
የሑሴን ሙንጭርጭሪቶች ✍📲👌👍
የደጋጎች ግሩም ስንቅ
✍
በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ
በአላህ መንገድ … ለኢስላምና ለሙስሊሞች ለሚደረግ ማንኛውም ትግልና ምድርን (ከፈሳድ) ለማስተካከል የሚውል ወጪ ፤ ለተቸገሩ ሰዎች ከምንሰጠው ሰደቃ የሚለይበትና የሚበልጥበትን መሰረታዊ ተጨባጮችን ብዙዎቻችን ገና የተረዳን አይመስልም ።
ከማብላትና ከማጠጣት ባሻገር ከእውቀት ጀምሮ ማህበረሰቡ ላይ ሊሰሩ ስለሚገባቸው ስር ነቀል ስራዎችና ማበልፀጊያዎች የሚወጡ ወጪዎች እጥፍ ድርብና ዘውታሪ ምንዳ አላቸው ።
مَّثَلُ الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ كَمَثَلِ حَبَّةٍ أَنبَتَتْ سَبْعَ سَنَابِلَ فِي كُلِّ سُنبُلَةٍ مِّائَةُ حَبَّةٍ ۗ وَاللَّهُ يُضَاعِفُ لِمَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ
{የእነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ሰዎች (ልግስና) ምሳሌ ፡· በየዘለላው ሁሉ መቶ ቅንጣት ያለባቸውን ሰባት ዘለላዎች እንደ አበቀለች አንዲት ቅንጣት ብጤ ነው፡፡ አላህም ለሚሻው ሰው (ከዚህ በላይ) ያነባብራል፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው ።} (አልበቀራህ 261)
… … …
ይህንኛውን ወጪ ነው … ተበልቶ ፣ ተጠጥቶና ተለብሶ ከሚያልቀው ወጪ በተለየ "ኢንቨስትመንት" (መዋዕለ ንዋይ) የምንለው ። ይህም ስያሜ በግለሰብም ሆነ በማህበረሰብ ደረጃ ወደፊት በተለያየ ጥቅማ ጥቅም ብዙ ለማትረፍ አስቀድመን የምናወጣቸውን ወጪዎች ይመለከታል ።
وَأَنفِقُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَلَا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى التَّهْلُكَةِ ۛ وَأَحْسِنُوا ۛ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ
{በአላህም መንገድ ለግሱ፡፡ በእጆቻችሁም (ነፍሶቻችሁን) ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፤ አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና ።} አል በቀራህ 195
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا هَلْ أَدُلُّكُمْ عَلَىٰ تِجَارَةٍ تُنجِيكُم مِّنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَتُجَاهِدُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ بِأَمْوَالِكُمْ وَأَنفُسِكُمْ ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ
{«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከአሳማሚ ቅጣት የምታድናችሁ የኾነችን ንግድ ላመላክታችሁን?» (በላቸው)፡፡ (እርሷም) በአላህና በመልክተኛው ታምናላችሁ፣ በአላህ መንገድም በገንዘቦቻችሁ በነፍሶቻችሁም ትታገላላችሁ፣ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ የተሻለ ነው ።} (አ’ሰፍ 10ና11)
… … …
የእውቀት መንገድ ፡ የጀነት መንገድ ነው ፣ የጀነት መንገድ ደግሞ “ሰቢሉላህ” ነው ። እናም በአላህ መንገድ ከሚደረጉ ወጪዎች መካከል አንዱና ዋናው እውቀትንና መንገዶቹን ለማሳለጥ የሚወጡ ወጪዎች ናቸው ።
هَا أَنتُمْ هَٰؤُلَاءِ تُدْعَوْنَ لِتُنفِقُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ فَمِنكُم مَّن يَبْخَلُ ۖ وَمَن يَبْخَلْ فَإِنَّمَا يَبْخَلُ عَن نَّفْسِهِ ۚ وَاللَّهُ الْغَنِيُّ وَأَنتُمُ الْفُقَرَاءُ ۚ وَإِن تَتَوَلَّوْا يَسْتَبْدِلْ قَوْمًا غَيْرَكُمْ ثُمَّ لَا يَكُونُوا أَمْثَالَكُم
{ንቁ! እናንተ እነዚያ በአላህ መንገድ ትለግሱ ዘንድ የምትጥጠሩ ናችሁ፡፡ ከእናንተም ውስጥ የሚሰስት ሰው አ’ለ ፡፡ የሚሰስትም ሰው የሚሰስተው በራሱ ላይ ብቻ ነው፡፡ አላህም ከበርቴ ነው፡፡ እናንተም ድኾች ናችሁ፡፡ ብትሸሹም ሌሎችን ሕዝቦች ይለውጣል፡፡ ከዚያም (ባለመታዘዝ) ብጤዎቻችሁ አይኾኑም፡፡} (ሙሐመድ 38)
ۗ وَالَّذِينَ يَكْنِزُونَ الذَّهَبَ وَالْفِضَّةَ وَلَا يُنفِقُونَهَا فِي سَبِيلِ اللَّهِ فَبَشِّرْهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ
{እነዚያንም ወርቅንና ብርን የሚያደልቡትን በአላህም መንገድ ላይ የማያወጧትን በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው።} (አ’ተውባህ 34)
እነሆ በአላህ መንገድ ላይ (ለእውቀት) ወጪ ማድረግን ከፈለጉ ፡ ከታች የተያያዘውን ሊንክ በመጫን የፕሮጀክቱ ማስተባበሪያ ግሩፕ ተቀላቅለው የልብዎትን ያድርሱ ።
https://t.me/mirathislamicorganization
ፅኑ ሀሜተኛ
✍
በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ
በቅድሚያ "ሐሜት ልተው ነው ።" ስላቹ ያመናችሁኝና "እኔም… " በሚል የተጋራችሁኝ ሷሒቦቼን ሳላመሰግን አላልፍም ። ሲቀጥል"ሐሜት ልተው ነው" እንጂ "ሐሜት ተውኩኝ" አላልኩም ፤ እየተናበብን ። በኋላ ሳማ ፣ ስቦጭቅና ስዘለዝል አጋጥምያቹ "አዪ … ከመቼው? " "ወሬ ብቻ! … ቱሪናፉ" ምናምን እንዳትሉና በመጥፎ ጠርጥራችሁኝ እንዳታሙኝ ነው ። (ብታሙኝኮ አጅራቹ ትራንስፈር እንደሚደረግልኝ አልዘነጋሁትም ፤ በእናንተ ጉዳት መጠቀሙን ስላልፈለኩት እንጂ ።)
ብቻ… በ"ልተው ነው" እና "በተወኩኝ" መካከል ያለውን ርቀትና ዳገት የሚያውቀውም ነው የማያውቀው ። ሱስ "ልተው ነው" ስለተባለ ብቻ ይተዋል እንዴ?! … እና ሐሜት ሱስ አይደለም ያለው ማነው? … እናሲዝ ሱስ ነው?!
ካላመናችሁኝ… ፈትሹኝ!
ሐሜት ሱስ ደረጃ እንደሚደርስ ያወቅኩት በማንም ሳይሆን በእኔው በራሴ ነው ። እንደ ሰሞኑን ቁር’ጥና ጭ’ክን አድርጌ ባልወስንበትም በተደጋጋሚ ስለመተው አስብ ነበር ። እናም ሀሳቤን የፈጠነ ከመርሳቴና የፀና ልምድ ሆኖብኝ ካለመተዌ በዘለለ ጭራሽ ይብስብኛል ።
ካስተዋላቹ … "በቅርቡ እተዋለሁ" ፣ "እቺን ብቻ" ፣ "የዛሬን ብቻ" ብለን የምንሰራውን ሱስ ፤ የመለያያና የመጨረሻ በሚል እስኪሰለቸን ድረስ ነው የሌለ የምንበረታበት ። እናም እንዳልነው መተው ካልቻልን የባሰ ሆነን እናርፋታለን ።
… … … … … … …
ሐሜት ተራ (መደበኛ) ወንጀል ብቻ ሆኖ የምንሰራበት ወቅትማ ድሮ ቀረ ፤ "ለማማት አይደለም…" "አላህ ዐውፍ ይበለኝ እንጂ… "አማህ አትበለኝ እንጂ… " እያልን በምናማበት ድሮአችን ላይ (ቀረ) ። ጀምረን በመሀል በምናቋርጥበት ፣ ጨርሰን እንኳ በኢስቲግፋር በምንዘጋበት ፣ ከሌሎች ራቅ ብለን በምናንሾካሽክበት የመሳቀቂያ ዘመን ላይ ነበር መደበኛ ወንጀል የነበረው ።
ታድያ ያ ሁሉ ቀርቶ… የለመደች አጫሽ ሴሽዋን ሐላል እያቦነነች ራን ራን እንደምትለው ፤ "ሰው አየኝ አላየኝ ፣ ሰማኝ አልሰማኝ ፣ አረ ይታዘቡኛል ፣ ኋላ ምን ይሉኛል" ሳንል እያማን ሱስ ደረጃ አልደረሰብንም ? ለመተው አስበን አልፈታ እያለንም ሱስ በመሆኑ ላይ አንተማመንም?
ጥፍጥናና እርካታ ያላቸውን ነገሮች በተደጋጋሚ ስንጠቀም በሱሳቸው የመጠቃት እድላችን ከፍተኛ እንደሆነ የታወቀ ነው ። ታድያ የሰው ስጋ መብላት ቀላል ነው እንዴ የሚጥመን?! የሚጠሉትን ሰው ለማሳነስ ልክ ልኩን ለሌሎች መንገርም እርክት እንደሚያደርግ የእኔን ያህል ባይሆንም ታውቁታላቹ ።
እና ሰው ስናማ… ሰውነታችን ውስጥ ከመጠን ያለፈ ዶፓሚን አይመነጭም ነው የምትሉኝ? እና "አምጣ, አምጣ"ው ከምን መጥቶ ነው ? አረ እመኑ! (ትድናላቹ)
ይህን ሁሉ አተታ የዘበዘብኩት በነሻጣና ቁጭት መፈክር አሰምተን ብቻ ከውሳኔ ወደ ኋላ ከሚጠበቅብን የቤት ሥራ እንዳንዘናጋ ነው ። እንዲሁም በሱሳችን ተሸንፈን በድጋሚ ስናማ ውሳኔና የመተው አቅማችንን ተጠራጥረን ተስፋ እንዳንቆርጥ ነው ።
ማገገሚያውን በሌላ ሙንጭርጭሪት እንመለስበታለን… በረቡና ፈቃድ!
መዐ’ሰላም!
እየተቃረብን! ↴
☘
☘
☘
☘
☘
☘
☘
https://t.me/yehussenmun
ህይወት ይቀጥላል!
✍
በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ
ረመዷንን በመጨረሳችን ለአላህ ምስጋና የተገባው ነው ። ("አልሐምዱሊላ"ው ረመዷን በማለቁ ይሁን ጨርሶ ስላፆመን ይሁን እንደየምርጫችን እናደርሳለን ።)
ለኑሮ እንቅስቃሴ ጉልበት ለማግኘት ምግብ በልተን ስንጨርስ … ህይወት ይቀጥላል ።
፣ የተሻለ አቅም ለመገንባት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርገን ስንጨርስም … ህይወት ይቀጥላል ።
፣ ተምረን ተስተምረን ስንመረቅም … ህይወት ይቀጥላል ።
፣ ልክ እንደዚሁ … በረመዷን የተሻለ ምንዳ ለማግኘትና የተሻለ ማንነት ለመገንባት ሰግደን ፣ ፆመን ፣ ቀርተንና ሰድቀን ወሩ ሲያልቅ … ህይወት ይቀጥላል ።
እነዚህ ሁሉ አጋጣሚና ስራዎች የህይወት መጀመሪያና መጨረሻ ሳይሆን ስንቅ መሰብሰቢያዎች ናቸው ።
"አላህ … ከረመዷንም በኋላ አለ።" ምናምን አይነት የተሰለቹ ነጥቦችን ማንሳት አልፈልግም ። በቃ ግን አንተ በህይወት ከቀጠልክ ለምን አርፈህ አትኖርም ?! ለምን መልካምነትህና የተሻለ ማንነትህን ከረመዷን መግባትና መውጣት ጋር የግድ አድርገህ ታስተሳስረዋለህ ?
ከረመዷን ውጭ መልካምነትን ችላ ሊልና በራሱ ላይ የኸይር አላስ ሊሆን "ሲገባ እገባለሁ ፣ ሲወጣ እወጣለሁ" የሚል ፋራ አንተን አየሁ ።
ረመዷን አንዱና ምርጡ የህይወት አጋጣሚ እንጂ መጀመሪያና መጨረሻው ካልሆነ ከሚቀጥለው ህይወት ጋር መኖር ቀጥል እንጂ ከሚያልቀው ጋር አልቀህ አትቁም ። በረመዷን አስፈላጊ የሆነ ነገር ሁሉ መጠኑ ይለያያል እንጂ ሁሌም ያስፈልጋል ። በረመዷን ልክ ያልሆነ ነገር ሁሉ አወጋገዙ ቢለያይም ያው ልክ ያልሆነ ነገር ነው ። እናም በቀጠለው ህይወትህ አስፈላጊውን በማድረግ ልክ ያልሆነውን በመተው መኖር ቀጥልበት ።
ለውጥም በረመዷን ተጀምሮ በረመዷን ላያልቅ ይችላል ። ከለውጥ አንፃር ከረመዷን የምንጠቀመው አንዱ ጥቅምም ህይወታችንን ለመለወጥ ማሰብና መነቃቃት ነው ። በዚህ ልክ የተነቃቃ ሰው ደግሞ ከረመዷን በኋላ የሚጠብቁት ብዙ የቤት ስራዎች መኖራቸውን ይረዳል እንጂ በልዩ አጋጣሚ የወጣውን ደረጃ ድጌ ዝቅ አይልበትም ።
መኖር ይቀጥላል !
እየሄድክ !
🏃♂➡️
እየተቃረብን! ↴
☘
☘
☘
☘
☘
☘
☘
https://t.me/yehussenmun
ሐሜት ልተው ነው!
✍
በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ
ካደግኩኝ በኋላ ከልጅነቴ ፍፁም በተለየ መልኩ ሰው ማማት ለምጃለሁ ፤ በጣም ። እናም በፊት (በልጅነቴ) የሀሜትን ክብደት ያለ መፈቀጃ አጋጣሚዎቹ ተረድቼ አላስነካ የምልበት ዘመን በሀሳቤ እየተመላለሰ ያስቀናኛል ። "ወደ ከንቱነቴ ነው ያደኩት" "ምኑን አ’ደኩት? አነስኩት እንጂ!" አላልኳችሁም ነበር ፤ "ልጅነቴ ናፈቀኝ ተመልሶ… " በሚለው ሙንጭርጭሪታችን ላይ ።
በተለይ "ኡስታዝ" ከሆንኩኝ በኋላ ፣ "ዳዒ" ከተባልኩ በኋላ ፣ ጭራሽ ደግሞ ሐሜት የሚቻልባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ ካወቅኩኝ በኋላማ ማን ይቻለኝ ?! በአይነት በአይነቱ እየመደብኩ ተንደላቅቄ ነው የማማው ። ከእኔ መ’ሸወድ በተጨማሪ "ኡስታዝኮ ለማማት ብሎ አይደለም… " እየተባለ ጆሮ ስለሚሰጠኝ ሳልሳቀቅ ነው የማማት አምሮቴን የምወጣው ።
ነገር ግን አሁን ላይ ደርሼ ፤ ድንገት በሚመስል መልኩ ሀሜት ለማቆም ወሰንኩ ። …በቃ ቆረጥኩ!
ታድያ … "ሐሜት ለመተው ምን አነሳሳህ?" አትሉኝም?
መረረኛ በቃ … አንገሸገሸኝ!
"ምኑ?"
እህ…
ስለ ሌሎች ችግር "ለማማት አይደለም! " እያልን ስንዘለጥናቸው እንከርምና ፣ ለዲን በመከላከልና በመማማር ስም ስንቦጫጭቃቸው እንቆይና የእርስ በእርሱ ላይ ስንደርስ ባላየ እንተላለፋለን ። ድንገት ደግሞ የአንዳችን ቅሬታ ከፍ ብሎ በሆነ አጋጣሚ የሌላችንን ችግር ለመጠቆም ከሞከረ በጣም ነው የሚያስቀይመን ፤ በጣም ።
ሆ
…
ወዳጆቼ ስለሌሎች ክፍተትና ስህተት ሲነግሩኝ እንጂ "አንተም… " ብለው የሚመክሩኝ ምንም አይጥመኝም ። "አንተኮ… " "እውቀትህኮ… " "ሀሳብኮ… " "ፀባይኮ…" "ውበትሽኮ…" ብለው እንዲያወድሱኝ እንጂ ለጥቆማ የሚሆን ክፍተት የለኝም ።
ለወዳጆቻችን ስለማናስነካ … ስለ ክፍተቶቻችን የማውራት እድል የሚያገኙት ተቃራኒዎቻችንና ጠላቶቻችን ናቸው ። ለዚያም ነው በወዳጅነት ወቅት ያልተመካከርናቸው ክፍተቶች የተጣላን ሰሞን "ያው በፊትምኮ ችለነው ፣ ታግሰነው ፣ ያስተካክላል ብለን አልፈነው ነው እንጂ… " በሚል እየተመዘዙ የዐይብ መግለጫ ተደርገው የሚዘረዘሩት ። ("የዐብይ መግለጫ" ብላቹ ያነበባቹ ሷሒቦቼ… ተውኣ!)
እናም በሚያሳዝን ተጨባጫችን ፡ እኛ ስለ ሌሎች እንጂ ስለኛ ክፍተት ለማውራትና እየተራረምን ለመሻሻል አልታደልንም ።
ከእናትና አባቴ ጋር ስለ ሰፈር ሰዎች እንጂ ስለራሳቸው ክፍተት በለሰለሰ መልኩ እንኳ ካወራው ፤ ወላጅን ካለማክበር ወስደውት ይቀየሙኛል ።
፣ ከወንድሞቼ ጋር ስለ ዘመድና ጓደኞቻችን እንጂ ስለ ራሳችን ካነሳን ለብዙ ጊዜ ሊያኮራርፈን ይችላል ።
፣ ከጎደኞቼ ጋር ስለሩቅ ጓደኞቻችን መቦጨቁ እንጂ እርስ በእርስ መተራረሙ ያደባብረናል ።
፣ ከዳዕዋ ጀመዐዎቼ ጋር ስለሌሎች ኢስላማዊ ድርጅቶችና ኡስታዞች ስናወራ እንጂ ፤ ስንመካከር ለመለያየት ጫፍ ተንደርድረን በብዙ መለማመጫ ነው የምንመለሰው ።
ደግሞ የብሽቅነቴ…
ከአንዱ ጀለሴ ጋር ፒስ በሆንኩበት ወቅት ሌላኛው ካስቀየመኝ የማማው አስተማም ፤ ነገ ከዚህኛው ጋር ተቀያይሜ ከዛኛው ጋር ፒስ ስፈጥር የማማው አይመስልምኮ ። "ሞራልህ… " ይላሉ አንዳንድ (ቀበጣቀበጥ) እንስቶች ፤ የማያስችል ነገር ያደረገ ለመሰላቸው ሰው ።
ከተማሪዎቼ መሀከል በወቅቱ ከሚያሸረግዱልኝ ጋር ሆኜ እኔን አልሰማና አልታዘዝ ያሉኝን ሳማ ሳማ እቆይና ፤ ሁኔታው ሲገላበጥም ተገልብጬ ማማቴን እቀጥላለሁ ።… ሞራሌ!
በቃ ራሴን ጥልት አደረኩት! እንዲህ አይነት ስብእና ያለው ሰው ደግሞ ምኑ አባቱ ይወደዳል?
… … … … … … …
ለሀሜት እንጂ ለምክክርና መወቃቀስ የማንመች ብሽቅ ትውልድ ሆነን የለ እንዴ ጎበዝ ?!
አነጋገራቸውኮ ነው እንጂ ክፍተታችን እንዲነገረንኮ እንፈልጋለንኣ?! … ፎጋሪ ሁላ! ሌላው ከነ ስድቡና ውርጅብኙ ሲታማ ጭጭ ብለን የእኛ ክፍተት ላይ ሲደረስ ነው የአነጋገር አጀንዳ የምንከፍተው ?!
እንደው ከልክ በላይ ደንቁረን አልገባ አለን እንጂ ፤ ሌሎች በስርኣት ከሚታሙልን ይልቅ እኛ በስድብና ቁጣ ብንመከር ይሻለን ነበር ። ስለአነጋገር መጨነቅ የነበረብንም ሌሎች በአግባቡ (በሚቻልበት ጠባብ ሁኔታ) ሲታሙ ነበር ።
እና ማለት ነው…
ስለ ሌሎች ክፍተት ማውራት ከወንጀልነቱ ባሻገር እኛን ፍፁም አድርገን እንድናይ ያደረገን ሲመስለኝ ተጠየፍኩት ። ድሮም ከንቱ ነበርኩኝ ፣ የከንቱ ከንቱ የሚያደርገኝ ሸቃባ መሆኑ ሲገባኝ ወሰንኩበት ። "አታውቀውኝም አላውቅህም ፣ አትፈልገኝ አልፈልግህም ፣ እንዳትደርስብኝ አልደርስብህም ፣… " ብዬ ኢግኖር ገጨሁት ።
እናም ወዳጅ ተብዬ በጠቅላላ … ከአሁን በኋላ ተናግርያለሁ ፡· ስለ እኔ ወይም ስለ አንተ ክፍተት ለመጠቋቀም ካልሆነ በቀር እንደለመድነው ለማማት አጠገቤ ዝር, ድርሽ እንዳትል (ከሚያማኝ በላይ የሚያስተማማኝ ሊጎዳኝ እንደጨከነብኝ ለወትሮ ሳይገባኝ ከርሜ) ። ድንገት ልምዱ አሸንፎን ከጀመርነውም ለማቆም ብታግዘኝ አከብርሀለው እንጂ አልቀየምህም ፤ ውለተኛዬ ነህና።
ኮሚቴው
📜
🫥
(ማህተም)
መዐ’ሰላም!
እየተቃረብን! ↴
☘
☘
☘
☘
☘
☘
☘
https://t.me/yehussenmun
የአመለካከት ግንባታ
(ረመዷንና ለውጥ #17)
✍
በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ
7, መወያየት
ሀሳብን በማስተማርም ሆነ በመወያየት ለሌሎች ማጋራት ካሉት ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ውስጥ አጅር አንዱ ሲሆን ፤ የተግባቦት ክህሎትን ማሳደግ ፣ ሀሳብን ማስገምገም ፣ አመለካከትን ማፅናትና ሌሎችም እንደተጨማሪ ይጠቀሳሉ ።
የተለያዩ የንጋትና የምሽት ፣ የመግባትና የመውጣት ፣ የመብላትና የመጠጣት ፣… አዝካሮች አንዱ ጥቅም እምነትን በአፍ እየደጋገሙ በልብ ማፅናት እንደሆነው ሁሉ ፤ ሀሳብና አመለካከትም በንግግር ይፀናሉ ።
እንዲሁም በተሳሳታ መልኩ መረዳታችንን ልብ ያላልናቸውን ነጥቦች ለማረም እድል ከሚሰጡን አጋጣሚዎች መካከል አንዱና ትልቁ ነው ።
8, መተግበር
መቼስ ከአመለካከት ግንባታ እንዲገኝ የሚጠበቅ ወሳኝ ነገር አለ ። እርሱም በገባንና በምንችለው ልክ መተግበር መሆኑ ጥርጥር አይገባውም ። ተግባር ግድ ከመሆኑ ባሻገር አመለካከታችንን ወደ ስራ በምናመጣበት ሂደት ውስጥ በመስማትና በማሰላሰል ያልተረዳናቸውን ነገሮች የማግኘት እድል ይኖረናል ።
እንዲሁም ያልተተገበረ አመለካከት ምንም እንኳ ቢሸመደድ ቀስ በቀስ የመደብዘዝ አደጋ ያጋጥመዋል ። በተጨማሪም ባወቁትና በተረዱት ልክ እንደሚችሉት አለመስራት ያለውን ሸሪዐዊ ተጠያቂነት እንደምናውቀው ነው ።
ሌላውና ከማንነት ግንባታችን ጋር በቀጥታ የሚያያዘው ነጥብ ፤ ተግባር የማንነታችን 1/2ኛ ነው ያልነውን ልማድ የምንሰራበት ብቸኛ እርምጃ ነው ። አንድን ያመንበትና የገነባነውን እውቀት ወይም ሀሳብ መተግበር ባለበት መልኩ ስንተገብረውና መደገም ባለበት መልኩ ስንደጋግመው ልማድ ከመሆን ምንም ቅሮት የለውም ።
9, ሂደቱን መደጋገም
በመሰረቱ ከላይ የጠቀስናቸውን ሂደቶች በሚገባ ተከትሎ የተጓዘ ሰው በአላህ ፈቃድ የተሻለ ማንነት የማይገነባበት ምንም ከልካይ የለውም ። ነገር ግን ይበልጥ የተሻለና የፀና ማንነት መገንባት የፈለገ ሰው ያለ መታከት ሂደቱን ይደጋግመዋል ።
የመስማት ፍላጎትና ንቃት ከምናውቀውና ማወቅ ከምንፈልገው ነገር አንፃር ስለሚቃኝ እዚህ ደርሰን ስንመለስ የሚኖረን አሰማም ከመጀመሪያው በተለየ መልኩ ንቃት ይኖረናል ። በመሆኑም አንዳንድ ነጥቦችን አስቀድመን ያልሰማናቸው ያህል ትኩረታችንንን ይስባሉ ።
በተለይ በጉዳዩ ላይ ከሌሎች የላቀ ለመሆንና ሌሎችንም እስከ ማገዝ ለመድረስ የሚሻ ሰው ከሌሎች በተለየ ሂደቱን መደጋገም ይኖርበታል ። ነገር ግን ሂደቱን በደገመ ቁጥር ስንጠቃቅሳቸው በነበረው ልክ ቅድመ ተከተሉን መጠበቅ ግድ አይለውም ። ብቻ ዋናው ነገር በእነዚህና በሌሎች ባልጠቀስኳቸው ተጨማሪና ዝርዝር ሂደቶች ላይ በምንችለው እየተጋን የተሻለ ማንነት ለመገንባት መጣራችን ነው ።
10, ተወኩልና ዱዐ
ስለ ተወኩልና ዱዐ ብዙ ስለተባለ እዚህ ቦታ ላይ ማብራራት ፅሁፉን ማርዘምና አንባቢንም ማሰልቸት እንዳይሆን በአንዲት ጥቆማ ብቻ እንብቃቃ ። ለተሻለ ማንነት ግንባት የምናደርገው ጥረት ስኬታማ የሚሆነው ሌሎች ሂደቶች ሁሉ ከነ እርዝራዣቸው በአንድ ሚዛን ሲሆኑና እነ ተወኩልና ዱዐ ደግሞ በሌላ ሚዛን ልካቸውን ሲያገኙ ነው ።
ወሏሁ አዕላ ወአዕለም!
(ረመዷንና ለውጥ #18 ሊቀጥል ይችላል)
ወ‘ሰላም!
እየተቃረብን! ↴
☘
☘
☘
☘
☘
☘
☘
https://t.me/yehussenmun
የአመለካከት ግንባታ
(ረመዷንና ለውጥ # 16)
✍
በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ
4, ማስታወሻ መያዝ
"በቃል ያለ ይረሳል ፣ በፅሁፍ ያለ ይታወሳል ።" እንደሚባለው ፤ ካደመጥናቸው ነገሮች መካከል አብዛሀኛውን ከጊዜ በኋላ እንዳንረሳና ድጋሚ ፣ ድጋሚም ማዳመጥ እንዳያስፈልገን የሚያደርግልን ትልቁ አጋዣችን ማስታወሻ መያዝ ነው ።
እንዲሁም ማስታወሻ መያዝ በስሚያችንና በእይታችን ካገኘናቸውና ከተረዳናቸው አጠቃላይ ሀሳቦች ውስጥ ደጋግመን በመመላለስ የእኛ አድርገን ልንሸመድዳቸው የሚገቡ ነጠብጣቦችን ግልፅ ያደርግልናል ።
እናም ማስታወሻ መያዝ… በማዳመጥና በመረዳት ⇉ እና ⇉ በመሸምደድና በማሰላሰል መካከል መኖሩ ግድ የሚል ድልድይ ነው ። ይህ ድልድይ ላይ ባለን ብልሀትና ንቃት ልክ ነው የቀጣዩ ሂደቶች ውጤት የሚወሰነው ።
5, መሸምደድ
ማስታወሻ ከመያዝ በላይ የሰማነውና የተረዳነውን ነገር በዘላቂነት የእኛ እንዲሆን ልናደርግ የምንችለው በመሸምደድ ነው ። የማስታወሻም መዳረሻነቱ ፡ ለመሸምደድ መምረጥና ማመቻቸቱ ላይ ነው ።
ከማስታወሻ መያዝ በኋላ ወደ ሽምደዳ ካልመጣን ፤ ማስታወሻችንን ባለ እውቀትና ባለ ሀሳብ አድርገን እኛ ግን ከመሀይምነታችን ብዙ ፈቀቅ አንልም ። ከጊዜ በኋላ የሚኖረን እውቀት በዛ ከተባለ በጥቅል ስሞች ብቻ የተገደበ ነው የሚሆነው ። ያንን ደግሞ ፕሮሰስ አድርጎ ወደ ጭብጥና ተግባር መለወጥ አዳጋች ነው ።
እናም ባደመጠውና ባወቀው መጠቀም የሚፈልግ ሰው በዋነኝነት ሊያደርጋቸው ከሚጠበቁ ጥረቶች መካከል አንዱ ጊዜና ቦታ ሰጥቶ መሸምደድ ነው ።
6, ማሰላሰል
እውቀትና ሀሳብን ማዳመጣችንም ሆነ መሸምደዳችን ሄዶ ሄዶ እኛን እና የእኛን ወደ ተሻለ ሁኔታ እንዲለውጡ በመሆኑ ፤ እስከ መሸምደድ ተጉዘን የእኛ ያደረግናቸውን እውቀትና ሀሳቦች ተመርኩዘን ኑሮና እንቅስቃሴያችንን ፣ ችግርና መፍትሄዎቻችንን ፣ አጀማመርና እቅዳችንን ሁሉ ጊዜና ቦታ ሰጥተን በጥሞና ማሰላሰል ግድ ይለናል ።
ያገኘነው እውቀትና ሀሳብ ሁሉ ልክ ሊሆን ስለማይችል ወይም ከእኛ ጋር (ለጊዜውም ቢሆን) ስለማይዛመድ ፤ የምንወስደውን ወስደን ፣ የምንጥለውን ጥለን ፣ የምናንጠለጥለውን አንጠልጥለን ለመሄድ ጥልቅ ፍተሻ የምናደርግበት ትክክለኛውም እርከን ይህ ነው ።
በንባብና ማድመጥ ወቅት የሚኖረን ድጋፍም ሆነ ቅሬታ በደንብ ተፈትሾ የተገኘ ሳይሆን አስቀድመን ከምናቀውቃቸውና ከለመድናቸው ሀሳቦች አንፃር የሚኖረን የመስማማት ወይም የመከላከል ስሜት ነው ።
እናም ብዙውቻችን በምናውቀው የማንጠቀመውና ለተጨማሪ እውቀትና ሀሳቦች ሊኖረን የሚገባውን ጉጉነትና ክፍትነት ያጣነው በጥሞና ለማሰላሰል የሚሆን ጊዜና ቦታ ፤ ከትምህርቱ ፣ ከስራው ፣ ከቤተሰብ ፣ ከጎደኛና ከሚዲያ … አልተርፍ ስላለንና ስለማንፈክር ነው ።
7, …
ይቀጥላል … (ቢኢዝኒላህ)
ወ’ሰላም!
እየተቃረብን! ↴
☘
☘
☘
☘
☘
☘
☘
https://t.me/yehussenmun
የአመለካከት ግንባታ
(ረመዷንና ለውጥ # 15)
✍
በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ
አመለካከት የእኛነታችን የዋናው ዋና ክፍል እንደሆነ ከተለያዩ ነገሮች አንፃር እየደጋገምን በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለማየት ሞክረናል ። እናም ይህንን ወሳኝ የማንነት ክፍልን እንዴት መገንባት እንዳለብን ማወቅ አስፈላጊም ተፈላጊም ነው ።
1, ለማወቅ መፈለግ
ጉጉት የቀጣይ ሂደቶች ሁሉ መሰረትና ማስነሻ ነው ። የማወቅ ፍላጎት የሌለው ሰው ከቀጣይ ሂደቶች መካከል የተወሰኑት ሳያስበው ቢገጥሙት እንኳ ተገቢውን ቦታ ስለማይሰጣቸው በሚገባ ሊጠቀምባቸው አይችልም ።
ሊያዳምጠውና ሊያስብባቸው የሚገቡ እውቀትና ሀሳቦች ሲደርሱት ችላ ብሎ በለመዳቸው ወሬና ጨዋታዎች ይመሰጣል ።
2, ማዳመጥ
መ’ለወጥ የሚገባቸውን ነገሮች ሳንለውጥ ከአመት እስከ አመት ከነምናምናችን እንድንዝግ የሚያደርገን የብዙዎቻችን እንቅፋት ፡ በተገቢው መልኩ አለማዳመጥ ነው ።
ብዙ ነገር አናቅም ፣ ግን በሰአቱ የሚመጣልንንና የምናገኘውን ነገር እናውቃለን (እናስመስላለን) ። ማለትም በሁኔታችን እውቀትና ሀሳብ እኛ ዘንድ እስኪመጡ ድረስ "ጃሂል ነን" ብለን ለመተናነስ እንሞክራለን ። እውቀቶቹ ሲደርሱን ግን "እቺንማ አውቃታለሁ።" አይነት ነው ትወናችን ። እናም በአግባቡ ስለማናዳምጥ አይገባንም ፣ አንግባባምም ።
ቁርኣንም… አለማዳመጥ ፡ የጀሀነም ሰዎች አንዱ መገለጫ እንደሆነም ይነግረናል ።
وَقَالُوا لَوْ كُنَّا نَسْمَعُ أَوْ نَعْقِلُ مَا كُنَّا فِي أَصْحَابِ السَّعِيرِ
{«የምንሰማ ወይም የምናስብ በነበርንም ኖሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ውስጥ ባልኾን ነበር» ይላሉ ።} (አልሙልክ 10)
(ማዳመጥ ያልነው ስለተለመደ እንጂ ማንበብም ተመሳሳይ ነው ።)
3, መረዳት
መረዳት የምንለው ደግሞ በመስማት ወይም በማንበብ ያገኘነውን እውቀት ምንነትና ኑሮአዊ ትርጓሜውን ማግኘት ነው ። ሊተላለፍ የተፈለገውን መልእክት በልኩ መድረስና መጨበጥ ።
ነገር ግን ብዙ ጊዜ እንደሚስተዋለው … ቦታ ሰጥተን ያደመጥናቸውን ነገሮች ሁሉ በሚፈለገውና በሚጠበቀው ልክ ላንረዳው እንችላለን ። ወይ የተወሰነ ይከብዱንና ጨርሶ እንዳልገባን እንረዳለን ወይ ደግሞ በጣም ይከብደንና ገብቶናል ብለን እንሸወዳለን ። (ኢሄኔ ደግሞ ከምናጠፋው ጥፋቶች መካከል ወጥሮ መቃወምና ተቃውሞን ለመግለፅ መቸኮል ናቸው ።)
የዚህን ክፍል ግማሽ ወይም አብዛሀኛውን ሀላፊነት የሚወስዱት አስተማሪና አስረጂዎች ቢሆኑም ከአድማጭም የሚጠበቁ ለመረዳት መደረግ ያለባቸው ጥረቶች አሉ ። ከእነርሱም መካከል በዋነኝነት የሚጠቀሰው ፤ ደግሞ ማዳመጥ ወይም ማንበብ ነው ።
4,
…
ይቀጥላል … (ቢኢዝኒላህ)
ወ’ሰላም!
እየተቃረብን! ↴
☘
☘
☘
☘
☘
☘
☘
https://t.me/yehussenmun
የተቆሰቆሰ ስሜት
(ረመዷንና ለውጥ # 14)
✍
በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ
የአመለካከት ስራ መግራት ብቻ ሳይሆን መቆስቆስም ጭምር ነው ። የተቆሰቆሰውንም አውንታዊ / በጎ ስሜት መግራት ስለሚኖርበት ነው የአመለካከትን ስራ መግራት እንደሆነ የምንጠቅሰው ። አሉታዊ ስሜቶችም በአመለካከት ደረጃ ሊቆሰቆሱ እንደሚችሉ አውስተናል ።
ቸርነት ድርጊት ሲሆን ልማዱ የሆነ ሰው ቸር/ደግ ይባላል ። እናም ይህ ቸርነት ከጊዜያዊነቱና አፈፃፀሙ ላይ ማሟላት ከሚጠበቅብን ተጨማሪ ነገሮች አንፃር የምር ና ማስመመሰል ብለን እንከፍለዋለን ።
ድርጊት የሆነው ቸርነት መነሻ ስሜቱ እዝነት ነው ። እዝነት በአመለካከት ሲቆሰቆስና ሲገራ ቅንነት ይሆናል ፣ ቅነነት የወለደው ቸርነት ተደጋግሞ ልማድ ሲሆን ደግሞ ደግነት ይሆናል ።
ደግ ማንነትን ለመገንባት … የእዝነት ስሜታችንን ለመቆስቆስ ብቻውን ግን በቂ አይደለም ። ይህንን መነሻ ስሜት እንዳይቆሰቆስ የሚያደርጉ ሌሎች ስሜቶች በማዳፈኛነትም ሆነ በአመለካከት ደረጃ በመኖራቸው እነርሱንም መግራት ያስፈልጋል ። የመጀመሪያው ስግብግብነት ሲሆን ስስትና መቋጠር ተከታትለው ይመጣሉ ።
እናም በተፈጥሮ ከሌሎች ጋር በመልካም ለመኗኗር የተሰጠንን የእዝነት ስሜት ቆስቁሰንና ገርተን ቸር እንዳንሆን የሚያደርጉንን ስሜታዊ እንቅፋቶችን መግራት ስንችልና ስንቆጣጠራቸው ደግነትን እንገነባለን ። ያኔ ደግሞ በዱንያም በአኺራ የተሳካለትን የደስታ ህይወት እንኖራለን ።
"አላህ ለጋስ ነው ፤ ለጋስነትንም ይወዳል ፣ ቸር ነው ፤ ቸርነትንም ይወዳል ።" ይላሉ ረሱሉላህ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፤ ሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ (ረዲየሏሁ ዐንህ) አስተላልፈውት ቲርሚዚይ በዘገቡት ሐዲስ ላይ ።
ኢብኑ ዐባስም (ረዲየሏሁ ዐንህ) እንዲህ ይላሉ ፡· “የአላህ መልእክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)
ከሰዎች ሁሉ የበለጠ ቸር ነበሩ
። ይበልጥ ቸር የሚሆኑት ደግሞ በረመዷን ነበረ ፤ ጅብሪል (ዐለይሂ ሰላም) በሚገናኛቸው ጊዜ ። ቁርኣንን ያስተማምራቸው ነበር ። እናም የአላህ መልእክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከተላከች ንፋስ በላይ ለበጎ ነገር በጣም ቸር ነበሩ ። ” (ቡኻሪ እንደዘገቡት)
ሰለዋቱ ረቢ ወተስሊማቱሁ ዐለይሂ ዳኢመን ወኣበዳ!
ٌ ۚ وَمَن يُوقَ شُحَّ نَفْسِهِ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ
{የነፍሱንም ንፍገት የሚጠበቅ ሰው እነዚያ እነሱ ምኞታቸውን አግኚዎች (ስኬታማዎች)ናቸው፡፡} (አልሐሽር 9)
… … … … … … …
በጊዜያዊ ማስነሸጫና በአመለካከት የተቆሰቆሱ ስሜቶች እጅግ የተለያዩ ነገሮች ናቸው ። በሳይኮሎጂም ቢሆን ሞቲቬሽን ብዙዎቻችን ከምናውቀው በተለየ አይነተ ሥስት ነው ። እነርሱም ፡· ማስጀመር (activation) ፣ ወደግብ ማንቀሳቀስ (direction) ፣ ማስቀጠል (persistence) ናቸው ።
ከቁስቀሳው እስከ ማስቀጠሉ የዘለቀ ማስነሸጫና ማነቃቂያ ፤ ልማድን ስለሚወልድ ሁለቱ በጣምራ ማንነትን ይገነባሉ ። ይህንን በዋነኝነት የሚሰራው ደግሞ የአመለካከት ግንባታና አገነባቡ ነው ።
ወ’ሰላም!
እየተቃረብን! ↴
☘
☘
☘
☘
☘
☘
☘
https://t.me/yehussenmun
የሑሴን ሙንጭርጭሪቶች
✍
📲
👌
👍
pinned «
የተዳፈነ ስሜት (ልዩ ሙንጭርጭሪት) (ረመዷንና ለውጥ # 12)
✍
በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ ረመዷን ላይ … አንዳንድ ስሜቶቻችን ከረመዷን ጋር ተያይዘው በተፈጠሩ ሁኔታዎች ለተወሰነ ጊዜ ይዳፈናሉ ። ኢሄኔ እነዚህ የተዳፈኑ ስሜቱች የተነቃቁ ለታ ጉድ እንዳያመጡ የሚገራቸውን አመለካከት በተወሰነም ቢሆን ከተገነባ ጉዳታቸው ይቀንሳል ። ግንባታው ሲጠናቀቅ ደግሞ ስማቶቻችን መቆጣጠር የምችልበትን አቅም እናገኛለን…
»
የተገራ ስሜት (፣) ን መቆጣጠር
(ረመዷንና ለውጥ # 13)
✍
በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ
የተለያዩ ሸህዋዎች(ውስጣዊ ፍላጎትና ግፊቶች)ን መቆጣጠር እንዳለብንና በዱንያም በአኺራ ደስተኛና ስኬታማ እንደሚያደርገን በተደጋጋሚ ብንደሰኮርም እንዴት እንደምናሳካው ግራ ግ’ብት ያለን ብዙዎች ነን ።
ከለውጥና ከማንነት ግንባታ ጋር በተያያዘ ያለን ግንዛቤ አነስተኛ በመሆኑ (ይመስለኛል) ፤ የሆኑ ነገሮችን ማድረግ ወይም መተው ፣ መሆን ወይም አለመሆን እንዳለብን በጥቅሉ ከማመንና ከማስተማር በዘለለ እንዴታውን የቀረበ እይታ ማግኘት ቸግሮናል ። ለዚያም ነው ብዙ ጊዜ መውደቂያችን ከፍላጎታችን እጅግ የተራራቀ የሚሆነው ።
(እናም እንዴት የሚለውን ስራዬ ብዬ ካፈላለግኩትና ካሰላሰልኩት በመነሳት የገባኝን ያህል ለማጋራት ነው የምሞነጫጭረው ፤ የገባቹ ላይ የገባኝ እንዲጨመርላቹ ።)
… … … … … … …
በቅድሚያ አሉቲዊ ስሜታችንን ከሚቆሰቁሱ ሁኔታዎች ርቀን አመለካከት በመገንባት መግራት ፣ ከዚያም ወደ መደበኛ የኑሮ እንቅስቃሴ መመለስና ስሜትን መቆጣጠር መለማመድ ነው ጥቅል ሂደቱ ። (አመለካከቱ እንዴት እንደሚገነባ እንመለስበታለን ፤ ኢንሻአላህ ።)
ለምሳሌ ፡· የቁጣ ስሜታችንን ለመግራት በቅድሚያ የሚቆሰቁስብንን ነገሮች መራቅ ። ቀጥሎም ሂደቱን በመጠበቅ ቁጣን የሚገራልን አመለካከት መገንባት ። ከዚያም ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያችን ተመልሰን ቁጣችንን የሚቆሰቁሱ ነገሮች ሲፈጠሩ መቆጣጠርን መለማመድ ።
በዚህ ሂደት … በትንሽ ትልቁ ቱግ ከሚልና በቁጣውም መጥፎ ውሳኔዎችን ወስኖ ልክ ያልሆኑ ድርጊቶችን ከሚያደርግ ሰው ፤ … ቁጣውን መቆጣጠር ወደሚችል ብርቱ ሰው መሸጋገር እንችላለን ።
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : " لَيْسَ الشَّدِيدُ بِالصُّرَعَةِ ، إِنَّمَا الشَّدِيدُ الَّذِي يَمْلِكُ نَفْسَهُ عِنْدَ الْغَضَبِ ".
በተደጋጋሚ እንደሰማነው ረሱላችን (ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም) በሐዲሳቸው "ብርቱ ማለት (ሰዎችን) ታግሎ የሚጥል ሳይሆን በቁጣው ጊዜ ነፍሱን (ስሜቱን) የሚቆጣጠር ነው ።" ብለውናል ። (ቡኻሪ እንደዘገቡት)
የቁጣ ስሜታችንን የሚቆሰቁሱ ነገሮች በሚያጋጥሙን በቁጣ ጊዜ ስሜቱን መቆጣጠር የሚችለው አስቀድሞ በአመለካከት የገራው ነው (ሌሎች ሸሪዐዊ ሰበቦች እንዳሉ ሆነው) ። ይህም ሰው በዱንያ ከሌሎች ጋር ባለው ሰላማዊ መስተጋብር ከሚያገኘው ደስታ በተጨማሪ በአኺራ የጀነት ተሸላሚ ነው ።
۞ وَسَارِعُوا إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ
{ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ፡፡} (ኣል ዒምራን 133)
الَّذِينَ يُنفِقُونَ فِي السَّرَّاءِ وَالضَّرَّاءِ وَالْكَاظِمِينَ الْغَيْظَ وَالْعَافِينَ عَنِ النَّاسِ ۗ وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ
{ለእነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣
ቁጭትን(ቁጣን)ም ገቺ(ዋጪ)ዎች
ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት (ተደግሳለች)፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡} (ኣል ዒምራን 134)
አላህ ከእነኚህ ውድ ባሮቹ ያድርገን!
ወ’ሰላም!
እየተቃረብን! ↴
☘
☘
☘
☘
☘
☘
☘
https://t.me/yehussenmun