Выберите регион
и язык интерфейса
Покажем актуальные для региона
Telegram-каналы и возможности
Регион
avatar

Seid Social

Seidsocial
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል
Подписчики
23 200
24 часа
30 дней
100
Просмотры
5 583
ER
20,22%
Посты (30д)
110
Символов в посте
912
Инсайты от анализа ИИ по постам канала
Категория канала
Политика
Пол аудитории
Мужской
Возраст аудитории
35-44
Финансовый статус аудитории
Средний
Профессии аудитории
Медиа и коммуникации
Краткое описание
May 08, 17:47

ከ 2013 እስከ 2022 በ 9 አመት ውስጥ ብቻ ኢትዮጵያ በሙስና 25 ቢሊዮን ዶላር አጥታለች። ይሄ የሀገሪቱን አጠቃላይ ኢኮኖሚ 25% ይሸፍናል። ከ 2022 በሗላ ደግሞ የሙስና ፍጥነቱ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በአመት ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር እየደረሰ መሆኑን የአፍሪካ ልማት ባንክ ያወጣው መረጃ ያሳያል።
በትንሹ 3 ቢሊዮን ዶላር ወስዳችሁ ከላይ ካለው ቁጥር ላይ ብትጨምሩበት አጠቃላይ ኢትዮጵያ ከ 2013 ጀምሮ በሙስና ያጣቺው ገንዘብ 34 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል።
ይሄንን አሀዝ ወደ ብር ብትቀይሩት 5 ትሪሊዮን 440 ቢሊዮን ብር ይደርሳል።
ይሄ የተወሰደ ብር የት ነው የሄደው ካላችሁ እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ መረጃ ከሆነ አብዛኛው በባለስልጣናት እና በባለሀብቶች አማካኝትት ከኢትዮጵያ ወጥቷል።
የአፍሪካ ልማት ባንክ መረጃ አክሎም በኢትዮጵያ የውጭ ገቢ ንግድ በትክክል ሪፖርት የሚደረገው 35% ብቻ ሲሆን 65% ሪፖርት የውሸት ሪፖርት ነው።
የኢትዮጵያ 15 የኢትዮጵያ ቢሊየነሮች በስዊዝ ባንክ እና በካሪቢያን ወስጥ በምትገኘው ካይማን ደሴት በሚገኝ ባንክ አካውንት ከፍተው ገንዘባቸውን ወደዚያ ያስወጣሉ- ከባለስልጣናት ጋር በመተባበር።
የኢትዮጵያ የወርቅ 30% ከኢትዮጵያ በሱዳን በኩል ብሎ ኢማራት ይደርሳል እንጅ የኢትዮጵያ ባንኮችን ንክች አያደርግም።
ይሄ ሁሉ ሀብት ከዚህ ድሀ ህዝብ ላይ ከዚህች ድሀ ሀገር ላይ የተቀማ የተሰረቀ ነው።
ይሄ እጅ ከወርች የሚያሳስር ሙስና ባለበት ተጨባጭ ሀገር በፍፁም በፍፁም አታድግም።
የደለቡት ሳይጠግቡ ሌሎች አዲስ ረሀብተኛ ሙሰኞችም እየመጡ ሀገሪቷ እንዲህ ሆና መቅረቷ ያሳዝናል።
ይህ ሙስና የኢትዮጵያ ህዝብ የኑሮ ሁኔታ ያቃወሰ ፤ የዋጋ ንረቱን ባለፉት ጥቂት አመታት ከ 400%
በላይ እንዳደርስ ያደረገ ፤ የብርን የመግዛት አቅም ባለፉት ስምን አመታት ብቻ በ 500% እንዲወድቅ ያደረገ አሳዛኝ ሰባሪ ክስተት ነው።
ይህን በሙስና የሚጠፋውን ገንዘብ ለማሟላት ሀገሪቱ በነ IMF የብድር ማነቆ ውስጥ ገብታለች ፤ ህዝባችን ላይ ከአቅም በላይ የሆነ ግብር ተቆልሎበታል እንዲሁም በርካታ ሀገር የሚለውጡ ፕሮጀክቶች ታጥፈዋል።
በዚህ ሙስና ምክንያት ሀገሪቱ የጦር አውድማ ሆና መረጋጋት የተሳናት ሆና ቀጥላለች!
ኡኡኡኡ የሚያስብል ሁኔታ ላይ ነው ያለነው!
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial

May 08, 11:12
Файлы недоступны
3
Открыть в Telegram

ይህ እንግዲህ ለአማራ ህዝብ ሲባል ነው¡
እንኳን ነፃ ሊያወጡ ነፃነት ምን እንደሆነ እንኳ የማያውቁት የመሀይማን ስብስብ በነፃነት ስም ላዘሮፉት ከዘመቱበት የአማራ ህዝብ ላይ እንደዚህ በሬውን እያረዱ የስጋ አምሮታቸውን እየተወጡ ነው።
እነዚህ ሽፍታዎች የአማራን ገበሬ ካለ በሬ አስቀርተው መሬቱን ጦር አሳድረው ለረሀብ እየዳረጉት ይገኛሉ።
ጠላ እያስጠመቁ እንጀራ እያስጋገሩ ከዚያ እንዲህ እያረዱ ዘልዝለው አለማቸውን እየቀጩ ነው።
የአማራ ህዝብ እንዲህ ያለ ጠላት በታሪኩ ገጥሞት አያውቅም!
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial

May 08, 06:38
Файлы недоступны
2
Открыть в Telegram

አሜሪካ ከማታው ሚከራዋ ዳግም አፈግፍጋለች።
የአሜሪካ ጦር መርከቦች ወደ ሆርሙዝ ሰርጥ ለመግባት ያደረጉት ሙከራም በኢራን የሚሳኤል ጥቃት ምክንያት ከሽፎ መርከቦቿ ወደ ሗላ መመለሳቸውን አሜሪካ አስታውቃለች።
በኢራን ዋና ግዛት ላይ የተፈፀሙ የአየር ጥቃቶችንም የኢራን አየር መከላከያ ማክሸፍ በመቻሉ ውድመት ሳይደርስ ቀርቷል።
አሜሪካ ጥቃቱን የፈፀምኩት በጦር መርከቦቼ ላይ ለተፈፀመው ጥቃት አፀፋ ነው ብትልም እውነተኛ ምክንያቱ ግን ኢራንን ወደ ድርድሩ ለማስገደድ እና የአሜሪካ ፍላጎቶች እንዲትቀበል ለማስገደድ ነበር። ሆኖም ሁሉም ሳይሳኩ አሜሪካ ጦጦርነቱን አቁማለች።
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial

May 07, 21:20
Файлы недоступны
3
Открыть в Telegram

አሜሪካ እና ኢራን ዳግም ጦርነት ጀምረዋል።
የኢራን አየር መከላከያ በቴህራን እና ሌሎችም የኢራን አካባቢዎች የመከላከል እርምጃ እየወሰደ ሲሆን በደቡባዊ ኢራን ፍንዳታ ተሰምቷል።
አሜሪካ ጥቃቱን እንደፈፀመች ገልፃ ነገር ግን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ማፍረስ አይደለም ብላለች።
ኢራን በበኩሏ አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነቱን መጣሷን በመግለፅ የአፀፋ እርምጃዋን እንደምትጀምር ገልፃለች።
ኢራን ወደ ሆርሙዝ ሊገቡ ያሉ ሶስት የአሜሪካ ጦር መርከቦችን ማጥቃቷንም ገልፃለች ።
t.me/Seidsocial

May 07, 19:42
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

ቻይና ሁለት መከላከያ ሚኒስትሮቿ ላይ የሞት ፍርድ ወስናለች።
በሙስና ምክንያት ከሁለት አመት በፊት ከስልጣን የተነሱት መከላከያ ሚኒስትሩ ወይ ፈንጌ እና ሌላኛው የቀድሞው መከላከያ ሚኒስትር ሊ ሻንግፉ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ መባላቸውን ተከትሎ ሁለቱም ላይ የቻይና ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ በይኗል።
የሞት ፍርዱ ለሁለት አመት የሚዘገይ ሲሆን በሁለት አመት ውስጥ ተጨማሪ ወንጀል ካልተገኘባቸው ወደ እድሜ ልክ እስራት ሊቀየር ይችላል።
ከሞት ፍርዱ በተጨማሪ የሁለቱ መከላከያ ሚኒስትሮች ሀብትም ሙሉ ለሙሉ ተወርሷል።
በቻይና ሙስና በሞት የሚያስቀጣ እጅግ አደገኛ ወንጀል ነው። ቻይና የትኛውም ባለስልጣን ሙስና ውስጥ ገብቶ አገኘሁት ካለች የሚጠብቀው ሞት ነው።
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial

May 07, 17:19

መንግስት የትምህርት ሴክተሩን ያክል ጦርነት ያወጀበት የገደለው ሌላ ሴክተር ያለ አይመስለኝም። በብልፅግና 8 የስልጣን አመታት የትምህርትን ያክል ትኩረት የተነፈገው በፊት ይበጀትለት የነበረው በጀት የተቋረጠበት ሴክተር የለም።
ለምሳሌ ዩኔሴፍ በ 2024 ይዞት የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ ለትምህርት የምትበጅተው በጀት ከኢኮኖሚዋ አንፃር በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መሆኑን ያሳያል። 2020 ላይ ኢትዮጵያ 4% ኢኮኖሚዋን ለትምህርት ታውል የነበረ ሲሆን በ 2024 ይህ አሀዝ ወደ 2.3% አሽቆልቁሏል ። ይህም ኢትዮጵያን በአለም ደረጃ ከኢኮኖሚ ጥቅል ምርታቸው አንፃር ዝቅተኛ በጀትን ለትምህርት ከሚመድቡ 21 ሀገራት አንዷ ያደርጋታል። በአለም ላይ ከኢትዮጵያ በታች ለትምህርት የሚመድቡት ኤርትራ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳንን የመሳሰሉ መናጢ ጎረቤቶቻችን ናቸው።
በአሁኑ ሰአት ኢትዮጵያ በአለም በትምህርት ደረጃ ከ 193 ሀገራት 182 ደረጃ ላይ ትገኛለች። ይህ የዩኒስኮ መረጃ ነው። የምንበልጠው 10 ሀገራትን ብቻ ነው ማለት ነው። እንዴ ሀገር ወዴት እየሄደች ነው ተብሎ አይጠየቅም እንዴ?!!
አንድት ከፍተኛ ያልተማረ ህዝብ ያለባትና ህዝቧም በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ያለባት ከፍተኛ የተማረ የሰው እጥረት ያለባት ሀገር ትልቁ በጀቷ ትልቁ ኢንቨስትመንቷ ሊሆን የሚገባው ትምህርት ነበር። እንዳለመታደል ግን እኛ በተቃራኒው ነው እየተጓዝን ያለነው።
ታዲያ መንግስት ለትምህርት የሚሰጠውን በጀት በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል ማለት ምን ማለት ነው? ጉዳቱስ ምንድነው ? ካልን እንደው በደፈናው ሀገር ቀንጭራ ትቀራለች ማለት እንችላለን። ትንሽ እናብላላው።
1 ለትምህርት የሚሰጠው በጀት በመቀነሱ ሀገሪቱ ባለፉት 8 አመታት አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች እና የምርምር ማእከላትን መገንባት እንድታቆም አድርጓታል። ካለነዚህ ተቋማት በምንም ተአምር አንዲት ሀገር አትለወጥም አታድግም!
2 ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች የቅበላና የማስተማር አቅማቸው በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቷል። የሚለቀቅላቸው በጀት በመቀነሱ ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎቻቼው የሚያቀርቡትን ግብአቶች በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሰዋል። ከካፌ ምግብ አቅርቦት ጀምሮ በአሁኑ ሰአት ዩኒቨስቲ መማር እጅግ ከባድ ሆኗል።
3 ትምህርት የጥቂቶች እንዲሆን ተደርጓል። ዩኒቨርሲቲዎች ድጎማ ስለተነሳባቸውና ራሳችሁን ቻሉ ስለተባሉ እያስከፈሉ ወደ መማር የንግድ ማእከልነት ተሸጋግረዋል። በዚህም መክፈል የማይችሉ የድሀ ልጆች በሀገሪቱ ታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች መማር እንዳይችሉ እየተደረጉ ነው። ታላቅ የትምህርት ብቃት ያላቸው ተማሪዎች እንዲህ እንዲሆኑ መፈረዱ አሳዛኝ ነው። ይህ ሂደት በሀገሪቱ አደገኛ ውጤት ይኖረዋል።
4 ደካማ የመማሪያ ከባቢ ተፈጥሯል። ከደረጃ በታች የሆኑ በቂ የቴክኖሎጂ ግብአት የሌላቸው እንዲሁም ፅዱ ኢንቫይሮሜንት የሌላቸው ዩኒቨርስቲዎችና ትምህርት ቤቶች በእውቀት የታጠቀ ከዘመኑ ጋር አብሮ መጓዝ የሚችል ትውልድ ያፈራሉ ብሎ ማሰብ ላም አለኝ በሰማይ የሆነ ህልም ነው!
5 የመማር መንፈስ ተሰብሯል። አሁን ትውልዱ መማር አይፈልግም። ቅድመ ምረቃም ሆነ ድህረ ምረቃ ያሉት ሁኔታዎች ለትምህርት የሚጋብዙ አይደሉም።
6 መንግስት የሰነፍ ፕሮፓጋንዳ እየሰራ ነው። ፈትኖ ትንሾ ተማሪ ማሳለፍን እንደ ትልቅ ስኬት በመቁጠር አብዛኛውን ተማሪ ብቁ እንዳይሆንና ከፈተና ጥራት ይልቅ የትምህርት ጥራት ላይ እንዳይሰራ አድርጓል።
7 ይህ ሁኔታ ከቀጠለ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ፣ እድገት ከፍተኛ አደጋ ይደቀንበታል።
8 ትምህርት የጥቂቶች ብቻ የሚሆንበት ሁኔታ እየተፈጠረ ነው። ይህቺን ለመቀባባት ምሳ እየመገብኩ እያሰሰተማርኩ ነው የሚለው የመንግስት ማስተባበያ ህመሙን አያክመውም።
9 መምህራኖች በቂ ክፍያ የማይከፈላቸው በመሆኑ የመማር ማስተማርን ሞራል በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳዋል። የስራ አጥነትም ይስፋፋል። የሀገሪቱን ፍላጎት ማሟላት የሚችሉ ብቁ ዝጎች እንዳይወጡ ያደርጋል።
በመሆኑም መንግስት ለትውልድ ካሰበ ትኩረት የነፈገውን የትምህርት ዘርፍ ትኩረት ይስጥ። የዩኒቨርስቲ ድጎማዎችን ይቀጥል። ለትምህርት ያልሆነ በጀት ለምርምር ያልሆነ ገንዘብ ለምን ሊሆን ነው???
እኔ በዚህ ጉዳይ ስለ ሀገሩ እንደ ሚቆረቆር አንድ ኢትዮጵያዊ መወትወቴን እቀጥላለሁ።
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial

May 07, 11:03
Файлы недоступны
3
Открыть в Telegram

"እንደት ፋኖን የትምህርት ጠላት አድርገህ ታስቀምጠዋለህ ፋኖኮ የአማራን ህዝብ ነፃ አውጭ ነው" የሚሉ አስተያየቶች ከቀደመው ፖስት ጋር ተያይዞ ደርሰውኛል።
እንደውም በኔ እምነት በኢትዮጵያ ውስጥ የፋኖን ያክል የትምህርት ጠላት ፤ የተማሩ ሰዎች ጠላት ያለ አይመስለኝም።
መማርም ማስተማርም የማይወድ የሰነፎችና የመሀይማን ስብስብ መሆኑን ቅንጣት አልጠራጠርም።
ይህ ሀይል "እንደት እኛ እየታገልን እናንተ ትማራላችሁ? በማለት በርካታ ተማሪዎችን የገደለ
" እንደት እኛ እየታገልን ታስተምራላችሁ በማለት በዚያ ጦርነት ውስጥ እንኳ እያስተማሩ የነበሩ መምህራንን አንበርክኮና አዋርዶ የረሸነ
በርካታ ትምህርት ቤቶችን አውድሞ የተቀሩትን መመሸጊያው ያደረገ
የለየለት የትምህርት ጥራት መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም።
ይህ ሀይል ውንብድናውን እንደ ነፃነት ትግል እየደሰኮረ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአማራ ልጆችን ከትምህርት ገበታ ውጭ ያደረገ ትምህርት በዞረበት ያልዞሩ ወያላዎችና ማጅራት መችዎች ስብስብ ነው።
ይህ ከታች ያለው ቪዲዮ የዚህ ቡድንን ማንነት የሚያሳይ አንድ ማሳያ ነው። እናም ይሄ ቡድን በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የትምህርት ገዳዮች ዋነኛው ነው።
መንግስትን እንደት የትምህርት ገዳይ ትላለህ ለሚሉ በቀጣይ ብልፅግና እንደት ትምህርትን እየገደለ መሆኑን እመለስበታለሁ!
t.me/Seidsocial

May 07, 09:08

መንግስትም ትምህርትን እየገደለው ነው!
አማፂያንም ትምህርትን እየገደሉት ነው!
የሀይማኖት ሰባኪ ነን ባዮችም ትምህርትን እየገደሉት ነው!
የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪዎችም ትምህርትን እየገደሉት ነው!
በአጭር አቋርጠው የከበሩ ባለሀብቶችም ትምህርትን እየገደሉት ነው።
ሀገሪቱ አጠቃላይ ትምህርትን ጥናትና ምርምርን ጠላት አድርጋ ይዛለች።
መሃይምነት በእጅጉ ተንሰራፍቷል። ህዝቡ የሀይማኖት ጠንቋዮች ገባሪ ሆኖ አሜንን እያለ በመጮህ ለመለወጥ እየሞከረ ነው የሚገኘው። ድሮም መሀይም ህዝብ የጠንቋዮች መጫወቻ ነው።
አሁን ላይ ትምህርትን አማራጭ አድርጎ የሚወስድ ትውልድ እየጠፋ ነው።
ወይ ፈምሶ ወይ ሸፍቶ ወይ የሀይማኖት ጠንቋይ ሆኖ ወይንም ካድሬ ሆኖ ነው ለመለወጥ እየተመመ ያለው።
ሀገሪቱ ለትምህርት የምትበጅተውን ገንዘብ እየቀነሰች ሳይሆን እያቆመች ነው ማለት ይቻላል። አሁን ላይ ለመንግስት ትምህርት የሚባል ሲያዩት የማያምር ነገር ትኩረቱም ደንታውም አይመስልም።
ከ 10 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች በመላ ሀገሪቱ ከትምህርት ገበታ ውጭ ናቸው። ዩኒቨርሲቲዎች ለመዘጋት ተቃርበዋል።ተማሪዎቻቼውን የሚመግቡት ምግብ እንኳ የላቸውም ለምን? በጀት ስለተቋረጠ።
እናም አበበ ጅብ ሆነ ብሎ የሚገድል ፤ ማሪያም ቆላድባ ተከሰተች ብሎ እልልታውን የሚያቀልጥ ፤ አካውንቱ ላይ ገንዘብ እንዲገባለት የቅዱሳንን
😁
ውሀ የሚያስረጭ ፤ መገዳደልና መጫረስ ቀላሉ የሆነለት መሀይም ህዝብ እየተፈጠረ ነው።
የአለም ህዝብ በምክንያታዊነት ወደፊት እየሄደ እየሰለጠነ በሄደ ቁጥር የኢትዮጵያ ትውልድ ግን በአስደናቂ መልኩ ወደሗላ ወደ መሀይምነት እየተጓዘ ነው። እዚህች ሀገር ላይ በትክክለኛው የትምህርት ስርአት ድግሪ የያዙ ሰዎች እያነሱ ድግሪ እና ዶክትሬት ገዝተው የሚያጠልቁ የሚበዙባት ሀገር እየሆነች የመሄዷ ነገር ያስፈራል!
መንግስት ትኩረት የነፈገውን የትምሀርት ዘርፍ ዳግም የትኩረት ዋነኛ አቅጣጫው አድርጎ ትውልዱን ካልታደገ እንደ ሀገር እንወድቃለን።
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial

May 06, 19:35
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

የእስራኤል ወታደር ዛሬ በሊባኖስ የድንግል ማርያምን ሀውልት ካዋረደ በሗላ ሁለት ሲጋራ ይዞ አንዱ ለርሱ እያጨሱ አንዱን የእርሷ ሀውል አፍ ላይ ሲሰካ መታየቱ አዲስ ቁጣን ቀስቅሷል።
በደቡባዊ ሊባኖስ ወረራ እየፈፀመ የሚገኘው የእስራኤል ጦር በክርስትና ገዳማት አብያተ ክርስቲያናት እና ሀውልቶች ላይ ከማፍረስ እስከ መፀዳዳት ከዚያ አልፎም በቤተክርስቲያን ውስጥ የወንድ ለወንድ ጋብቻ እስከማድረግ የደረሰ ማዋረድ እየፈፀመ ይገኛል።
እስራኤል ለይምሰል መግለጫ ብታወጣም ድርጊቱ ተባብሶ ቀጥሏል።
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial

May 06, 18:33

ሱልጧን ብይዚድ የልድሪም ማን ነው ካላችሁ እርሱ ጠላቶቹ በእጅጉ የሚፈሩት ስሙንም የልድሪም ወይንም ነጎድጓዳማው ያሉት አራተኛው የኡስማኒያ ሱልጧን ነበር።
ሱልጧን ቤይዚድ በልጅነቱ ከአባቱ ሙራድ ጋር በመሆን በጦር ልምድ ጥንቅቅ ብሎ ያደገ በኡለሞች ተኮትኩቶ ለመሪነት የወጣ ተወዳጅም ተፈሪም ሱልጧን ነበር። እርሱ የአርቱግሩል አምስተኛ ትውልድ የኡስማን አራተኛ ትውልድ የኦርሀን የልጅ ልጅ ልጅ የሙራድም ልጅ ነበረ።
ጦሩን ከአናቶሊያ እስከ ስራቅ አውሮፓ በሚያስደንቅ ፍጥነት የሚያንቀሳቅስ በመሆኑ መብረቅ ወይንም ነጎድጓድ የሚል ስም ተሰጠው።
ሱልጧን ቤይዚድ የመስቀል ጦረኞችን በሙስሊሙ አለም ላይ ከማሸነፍም አልፎ ተከታትሎ አውሮፓ ድረስ በመግባት ኒኮፖሊስ ላይ በ 1396 ከፈረንሳይ እንግሊዝ ጀርመን እና ሌላውም የአውሮፓ ክፍል የተውጣጣውን የአውሮፓ መስቀል ሀይል በመደምሰስ ደቡብ ምስራቅ አውሮፓን ለመጀመሪያ ጊዜ የኢስላማዊው ኦቶማን ግዛት አድርጎታል። በዚህም የባልካን ግዛት የኡስማኒያ ግዛት ሆነ። ዛሬ ላይ በአውሮፓ የምናውቃቸው ሙስሊም ሀገራት እነ አልባኒያ ፣ ቦስኒያ ፣ ኮሶቮ የመሳሰሉት ከያኔው መከፈት ጋር የተያያዙ ናቸው።
ቤይዚድ ሀያል ጦሩን እየመራ ኮንስታንትኖፕልን ለመጀመሪያ ጊዜ ከበበ። በዚህ ከበባ ላይ እያለ የቱርኮ ሞንጎሉ መሪ አሚር ቲሙር በቤይዚድ ላይ ጦርነት አወጀበት። አሚር ቲሙር ወይንም ቲሙር ኻን አልያ ታመርሌንም ይሉታል የቱርክ እና ሞንጎል ቅልቅል ሲሆን ኢስላምን ተቀብያለሁ በማለት አሚርነትን የተጎናፀፈ መሪ ነበር።
አሚር ቲሚር እጅግ ሀይለኛ በአለም ታሪክ ከታዩ የጦር ታክቲሻኖች ከእጅግ አስደማሚዎቹ አንዱ ነው። የቲሙር ቅፅል ደግሞ ነበልባል ይባል ነበር። በጊዜው ባደረገው ጦርነት ከ 17 ሚሊዮን በላይ ህዝብ እንደጨረሰ ይነገራል። እናም ቤይዚድ ነጎድጓዱ እና ቲሙር ነበልባሉ በአንካራ ግዙፉን ጦራቸውን እየመሩ ተላተሙ። ምድር ቃጤ ሆነች።
በርካታ ኡለምች አሚር ቲሙር ሙስሊም የመሰለው ለፖለቲካው ነው በማለት በቲሙር ላይ ጂሀድ ቀሰቀሱ። ግና ድል የአሚር ቲሙር ወይንም ታመርሌን ነበረች።
በአንካራ ጦርነት የኦቶማን ሱልጧኔት በቲምሩድ ሀይል ተሸነፈና ሱልጧን ቤይዚድ ተማረከ።
ሱልጧን ቤይዚድ ከነባለቤቱ ተማርኮ በአሚር ቲሙር ጋር ካሳለፈ በሗላ ሚስቱ አገልጋይ ሆና እንዲያት በማድረግ ከፍተኛ ቁጭት ከከተተው በሗላ አሚር ቲሙር በመጨረሻም ቤይዚድን ሊገድለው ችሏል።
ሱልጧን ቤይዚድ በመገደሉ ኮንስታንትኖፕልን መክፈቱ ሲቋረጥ የኦቶማን ሱልጧኔትም ተበታተነ። ከዚያ በሗላ ነው የሱልጧን ቤይዚድ ልጅ ሙሀመድ የተበታተነው ሱልጧኔት እንደገና መልሶ ዳግም ኦቶማንን የወለደው።
የሙሀመድ የልጅ ልጅ ሙሀመድ አልፋቲህም የቅድመ አያቱን የቤይዚድን ህልም በማሳካት ኮንስታንትኖፕልን ወይንም ኢስታንቡልን ሊከፍታት ችሏል።
ሱልጧን ሙሀመድ አልፋቲህ የሱልጧን ቤይዚድ የልጅ ልጅ ልጅ ነበረ።
ሱልጧን ቤይዚድ ከፍተኛ ዲስፕሊን ያለው ኡለማኦችን በከፍተኛ ደረጃ የሚወድ ሙስናና ማጭበርበርን በፍፁም የማይታገስ መሪ እንደነበር ይነገራል። ሱልጧን ቤይዚድ ለወታደሮቹ ቋሚ መደበኛ ደመወዝ መክፈል የጀመረ እንደሆነም ይነገርለታል።
እናም ቱርክ የመጀመሪያውን አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል የሰየመቺው በዚህ ታሪካዊ መሪዋ ስም ነው።
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial