ተንቢሃት Tenbihat – ኢስላማዊ ህግጋት እና ተግሳፃት
የጨዋነት (ሐያእ) ሚስጥራዊ ኃይል!
ኢብኑ ሓዝም እንዳህ ይላሉ፦
"
ወንድ መባል የሚገባውን ወንድ" የሚማርከው የሴት ልጅ አይነ-አፋርነትና ክብሯ ነው። ይህ አይነቱ ወንድ በቅጥ ያጣ ንግግር ወይም በብልጭልጭ ነገር አይታለልም። ይልቁንም የሴት ልጅ ቁጥብነት እንደ ትልቅ ግርማ ሞገስ ይስበዋል።"
አስተዋይ ወንድና "ሀያእ" የሌላት ሴት
አስተዋይና በራሱ የሚተማመን ወንድ፣ ጨዋነቷ ከቀነሰና ዝርክርክነቷ ከበዛ ሴት ይሸሻል። ለምን ቢባል፡-
መቅለልን ይጠላል፡ ብዙ የሚያወሩና በየቦታው የሚታዩ ሴቶች በአስተዋይ ወንድ ዘንድ ክብራቸው የቀለለ ሆኖ ይታያል።
መረጋጋትን ይፈልጋል፡ አንድ ወንድ የህይወት አጋሩ እንድትሆን የሚመኛት ሴት፣ ቤቱንና ክብሩን የምትጠብቅ እንጂ ለሰው ሁሉ ግልጽ የሆነች አጋርን አይደለም።
ሙሉ የሆነ ጨዋነት
ከላይ እንዳሳለፍነው፣ ጨዋነት በአንድ ነገር ብቻ አይገለጽም፤ ይልቁንም በሁለንተናዊ ማንነት ውስጥ ይንጸባረቃል፡-
በአረማመድ፡ በትዕቢት ወይም ሰውን ለመሳብ ሳይሆን በክብር መራመድ።
በአለባበስ፡ ውበትን የሚገልጥ ሳይሆን ክብርን የሚሸፍን ልብስ።
በንግግር፡ ድምፅን ዝቅ አድርጎ፣ ቁምነገር ያለውና ለዛ ያለው ንግግር።
በአይን እይታ፡ ሁሉንም ነገር ለማየት ከመቅበዝበዝ ይልቅ አይንን በመስበር የሚገለጽ አይነ-አፋርነት።
"ለእያንዳንዱ ሃይማኖት የራሱ ስነ-ምግባር አለው፤ የኢስላም ስነ-ምግባር ደግሞ ጨዋነት (ሀያእ) ነው!"
እንደዚህ አይነት ሴት ናት እንግዲህ ወንድ ልጅ ውድ ዋጋ ሊከፍልላትና ሊያገኛት የሚመኛት። ምክንያቱም እሷ በቀላሉ የምትገኝ "ሜዳ ላይ ያለች አበባ" ሳትሆን፣ በጥብቅ ጥበቃ ውስጥ ያለች "ውድ ዕንቁ" ናት።
በእውነትም ጨዋነት(ሐያእ) የሴት ልጅ ዘውድ ነው!
🌸
🍃
የዒድ ዋዜማና የዒድ ቀን ሱናዎችና አዳቦችን አንድ ሙስሊም ሊያከናውናቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦
1
. ተክቢራ ማድረግ
፦
ይህ ከታላላቅ የዒድ ሱናዎች አንዱ ነው። አላህ በቁርአኑ፦ "...ቁጥሩንም እንድትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ልታልቁት (ተክቢራ ልትሉ) (ታመሰግኑት) ዘንድ (ደነገገላችሁ)" (አል-በቀራህ፡ 185) ብሏል።
*
ወቅቱ
፦ ከዒድ ዋዜማ ጀምሮ ኢማሙ ለሶላት እስከሚወጣ ድረስ ባለው ጊዜ ወንዶችም ሴቶችም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው (ሴቶች ለብቻቸው ሲሆኑ) ተክቢራ ማድረጋቸው የተወደደ ነው።
2.
መታጠብ (ጉስል
)፦
ለዒድ ሶላት ከመውጣታቸው በፊት መታጠብ የሰለፎች ተግባር ነው። ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ወደ ዒድ ሶላት ከመውጣታቸው በፊት ይታጠቡ እንደነበር ተዘግቧል።
3.
በልቶ ወደ መስገጃው ስፍራ መውጣት (በዒድ አል-ፊጥር
)፦
ወደ ሶላት ከመውጣት በፊት ጥቂት ተምሮችን (በቁጥር ጎዶሎ ቢሆኑ ይመረጣል) መብላት ሱና ነው።
ነቢዩ (ﷺ) ተምሮችን ሳይበሉ ለዒድ ሶላት አይወጡም ነበር። (ቡ
ኻሪ ዘግበውታል)
4.
ማጌጥና ጥሩ ልብስ መልበስ
፦
ለዒድ ቀን ካሉህ ልብሶች ሁሉ ምርጡንና የክቱን ልብስ መልበስ ይወደዳል። ጃቢር (ረዲየሏሁ ዐንሂ) እንደዘገቡት
ነቢዩ (ﷺ) በሁለቱ ዒዶችና በጁምዓ ቀን የሚለብሱት የሚያምር ካባ ነበራቸው።
(ኢብኑ ኹዘይማህ ዘግበውታል)
* ማሳሰቢያ፦ ወንዶች ሽቶ መቀባት ይወደድላቸዋል፤
ሴቶች ግን ከቤት ሲወጡ ሽቶ መቀባትና ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን ትኩረት የሞሰብ እጅግ የተዋባ ልብስ መልበስ የለባቸውም።
5
. የዒድ ሶላትን በጀመዓ መስገድ
፦
ምንም እንኳ አንዳንድ ዑለማዎች ሱና ነው ቢሉም፣ ትክክለኛው አቋም ግን (እንደ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ)
የዒድ ሶላት በሁሉም ላይ ዋጅብ (ግዴታ) መሆኑ ነው።
6.
መንገድ መቀየር
፦
ወደ ሶላት የሄዱበትን መንገድ ትቶ በሌላ መንገድ መመለስ ሱና ነው። ጃቢር ኢብኑ ዐብዱላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንደዘገቡት፦ "
ነቢዩ (ﷺ) በዒድ ቀን መንገድ ይቀይሩ ነበር።
" (ቡኻሪ ዘግበውታል)
7.
የእንኳን አደረሳችሁ መለዋወጥ (ተህኒያህ)፦
ሰዎች ሲገናኙ፦ "
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም" (አላህ ከእኛም ከእናንተም መልካም ሰራችን ይቀበል) በማለት እንኳን አደረሳችሁ መባባል መልካም አዳብ ነው። ይህ በሶሐባዎች ዘንድ ይዘወተር ነበር።
ማጠቃለያ
እነዚህ ተግባራት ዒድን በሸሪዓዊ መልኩ እንድናከብርና የአላህን ችሮታ እንድናስታውስ ይረዱናል። በተለይ በዋዜማው ተክቢራን ማብዛትና በዕለቱ ዝምድናን መቀጠል ትልቅ መንፈሳዊ ፋይዳ አለው።
አላህ ዒዱን የሰላምና የደስታ ያድርግልን!
https://t.me/sultan_54
ይህንን መልዕክት በሰፊው ለሰዎች እንዲደርስ ለሌሎች ያጋሩ።
📣
ዘካተል ፊጥር ላልሰጣችሁ
🌾
ዘካተል ፊጥር መሰብሰቢያ ሰዓት ስላራዘምን ያልሰጣቹ ወንድምና እህቶች ዛሬ እስከ ቀኑ 10:00 ድረስ ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ::
ኢብኑ መስዑድ እስላሚክ ሴንተር
📣
ዘካተል ፊጥር መሰብሰብ ጀምረናል
❗
▪️
ከንባታ ፣ወሊሶ፣ ጉራጌ ዞን፣ ሸገር ሲቲ እና አዲስ አበባ አካባቢ ላሉ ለተቸገሩ ወገኖቻችን ዘካተል ፊጥራችሁን ለናንተ ወኪል ሆነን በጤፍ ወይንም በፉርኖ ዱቄት ለማድረስ ዝግጅታችንን አጠናቀናል::
▪️
የ 1ሰው ተመን በጤፍ 300 ብር
በፉርኖ ዱቄት 275 ብር
▪️
ገቢ የምታደርጉበት አካውንት
ንግድ ባንክ 1000742126386
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
⚠️
ዘካውን በጤፍ ተመን የምታወጡ ያስገባችሁበትን ደረሰኝ በ 0904366666 ላይ በቴሌግራም ላኩልን።
⚠️
ዘካችሁን የምንቀበለው እስከ ረቡዕ ረመዳን 29 ከቀኑ 7:00 ድረስ ብቻ ይሆናል።
__
🕌
ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር
Http://telegram.me/merkezuna
📣
አደራችሁን አድርሰናል! አልሃምዱሊላህ
ደካሞችን የማስፈጠር ኸይር ስራ ጥሪ ምላሽ የሰጣቹ የመርከዝ ተማሪዎች፣ ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ያላችሁ እህትና ወንድሞች እንዲሁም ለዚህ ፕሮግራም መሳካት አስተዋጽዖ ያደረጋችሁ ሁሉ አላህ መልካም ስራችሁን ይቀበላችሁ
جزاكم الله خيرا
____
🕌
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
📲
t.me/merkezuna
ዘካተል ፊጥር እና አፈጻጸሙ
በወንድም ጣሀ አህመድ
ዘካተል ፊጥር ከረመዳን ወር ፆም መጠናቀቅ ጋር በተያያዘ ግዴታ የሚሆን የዘካ አይነት ነው፡፡ ዘካተል ፊጥርን መስጠት እያንዳንዱ ሙስሊም ላይ በነፍስ ወከፍ ግዴታ ሲሆን፤ እያንዳንዱም አባወራ የራሱን ጨምሮ በእርሱ ስር ስላሉ ቤተሰቦቹ ሁሉ መስጠት ይጠበቅበታል፡፡ ኢብኑል ሙንዚር ‘አል-ኢጅማዕ’ በተሰኘው ኪታባቸው ‹‹ዒልምን የተማርንባቸው ዑለማዎች ሁሉ ዘካተል ፊጥር ግዴታ መሆኑን ተስማምተውበታል›› በማለት የጉዳዩን ግዴታነት ከሚያመለክቱት ነብያዊ ሀዲሶች በተጨማሪም የኡለማዎችን አጠቃላይ ስምምነት (ኢጅማዕ) የተገኘበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
√ የተደነገገበት ጥበብ
ድሆች በባዕሉ (ዒድ) እለት ሰዎችን ከመለመን እንዲድኑና የእለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ ማድረግ እንዲሁም በፆም ወቅት ተከስተው ላለፉ አንዳንድ ጉድለቶች (ግድፈቶች) ማሟያ እንዲሆን ነው፡፡
ይህን አስመልክቶ ዐብደላህ ኢብን አባስ እንዲህ ይላሉ፤
عن ابن عباس ـ رضي الله عنهما ـ قال: "فرض رسول الله صلى الله عليه وسلم زكاة الفطر طهرة للصائم من اللغو والرفث وطعمة للمساكين، فمن أداها قبل الصلاة فهي زكاة مقبولة، ومن أداها بعد الصلاة فهي صدقة من الصدقات" رواه أبو داود
وابن ماجه
‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ዘካተል ፊጥርን ለፆመኛ ለ ‘ለግዉ’ (ጥቅም ለሌላቸው ውድቅ የቀልድ ንግግሮችና ተግባሮች) እና ለ ‘ረፈስ’ (ፆታዊ ስሜትን ቀስቃሽ ለሆኑ ንግግሮች) ማፅጃ፤ ለምስኪኖች (ድሆች) መብል ሲሆን በግዴታ መልኩ ደንግገውታል፡፡ ስለዚህም ከኢድ ሰላት በፊት (ዘካውን በመስጠት ግዴታውን የተወጣ) ተቀባይነት ያለው ዘካን ሰጥቷል፤ ከኢድ ሰላት በኋላ ዘካውን የሰጠ ከሌላ ግዴታ ያልሆነ ሰደቃ አንዱ እንደሆነ ይታሰብለታል፡፡››
(አቡዳውድ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል)
√ የዘካተል ፊጥር መጠን
ኢብኑ ኡመር ሀዲስ ላይ እንዲህ የሚል መልዕክት ስለተላለፈ ነው፤ ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ከተምር ወይም ከገብስ አንድ ‹‹ሷዕ›› በእያንዳንዱ ሙስሊም፤ ባሪያ፣ ጨዋ (ባሪያ ያልሆነ)፣ሴት፣ ህፃን፣ አዋቂ ላይ ግዴታ አድርገዋል፡፡ እንዲሁም ሰዎች ወደ (ዒድ) ሰላት ከመውጣታቸው በፊት ለሚገባቸው ሰዎች እንዲደርስ አዘዋል፡፡›› (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ሷዕ የመስፈሪያ አይነት ሲሆን በድሮ ጊዜ የነበረ የእህል መስፈሪያ ነው። በዘመናዊ መለኪያ አንድ ‹‹ሷዕ›› 2.04-2.5 ኪ.ግ ይመዝናል፡፡ 1 ሷዕ = 4 የሁለት ዕጅ እፍኞች ነው።
√ ዘካተል ፊጥር በማን ላይ ግዴታ ይሆናል?
ዘካተል ፊጥር ግዴታ የሚሆነው ሁለት መስፈርቶችን ባሟላ ሰው ላይ ብቻ ነው፤ እነርሱም 1. ሙስሊም በሆነ 2. ዘካተል ፊጥር ማውጣት ግዴታ በሚሆንበት ቀን እና ሌሊት፤ ለራሱ እና ለቤተሰቦቹ የሚበቃ መብል ኖሮት የተረፈው እና ተጨማሪ ነገር ያለው፡፡
√ ዘካተል ፊጥር የሚሰጠው መቼ ነው?
ዘካተል ፊጥርን ከ(ዒድ) ሰላት በኋላ ማዘግየት የተከለከለ ሲሆን፤ ማውጣቱ ግዴታ የሚሆንበት ወቅት የሚጀምረው ከረመዳን የመጨረሻው እለት ፀሀይ ከጠለቀችበት ወይም ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰዓት አንስቶ ነው፡፡ ነገር ግን ኢብኑ ዑመርን ጨምሮ ሌሎቹም ሰሀቦች ያደርጉት እንነበረው ከዒድ አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀድሞ ዘካተል ፊጥርን ማውጣት ይፈቅዳል፡፡
√ ለዘካተል ፊጥር የሚሰጡ የእህል አይነቶች
ዘካተል ፊጥር ሙስሊሞች ከሚመገቡዋቸው እንደ እሩዝ፤ በቆሎ፤ ጤፍ…. ባሉ የምግብ እህል አይነቶች ነው። መልእተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) በሀዲስ የጠቀሷቸው የምግብ እህሎች (እንደ ገብስ፤ ተምር፤ ዘቢብ) የመሳሰሉት ሲሆኑ፤ ነገር ግን የምግብ አይነቶቹ በነዚህ ላይ ብቻ እንደማይገደቡ የሻፊዒያ እና የማሊኪያ መዝሀብ ዑለማዎች ሲስማሙበት ሸይኹል ኢስላምም የመረጡት አቋም ነው፡፡
የአላህ መልአክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ከተምር ወይም ከገብስ አንድ ‹‹ሷዕ›› እንዲወጣ ማዘዛቸውን በተመለከተም እነዚህ ዑለማዎች የሚሰጡት ምላሽ ‹‹መልእክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) እነዚህን የምግብ አይነቶች የጠቀሱት የመዲና ሰዎች በምግብነት ይጠቀሟቸው የነበሩ ከመሆናቸው አንፃር ነው፡፡ ስለሆነም የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) አነሱ የሚያገኙትንና የሚመገቡትን የምግብ አይነት ነው እንዲያወጡ ያዘዟቸው›› የሚል ነው፡፡
በዚህም መሰረት በማንኛውም አካባቢ የሚኖር ሙስሊም ማህበረሰቡ አዘውትሮ ከሚመገባቸው የምግብ እህሎች ዘካተል ፊጥሩን መልዕክተኛው ሲጠቀሙበት በነበረው መስፈርያ መጠን ማውጣት ይችላል፡፡
√ ዘካተል ፊጥር መሰጠት የሚገባው ለማን ነው?
በዚህ ጉዳይ ላይ ዑለማዎች ሁለት አይነት አመለካከት ያለቸው ሲሆን ሚዛን የሚደፋው ሀሳብ ለምስኪኖች እና ለድሆች ብቻ ይሰጣል የሚለው ነው፡፡ ምክንያቱም በኢብኑ አባስ ሀዲስ ላይ መልዕክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ‹‹ለምስኪኖች መብል …›› በማለት ዘካተል ፊጥር የተደነገገበትን አላማ ከመግለፃቸው ጋር የተያያዘ ነው፡፡
√ ዘካተል ፊጥርን በገንዘብ ተምኖ መክፈል
ዘካተል ፊጥርን በዋጋ ተምኖ መክፈል አይፈቀድም።
ምክንያቱም፤ በኢብኑ አባስ ሀዲስ ላይ መልዕክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ዘካተል ፊጥር የተደነገገበትን አላማ ሲገልፁ ‹‹ለምስኪኖች መብል …›› በማለታቸው ጋር የተያያዘ ነው፡፡
አቢ ሰዒድ አልኹድሪይ እንዲህ ብለዋል፤
“የአላህ መልዕክተኛ በነበሩበት ዘመን ዘካተል ፊጥር የምናወጣው ከምግብ አንድ ሷዕ ነበር” ብለዋል።
ዘካተል ፊጥርን ከተገደበለት ጊዜ ማስቀደም ወይም ማቆየት እንደማይቻል ሁሉ የአወጣጡን አይነትም መቀየር አይቻልም። ዒባዳ ሁልጊዜ በአላህ የሚደነገግ እንጂ በአስተያየት ምንፈፅመው አይደለም። ማንኛዉም ሙስሊም ዒባዳው እንዳይበላሽበት ሊጠነቀቅ ይገባዋል። በገንዘብ መተመን በቀደምት ሰለፎች አልተፈፀመም። ከጥቂቶች በቀር አብዛኞቹ የኢስላም ሊቃዉንት በገንዘብ ማዉጣትን ይቃወማሉ። አል-ኢማም ማሊክ፣ አል-ኢማም አሻፊዒይ እና አል-ኢማም አህመድ ይህ መዝሀባቸው ነው። ስለዚህም በተባለው መልኩ በእህል ያወጣ ሰው በሁሉም ስምምነት ትክክለኛ ዒባዳ ሰርቷል።
√ ዘካተል ፊጥርን ወደ ሌላ ቦታ መላክ፤
እያንዳንዱ ሙስሊም በጾመበት ቦታ ዘካተል ፊጥርን ማዉጣቱ ቢሆንም የሚያስፈልገው ነገር ግን ምግብ የሚቀበል ሚስኪን ሰው የሌለበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በቤተሰቦቻቸዉ ወይም ጓደኞቻቸው አማካኝነት ችግረኞች ወዳሉበት ቦታ መላክ ይችላሉ።
በጥቅሉ ማንኛዉም ሰው ኢባዳውን በኢልም ላይ የተመሰረተ በማድረግ ኢስላምን በሚገባ ለመተግበር መሞከር ይገባዋል።
تقبل الله الصّيام والقيام وجميع الطّاعات
--
"አላህ መልካም የሻለትን (ሰው) ዲኑን ያስገነዝበዋል" ቡኻሪና ሙስሊም
🌙
የጎዳና ኢፍጣር
🌙
===============
🖌
በኢልያስ አሕመድ
በቅድሚያ ይህን ፕሮግራም ለማሰናዳት በቅንነት የሚለፉ ግለሰቦችና ድርጅቶችን አላህ የኒያቸውን እንዲሰጣቸው እንለምናለን፤ ከዚህ በታች ያለው አጭር ፅሑፍ የልፋታቸው መሰረት የተስተካከለ እንዲሆን ታስቦ በተቆርቋሪነት የተከተበ ነው።
››››› ‹‹‹‹‹
በህብረት ማፍጠር ሁለት አይነት አፈፃፀሞች ሊኖሩት ይችላል፦
1ኛ/
ለማፍጠር መሰባሰቡን ዋና ኢላማ ሳያደርጉ በተወሰኑ አጋጣሚዎች በህብረት ማፍጠር ሲሆን ይህም እንደማይወገዝ ግልፅ ነው።
ለምሳሌ፦ ለሰላት ወደ መስጂድ የመጣውን ስብስብ ወይም ድሆችን በአንድ ቦታ ለማስፈጠር የሚኖረው መሰባብሰብ ተቃውሞ ሊነሳበት አይችልም። ዘመድና ጓደኛን ጠርቶ በጋራ ማፍጠርም እንደተራ ግብዣ ሊታይ ይችላል። ፆመኛን ማስፈጠርን አስመልክቶ የተወራውን ምንዳ ለማግኘት ከታሰበ ደግሞ እንደ እሳቤው የተወደደ ሊሆን ይችላል።
ብዙ ዑለማዎች የፈቀዱትም በዚህኛው ምድብ የሚካተተውን ነው።
2ኛው/
ለኢፍጣር መሰባሰቡ ራሱ እንደ ዋና ግብ ታልሞና ይህንንም በሚያሳብቁ ተግባራት ታጅቦ በስፋት የሚተገበር አፈፃፀም ሲሆን ይህ የቢድዓ መገለጫን ሊላበስ ይችላል።
በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለመደው የጎዳና ኢፍጣር ይህንን ይዘት እንደተላበሰ ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል፦
👉
እንደ በዓላት የሚጠበቅ ህዝባዊ ኩነት መሆኑ፣ (Grand Iftar 1, 2 እየተባለ ዘንድሮ 4ኛው ላይ ደርሰናል!)
👉
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበድር ዘመቻ የተካሄደበት የረመዳን 17ኛው እለት ለዚህ አመታዊ መሰባሰቢያ እንዲሆን በተደጋጋሚ መመረጡ፣
👉
ሰዎች በነቂስ ወጥተው እንዲታደሙ ሰፊ ጥሪ መደረጉ፣
👉
በታዳሚያን ብዛት ከሌሎች አገራት ጋር ፉክክር ውስጥ የተገባበት መሆኑ፣
እና ሌሎች አባሪ ሂደቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ።
የነዚህ ሂደቶች ስብስብ ተግባሩን ራሱን የቻለ አዲስ የሙስሊሞች ይፋዊ ምልክት (ሺዓር) እያደረገው ነው።
📌
ታላቁ ኢማም
#ኢብኑ_ተይሚያህ
በዲን ውስጥ ስለሚጨመሩ የፈጠራ በዓላት በሚያብራሩበት አውድ ስለ በዓላት ምንነት ሲያስረዱ የሚከተለውን ይላሉ፦
«
“ዒድ” (በዓል) በተለመደ መልኩ ለሚደጋገም ሁሉን አቀፍ መሰባሰብ የሚሰጥ ስያሜ
ሲሆን በየአመቱ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ (በውስን ቀናት) የሚመላለስ ነው።
በዓል የተወሰኑ ነገሮችን አቅፎ ይይዛል፤ ከነሱ መካከል፦
እንደ ዒድ አል-ፊጥር እና እንደ ጁሙዓ የሚመላለስ ቀን፣ (በቀኑ) መሰባሰብ፣ ይህን ተከትለው የሚመጡ አምልኳዊ ወይም ልማዳዊ ተግባራት ይገኛሉ።
በዓል በውስን ቦታ የተገደበ ሊሆን ይችላል፤ ያልተገደበም ሊሆን ይችላል፤
እነዚህ ነገሮች ሁሉ (በነጠላ) ዒድ ሊሰኙ ይችላሉ....
“ዒድ” የሚለው ቃል ለእለቱና በውስጡ ላለው ተግባር ጥምረት የሚሰጥ ስም ሊሆን ይችላል፤ ይህም አብዛኛው (አጠቃቀሙ) ነው።»
[“
ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም
” (1/496 – 497)]
📌
በሌላ ቦታም እንዲህ ብለዋል፦
«ከተደነገጉት መሰባሰቦች ውጪ ሳምንታት፣ ወራት፣ ወይም አመታት በተደጋገሙ ቁጥር የሚደጋገም መሰባብሰብን በቋሚነት መያዝ ለአምስቱ ሰላቶች፣ ለጁሙዓ፣ ለሁለቱ ዒዶችና ለሐጅ ከመሰባብሰብ ጋር ይመሳሰላል፤
ፈጠራና አዲስ ተግባር ማለት ይህ ነው
!))
[“
ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም
” (2/140)]
📌
አለፍ ብለውም እንዲህ ይላሉ፦
«ከነዚህ (ከተደነገጉት) መሰባሰቦች ባሻገር የሚለመድ ተጨማሪ መሰባሰብ ከተጀመረ አላህ ከደነገገውና ካፀደቀው ፈለግ ጋር የሚመሳሰል ይሆናል …. -
ለብቻው የሆነ ግለሰብ ወይም ውስን ስብስቦች አንዳንዴ ከሚሰሩት በተለየ መልኩ!
))
[“
ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም
” (2/144)]
ይህ ማብራሪያ ሰዎች በየውስን ጊዜ በታወቀ ቀጠሮ የሚፈፅሙት ህዝባዊ ስብስብ እንደ በዓል ባይታቀድ እንኳ በዓላዊ ይዘትን እንደሚላበስ ያሳያል።
አንድ ነገር በጥቅሉ የሚፈቀድ፣ ብሎም የሚደነገግ ከመሆኑ ጋር በአፈፃፀሙ ረገድ የሚኖሩ ተጓዳኝ ነገሮች ብይኑ እንዲቀየር ሊያደርጉ ይችላሉ።
📌
ታዋቂው ዓሊም
#ኢብኑ_ደቂቅ_አል_ዒድ
አንዳንድ ሸሪዓዊ አፈፃፀሞችን ለመተግበር በደካማ የሐዲሥ ዘገባ ላይ ስለመመርኮዝ የሚነሳውን ውዝግብ አስመልክቶ እንዲህ ይላሉ፦
«የ“መውዱዕ” (የተቀነባበረ የውሸት ሐዲሥ) ክልል ውስጥ ያልገባ ደዒፍ (ደካማ) ከሆነ
በዲን ላይ አዲስ ይፋዊ ምልክት “ሺዓር” የሚፈጥር ከሆነ ይከለከላል
፤ ካልሆነ ደግሞ ምልከታ የሚቸረው ይሆናል...» [“
ኢሕካሙ’ል-አሕካም
” (1/501)]
👉
አንድን ተግባር እንደ “ሺዓር” ከሚያስቆጥሩት የአፈፃፀም ሂደቶች መካከል ሰዎች ተጠራርተው የሚሰባሰቡበት ኩነት መሆኑ ነው
፤
በተለይ እንደ ዒድ ሰላት በጎዳና/በአደባባይ ላይ የሚተገበር ከሆነ!
ይህን የሚያብራራ አንድ ምሳሌ እንጥቀስ፦
ሰዎች በተሰባሰቡበት አጋጣሚ አንዳንዴ ዱዓ ማድረግ የሚቻል ከመሆኑ ጋር ይህን በህብረት ለመፈፀም መጠራራትን ብዙ የኢስላም ሊቃውንት አይደግፉም።
📌
#አል_ኢማም_አሕመድ
እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦ «ሰዎች ተሰባስበው አላህን መለመናቸውና እጃቸውንም ማንሳታቸው ይጠላል?»
እርሳቸውም፦
«مَا أَكْرَهُهُ لِلْإِخْوَانِ إذَا لَمْ يَجْتَمِعُوا عَلَى عَمْدٍ إلَّا أَنْ يَكْثُرُوا»
= «
ሆን ብለው ካልተሰባሰቡ
ለ(ዲን) ወንድማማቾች አልጠላውም –
ካልበዙ በስተቀር
!»
📌
#አል_ኢማም_ኢስሓቅ
ኢብኑ ራሀወይህ ሲጠየቁም ተመሳሳይ መልስ ሰጥተዋል።
«ካልበዙ በስተቀር» ሲሉ ልማድ በማድረግ እስካልተበራከቱ ድረስ ማለታቸው እንደሆነ ጠያቂው (ኢስሓቅ ኢብኑ መንሱር) ተናግረዋል!
[“
መሳኢሉ’ል-ኢማሚ አሕመድ ወኢስሓቅ
” (9/4879)፣ “
ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም
” (2/140)]፣
“
አል-ኣዳብ አሽ-ሸርዒይ-ያህ
” ሊ’ብኒ ሙፍሊሕ (2/103)]
👉
ስለሆነም ነገሩ ከዚህ በላይ ሳያድግ መግታቱ አስፈላጊ ነው።
ይህ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ የአፈፃፀም ግድፈቶችን ከግምት ሳናስገባ የምንደርስበት መደምደሚያ ሲሆን፤ ያለ በቂ ምክንያት መንገድ መዘጋጋት፣ አግባብ ያልሆነ የወንድና የሴት መቀላቀል፣ የሴቶች ምስል በሚዲያ የሚሰራጭበት ቀረፃ፣ ሴቶች በምሽት መንገላታታቸው፣ በሙዚቃ መሳሪያ የታጀበ "ነሺዳ"፣ የምግብ ብክነት እና መሰል ጥፋቶች የሚታከሉበት ከሆነ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል።
አዎን! ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት ሞራላዊ ጥቅምን አስገኝቶ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን በውስጡ ከላይ የጠቆምነውን አመዛኝ ጉዳት ማካተቱ ለመታቀብ በቂ እንደሆነ አስባለሁ።
አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው።
ረመዳን 15/1445
__
__
@ustazilyas
📣
ሺዓና ህፀፆቹ 1‐4
🎙
በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
ስለ ሺዓ አንጃ ቀደም ያለ የሸይኽ ኢልያስ ትምህርት
የሺዓ ፊርቃ 1
https://t.me/yeilyaswedaje/368
የሺዓ ፊርቃ 2
https://t.me/yeilyaswedaje/370
የሺዓ ፊርቃ 3
https://t.me/yeilyaswedaje/371
የሺዓ ፊርቃ 4
https://t.me/yeilyaswedaje/372