
Amhara Media Corporation
🕊️
የግጭት ምንጭ ይድረቅ፣ የሞት እርምም ይውጣ
✨
በአማራ ክልል ባለፉት ሦሥት ዓመታት በዘለቀው የሰላም እጦት ምክንያት ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት ደርሷል። ማኅበረሰቡ በደስታና በሀዘን እንዳይገናኝ፣ ማኅበራዊ ግንኙነት እንዲገታ አድርጎ ቆይቷል። በርካቶችን ለሥነ-ልቦና ጉዳትም ዳርጓል።
ወንድም ወንድሙን እያደማ ቆይቷል። ግጭቱን ለማስቆም በርካታ የሰላም ጥሪዎች ቀርበዋል። የሰላም በሮችም ተከፍተዋል። ይህንን አስከፊ በደል እና ግፍ በመገንዘብ የሰላም አማራጭን…
የሰማዩ ንስር፣ የሉዓላዊነት ጠበቃ!
የኢትዮጵያ አየር ኅይል የሀገርን ሉዓላዊነት እና ደኅንነት ለማረጋገጥ ሰማይን በንስር ዐይን እየቃኘ 90 ዓመታትን ተሻግሯል።
ይህ ታሪካዊ አየር ኃይል የኢትዮጵያን እና የቀጣናውን ሰላም ሲያስከብር የኖረ የጀግኖች ቤት ነው።
የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ከማስከበር አልፎ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተልዕኮዎችን በብቃት መወጣት ችሏል። በ1954 ዓ.ም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሥር ኾኖ በኮንጎ…
የሐረሪ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚቀላቀሉ ተማሪዎች ድጋፍ አደረጉ።
ርእሰ መሥተዳድሩ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ወስደው ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚቀላቀሉ እና ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች ማበረታቻ እና ድጋፍ አድርገዋል።
በክልሉ በፈተናው ከ500 በላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ከ50 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ሰሞኑን የተበረከተ ሲኾን ዛሬ ደግሞ ከከተማ እና ከገጠር ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ እና ድጋፍ…
በወገራ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበላቸውን ቀጥለዋል።
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ ገደብጌ እና አካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።
የወገራ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ሹመት ዋሴ መንግሥት የሰላም አማራጩን ክፍት በማድረግ በግጭት ውስጥ ያሉ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ዕድል እየሰጠ መኾኑን ገልጸዋል ።
የወገራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አይፈራም አያናው…
ሰላምን አጥብቃችሁ ያዟት !
ሰላም በዋጋ የማይለካ እና ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው የሰው ልጅ የመኖር ሕልውና ነው። በአማራ ክልል ባለፉት ዓመታት በነበሩ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች የደረሱ ውድመቶች የሰላምን ዋጋ በግልጽ አሳይተዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ዋና ፀሐፊ መላዕከ ብርሃን ፍስሐ ጥላሁን ሰላም ሲታጣም ኾነ ሲደፍርስ የሚጎዱት የሰው ልጆች ብቻ…
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከሱዳን ጋር ይጫወታል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን (ዋልያዎቹ) በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ከሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል። ጨዋታው በደቡብ ሱዳን ጁባ ናሽናል ስታዲየም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ሲኾን ብሔራዊ ቡድኑ የማጣሪያ ጉዞውን በስኬት ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቅቋል። በዚህ የሜዳ ውጭ ጨዋታ ዋልያዎቹ ሦሥት ነጥብ ይዘው በመውጣት ለቀጣዩ ጉዟቸው አዎንታዊ የሥነ-ልቦና የበላይነት ይይዛሉ…
ለዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ዝግጁ የኾነው ግዙፍ ስታዲየም በምስል
👆
👆
👆
#አሚኮ
#bahirdarinternationalstadium
#Ethiopia
የተራራው ላይ የመስቀል በዓል _ አንኮበር
አንኮበር በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደብረ ብርሃን ከተማ 42 ኪሎ ሜትር ገደማ ላይ የምትገኝ፣ ታሪክ፣ ባሕል እና ተፈጥሮ የተጣመሩባት ታሪካዊ ሥፍራ ናት። በቀደሙት ዘመናት የሸዋ ነገሥታት ማዕከልም ኾና አገልግላለች።
አንኮበር እና አካባቢዋ የአጼ ምኒልክ ቤተ መንግሥት፣ ጥንታዊ አብያተ ክርስትያናት፣ የወፍ ዋሻ ደን፣ የቀደምት የሸዋ ነገሥታት የቀብር ቦታ፣ ፍልፍል…
“ሰዎች ባስቆጠርኳቸው ግቦች ብቻ ሳይኾን ለወገኔ ባበረከትኩት በጎ ነገር እንዲያስታውሱኝ እፈልጋለሁ” ሳዲዮ ማኔ
ሳዲዮ ማኔ በትውልድ መንደሩ የ20 ሚሊዮን ዶላር የግብርና ፕሮጀክት አስጀመረ። የሴኔጋሉ የእግር ኳስ ኮከብ ሳዲዮ ማኔ በትውልድ ቀዬው ባምባሊ “ኤስኤም10 አግሮ” የተሰኘ የ20 ሚሊዮን ዶላር የግብርና ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል። ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ከ2ሺህ 500 በላይ ለሚኾኑ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር ሲኾን ከ78ሺህ በላይ የማንጎ ዛፎችን ለመትከል ያለመ ነው። ማኔ ከስኬቱ በስተጀርባ ያለውን ዓላማ ሲያብራራ…
በወረኢሉ ወረዳ በኩታ ገጠም እየለማ የሚገኝ የስንዴ ማሳ
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ በኩታ ገጠም እየለማ የስንዴ ማሳ
📷
ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገጽ የተወሰደ