Выберите регион
и язык интерфейса
Покажем актуальные для региона
Telegram-каналы и возможности
Регион
avatar

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

IbnuMunewor
كناشة ابن منور
Подписчики
109 000
24 часа
30 дней
Просмотры
9 740
ER
9,58%
Посты (30д)
133
Символов в посте
380
Инсайты от анализа ИИ по постам канала
Категория канала
Религия и духовность
Пол аудитории
Мужской
Возраст аудитории
35-44
Финансовый статус аудитории
Средний
Профессии аудитории
Образование
Краткое описание
April 29, 17:02

Live stream finished (58 minutes)

April 29, 16:04
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

😂
ቀጥታ ስርጭት!
📚
የኪታብ ስም፦ሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም!
https://t.me/IbnuMunewor?livestream=f3e6f9f908ef0a70bb

April 29, 16:04

Live stream started

April 29, 14:57
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

ዛሬ ረቡዕ 21/2018 የሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም ኪታብ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ።
*ቦታ :- አሸዋ ሜዳ መስጂደል ዋሊደይን
* ጊዜ :- ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
* ቦታው ላይ መገኘት ለማይችሉ ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

April 29, 14:01

ራሱን ባጠፋ ሰው ላይ ሶላተል ጀናዛ መስገድ
~
በኢስላም ራስን ማጥፋት ትልቅ ወንጀል ነው። ሆነ ብሎ ራሱን ያጠፋ ሰው ከባድ ወንጀል ነው የፈፀመው። ይሄ ማለት ግን አላህ እንዲምረው ዱዓእ ማድረግ እና በሱ ላይ ሶላተል ጀናዛ መስገድ አይቻልም ማለት አይደለም። እንዲያውም ይበልጥ ዱዓእ ያስፈልገዋል። ራስን ማጥፋት ከኢስላም አያስወጣም። ሙስሊምነቱ ከታወቀ ደግሞ በሱ ላይ ሶላተል ጀናዛ መስገድ አይከለከልም። ነብያችን ﷺ ራሱን ባጠፋ ሰው ላይ ያልሰገዱት ከዚህ ጥፋት ሰዎችን ለማስጠንቀቅ ነው። እንጂ ሌሎች እንዳይሰግዱበት አልከለከሉም። በተመሳሳይ ሁኔታ በማህበረሰብ ውስጥ ከፍ ያለ ቦታ ያለው በመሆኑ ሶላተል ጀናዛ አለመስገዱ ሌሎችን የሚያስደነግጥ የሆነ ሰው ባይሰግድ ተመራጭ ይሆናል። ሌሎች ሰዎች ግን ለሟች እንደ ማንኛውም ሙስሊም ዱዓእ ሊያደርጉለት፣ ሶላተል ጀናዛ ሊሰግዱበት ይወደዳል።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 16/2016)
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor

April 28, 10:27
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

አሰላም አሊኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ
ይህቺ ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቷት እህታችን
ሱመያ ካሚል
ትባላለች። የምትኖረው አዳማ
ወንጂ ገፈርሳ
በሚባል ከተማ ሲሆን አሁን ላይ
ሸገር ሲቲ አንፎ ጉዲና (አንፎ ድልድይ
)
አከባቢ ቁርአን ከምትቀራበት መድረሳ ትላንት ሰኞ
ሱብሂ ላይ ከ ጊቢ ከወጣች እስካሁን አልተመለሰችም።  እናም እናት አባት በጣም በጭቀት ላይ ናቸው እና ያያችኋት ወይንም ካገኛችኋት ከታች በምናስቀምጠው ስልክ ደውላችሁ እንድታሳውቁን
በአላህ ስም እንለምናቹሀለን

ለተባበረን ወረታውን እንከፍላለን
ስልክ 0910414128 ካሚል አህመድ
0913703357 ስንታየሁ አየለ

April 28, 03:31

እምነትህን በየትኛውም ዱንያዊ ጥቅም እንዳትለውጥ
~
ዱንያ የፈተና መድረክ ነች። ከፈተና ሁሉ ከባዱ ፈተና ደግሞ የዲን ፈተና ነው። ይህንን ነብያዊ ዱዓእ ላስተዋለ ሰው ትልቅ ቁም ነገር ያገኛል፦
اللهمَّ ... ولا تجعلْ مصيبَتنا في دينِنا، ولا تجعلِ الدنيا أكبرَ همِّنا، ولا مبلغَ علمِنا
"አላህ ሆይ! ... ፈተናችንን በዲናችን ላይ አታድርግብን። ዱንያንም ቀዳሚ ሃሳባችን እንዲሁም የእውቀታችን ጥግ አታድርግብን።" [አልጃሚዑ ሶጊር፡ 1499]
ከሰው ሁሉ አሳዛኝ ከሳሪ ማለት የሚያውቀውን ሐቅ ገፍቶ አላፊ ዱንያን ያስቀደመ ነው። ስንት አሉ ውስጣቸው እየተረበሸ በህሊናቸው ላይ ሸፍተው ወንድ ተከትለው ወይም ሴት ተከትለው ወይም ሌላ ዱንያዊ ፍርፋሪን አስቀድመው ዘላለማዊ ህይወታቸውን ያከሰሩ! "ወንድ ተከትላ እምነቷን ቀየረች"፣ "ሴት ተከትሎ እምነቱን ቀየረ" መባል ሞት አይደለም ወይ? ሰው እንዴት በዚህ መጠን ራሱን ያረክሳል?! ለእርዳታ፣ ለስራ ቅጥር፣ ለትምህርት እድል፣ ለስልጣን፣ ለህክምና፣ ብቻ ለየትኛውም አላፊ ጥቅም ብሎ እንዴት ዘላለማዊ ህይወት ላይ ይወሰናል?! ኣኺራኮ ፍፃሜ የለውም። ከዚህ በላይ ምን ኪሳራ አለ?!
{ فَٱعۡبُدُوا۟ مَا شِئۡتُم مِّن دُونِهِۦۗ قُلۡ إِنَّ ٱلۡخَـٰسِرِینَ ٱلَّذِینَ خَسِرُوۤا۟ أَنفُسَهُمۡ وَأَهۡلِیهِمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۗ أَلَا ذَ ٰ⁠لِكَ هُوَ ٱلۡخُسۡرَانُ ٱلۡمُبِینُ }
"ከእርሱ ሌላ የሻችሁትን ተገዙ። 'ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በትንሣኤ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ንቁ! ይህ እርሱ ግልጽ ከሳራ ነው' በላቸው።" [አዙመር፡ 15]
ህይወት ማለት የኣኺራ ህይወት ነው። ዱንያማ ምን ብትደላ ጤዛኮ ናት።
{وَمَا هَـٰذِهِ ٱلۡحَیَوٰةُ ٱلدُّنۡیَاۤ إِلَّا لَهۡوࣱ وَلَعِبࣱۚ وَإِنَّ ٱلدَّارَ ٱلۡـَٔاخِرَةَ لَهِیَ ٱلۡحَیَوَانُۚ لَوۡ كَانُوا۟ یَعۡلَمُونَ}
"ይህችም የቅርቢቱ ሕይወት መታለያና ጨዋታ እንጂ ሌላ አይደለችም። የመጨረሻይቱም አገር እርሷ በእርግጥ የዘላለም ሕይወት አገር ናት። የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ፤ (ጠፊይቱን ሕይወት አይመርጡም ነበር)።" [አልዐንከቡት፡ 64]
ስለዚህ ዐቅል ያለው ሰው ፈፅሞ ለርካሽ ዱንያዊ ጥቅም ብሎ ኣኺራውን አይሸጥም። በአላፊ የዱንያ ፈተና ተሸንፎ እምነቱን ለድርድር አያቀርብም። ሸይኽ ሷሊሕ አልፈውዛን እንዲህ ይላሉ፦
"የፈለገውን ያህል ዋጋ ቢያስከፍልህ እንኳ እምነትህ ላይ ፅና። ለዱንያዊ ክጃሎት ወይም ጠላትን ፈራሁ ብለህ ከሱ እንዳትርቅ። ያማረው ፍፃሜ አላህን ለሚፈሩት ነውና።"
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor

April 28, 03:31
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

April 27, 12:02

በሌላ አቅጣጫ ደግሞ…
እድሜያቸው ከ10 አመት ምናምን በላይ የሆኑ ልጆቻችን ወደ መስጂድ ይመጣሉ። ነገር ግን ለሶላት ኢቃም ሲባል ወይም ሶላት እየተሰገደ እነሱ በሽንት ቤት ወይም በኡዱዑ ማድረጊያ ቦታ እንዲሁ በማይረባ ወሬ ሶላተል ጀምዓን በማሳለፍ ሁለተኛ ጀምዓ መስገድ አንዳንዴም ሳይሰግዱ ወደ ቤት መመለስ ይስተዋላልና ልጅ ስለሆኑ ጨዋታም ሊያታልላቸው ሸይጣንም ከመጡበት አላማ ሊያዘናጋቸው ይችላልና ወደ መስጂድ መምጣታቸውን በማበረታታት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡት የመጀመሪያ ጀምዓ እንዲሰግዱ ብንነግራቸው መልካም ነው ብየ አስባለሁ።
ወንድማችን Taju Nasir Abu Hanifa

April 27, 08:46

አይተው አይለፉ!
~
መይሙን ብኑ መህራን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"አንድን ሰው ሶላቱ ውስጥ ስህተት እያየበት የማያርም ሰው ምሳሌው የተኛን ሰው እባብ ሲነድፈው እያየ እንደማይቀሰቅስ ሰው ነው።"
[ፈትሑል ባሪ፣ ኢብኑ ረጀብ: 3/144]
~
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor