መለወጫ ብለን ማክበር አይፈቅድልንም። ዒዳችን ሁለት ዒዶች ናቸው፣ ዒዱል አድሃና ዒዱል ፊጥር፣ ከዚህ ውጭ ሳምንታዊ ጁምዐህ ነው፣ አበቃ። የትኛውም ዘመን መለወጫ የሚባል ኮተት ሙስሊሙን አይወክለውም!!።
✍🏻
ኢብን ሽፋ (
t.me/ibnshifa
)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን
⤵️
#join
በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel:
⤵️
⤵️
https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f
ጠያቂ:- የሙነወር ልጅ (ኢብኑ ሙነወር) ከትክክለኛው መንሀጀ'ሰለፍ የወጣበትን ነጥብ በዝርዝር ብትጠቅሱልን? መልስ:- ከሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)
🔷
ክፍል
1⃣
➥ የሙነወር ልጅ ከጠንካራው የሠለፎች መንገድ ተዘንብሎ ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ጋር የተካተተበትን ነጥብ ለጠየቀ ሰው የተሰጠ መልስ። እወቅ! አላህ ይዘንልህና ደጋግ ቀደምቶች ቢድዓንና ባለቤቶቹን…
ጠያቂ:-
የሙነወር ልጅ (ኢብኑ ሙነወር) ከትክክለኛው መንሀጀ'ሰለፍ የወጣበትን ነጥብ በዝርዝር ብትጠቅሱልን?
መልስ:-
ከሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ
(ሀፊዘሁላህ)
🔷
ክፍል
1⃣
➥ የሙነወር ልጅ ከጠንካራው የሠለፎች መንገድ ተዘንብሎ ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ጋር የተካተተበትን ነጥብ ለጠየቀ ሰው የተሰጠ መልስ።
እወቅ! አላህ ይዘንልህና ደጋግ ቀደምቶች ቢድዓንና ባለቤቶቹን በመጥላትና ከእነርሱም በመራቅ ላይ በእርግጥ ተስማምተዋል።
ኢማሙ ሷቡኒይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:- "…
ደጋግ ቀደምቶች የቢድዐህ ባለቤቶች ላይ የበላይ በመሆንና እነሱን በማዋረድ፣ ከእነርሱም በመራቅ፣ እነሱን ባልደረባ አድርጎ ከመያዝና አብሯቸው ከመኗኗር በመራራቅ፣ ተስማምተዋል። እነርሱን በመራቅና በመዝጋት ተግባርም ወደ አላህ በመቃረብ ላይ ተስማምተዋል።
" [ዐቂደቱ ሰለፍ ሊሷቡኒይ]
= የደጋግ ቀደምቶችን የጋራ ስምምነት የተፃረረ፣ አለያም ለቢድዐህ ባለ ቤቶች የተከላከለ ሰው፣ አለያም የቢድዐህን ባለ ቤት ያወደሰ ሰው እርሱን ከቢድዐህ ባለቤቶች ያስጠጉታል ክብር የለውም። ይልቁንም ከቢድዐህ ባለቤቶች ጋር የሚቀማመጥ ሰው ስለ ቢድዐህ ባለቤቶች ግልፅ ካልሆነለት ይብራራለታል፣ ተብራርቶለትም መቀማመጡን ከቀጠለ ወደዚያው ይካተታል(እሱም ከቢድዐህ ሰዎች ይመደባል)፣ደጋግ ቀደምቶች በዚህ መልኩ ነው የተጓዙት። በእርግጥም አምላካችን አላህ ወንጀል (ኃጢያት) የሚሰራና ሳይሰራ አብሮት የሚቀማመጥን ሰው እኩኩል አድርጓቸዋል፣ እስካልራቃቸው ድረስ ብይኑ ተመሳሳይ ነው። አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-
وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِي الْكِتَابِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ آيَاتِ اللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا مَعَهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ ۚ إِنَّكُمْ إِذًا مِّثْلُهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ جَامِعُ الْمُنَافِقِينَ وَالْكَافِرِينَ فِي جَهَنَّمَ جَمِيعًا
«
በእናንተም ላይ በመጽሐፉ ውስጥ የአላህን አንቀጾች በርሷ ሲካድባትና በርሷም ሲላገጥባት በሰማችሁ ጊዜ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከእነሱ ጋር አትቀመጡ፡፡ ማለትን በእርግጥ አወረደ፡፡ እናንተ ያንጊዜ ብጤያቸው ናችሁና፡፡ አላህ መናፍቃንን እና ከሀዲዎችን በሙሉ በገሀነም ውስጥ ሰብሳቢ ነውና፡፡
» አን'ኒሳእ 140
አል ኢማም ኢብኑ ተይሚየህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- "
ለዑመር ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ኸምር (አስካሪ መጠጥ) የሚጠጡ የነበሩ ሰዎችን ይዘው አመጡለት፣ እንዲገረፉም አዘዘ፣ ከእነሱ ውስጥ ፆመኛ ሰው አለ ተባለ፣ ከፆመኛው ጀምሩ አለ፣ አላህ እንዲህ ማለቱን አልሰማችሁም እንዴ?
وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِي الْكِتَابِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ آيَاتِ اللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا مَعَهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ ۚ إِنَّكُمْ إِذًا مِّثْلُهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ جَامِعُ الْمُنَافِقِينَ وَالْكَافِرِينَ فِي جَهَنَّمَ جَمِيعًا
«
በእናንተም ላይ በመጽሐፉ ውስጥ የአላህን አንቀጾች በርሷ ሲካድባትና በርሷም ሲላገጥባት በሰማችሁ ጊዜ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከእነሱ ጋር አትቀመጡ፡፡ ማለትን በእርግጥ አወረደ፡፡ እናንተ ያንጊዜ ብጤያቸው ናችሁና፡፡ አላህ መናፍቃንን እና ከሀዲዎችን በሙሉ በገሀነም ውስጥ ሰብሳቢ ነውና፡፡»
አን'ኒሳእ 140
ዑመር ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ (ረዲየላሁ ዐንሁ) አንድ ሰው
የተወገዘ ተግባር ከሚሰራ ሰው ጋር መገኘቱ በራሱ ሰውዬው ባይሰራም እንኳ አላህ ልክ እንደሰሪው እንዳደረገው ግልፅ አድርጓል።
[መጅሙዕ አል ፈታዋ 28/221]
አል ኢማም ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) ተጠየቁ: የቢድዐህ ባለቤቶችን የሚያወድስና የሚያሞግስ ሰው የነሱን ብይን ይዛል (ከቢድዐህ ባለበፀቶች ይሆናል?)
መልስ:-
አዎን ጥርጣሬም የለውም!። እነሱን ያወደሳቸውና ያሞገሳቸው ሰው የነሱ ተጣሪ ነው፣ አላህ ይጠብቀንና ሰዎችን ወደነሱ ጠርቶላቸዋል
። [ሸርህ ፈድሉ'ል ኢስላም]
በእርግጥ የሙነወር ልጅና ሌሎችም ሙመይዓዎች በሁለት ነጥቦች ተፈትነዋል:- የመጀመሪያው የተብዲዕ ነጥብ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የጀርህና ተዕዲል ነጥብ ነው። የሙነወር ልጅና ከእርሱ ጋር ያሉ ሰዎች በዒልመል ሀዲስ (በሀዲስ እውቀት)፣ በጀርህና ተዕዲል ላይ ጥግ የደረሱ መሀይሞች ናቸው። የሙነወር ልጅ የተመረቀው በታሪክ ጥናት ነው፣ ሸሪዓዊ በሆነ እውቀት ላይ ግንኙነት የለውም፣ ከመሻይኾቹም ከአህሉሱንና የሆኑ መሻይኾችን አናውቅለትም። በሱንና ዑለማዎች ላይ ባልተማረ ሰው መማሩ ደግሞ አይፈቀደም!። ሰለፎች እንዲህ ብለዋል:- "
ይህ እውቀት ዲን ነው፣ ዲናችሁን ከማን እንደምትይዙ ተመልከቱ።"
በእርግጥም የሙነወር ልጅ ለመርከዝ ኢብኑ መስዑድ በመከላከልና የሱንና ዑለማእዎችን በመተቸት ላይ እራሱን አጋልጧል (አንገቱን) ቀና አድርጓል፣ የቅርቡም የሩቁም ሁሉ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎች ከመንሀጀ'ሰለፍ ወጥተው ከአል ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር መጠቃለላቸውንና ሠለፊዮችን በሁሉም ቦታ የሚዋጉ መሆናቸውን በእርግጠኝነት አውቋል። ይህ ተግባራቸው ደግሞ ንፁህ አዕምሮ ላለውና ሚዛናዊ ለሆነ ሠለፊይ ሁሉ ግልፅ ነገር ነው፣ ለመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎች አይከላከልም ከእነሱ የሆነ ቢሆን እንጂ።
የሙነወር ልጅ ለመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎች በመከላከል በርካታ የተለያዩ ፅሁፎችን ፅፏል፣ እንዲያውም ለኢልያስ አህመድ እየተከላከለ "የቢድዐህ ባለቤቶችን ያወደሰ ከሱንና አይወጣም" ብሏል፣ ይህን ለማጠናከርም በቀጣይ እንደሚቀርበው በበርካታ ዑለማዎች ላይ ቀጥፏል።
እንደሚከተለው የተወሰኑ የሙነወርን ልጅ የጥመት ሰበቦችን ማስታወስ ይቻላል:-
በቅድሚያ እንደማንቂያ:-
ቀደም ሲል በነበሩ ጊዜዎች የሙነወር ልጅ በመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎች ላይ ይናገር እንደነበር ማንም አይጠራጠርም። ጥፋታቸውን ግልፅ አድርጎ ከአል ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር እየተጓዙ እንደሆነ ተናግሮ ሠለፊዮችም በዚህ ተግባሩ ተደስተው አመስግነውት ከጎኑ ቆመው እንደነበር ይሰመርበት።
1ኛ
, ከዚያ በኋላ በመርከዙ ሰዎች ላይ ከመናገር፣ ከቀጠለውና እየበዛ ከመጣው ጥፋታቸው (ወደ ቢድዐህ) ማዘንበላቸው ምላሽ ከመስጠት ቆመ። ልቦች በአላህ እጅ ናቸው፣ የላቀው አላህ እንደፈለገ ይገለባብጣቸዋል፣ በዚህ ምክንያትም የሱንና መሻይኾች በኢብኑ መስዑ መርከዝ ሰዎች ላይ ያለውን ትክክለኛ አቋም ግልፅ እንዲያደርግ ጠየቁት።
2ኛ
, ጭራሹኑ ለመርከዙ ሰዎች ምክንያት ይደረድርላቸው ጀመር፣ በተቃራኒው ደግሞ የሱንና መሻይኾችን መተቸት ጀመረ፣ ሸይኽ ዐ/ሐሚድንና ሸይኽ ሐሰን ገላውን ይመስል፣ ቆሻሻ በሆኖ ገለፃዎች ሁሉ ማጠልሸት ጀመረ፣ ወደ ሀዳዲይነትም አስጠጋቸው፣ ሰለፎች እንዳሉት ደግሞ ከቢድዐህ ባለቤቶች መገለጪያ አንዱ የሱንና ሰዎችን መተቸት ነው።
ይቀጥላል…
✍🏻
ትርጉም
:- ኢብን ሽፋ
#Join
⤵️
⤵️
ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel:
⤵️
⤵️
https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f
ለኢብኑ ሙነወር የተሰጠ ምላሽ
ርእስ
:-
ሠለፊዮችን መዳኺላ የሚለው ማንነው?
🎙
በሸይኽ ዶ/ር
ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ
(ሀፊዘሁላህ)
በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል
ጥር 17/2016 የተደረገ
የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም
👇
👇
ቻናል
#join
በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444