Выберите регион
и язык интерфейса
Покажем актуальные для региона
Telegram-каналы и возможности
Регион
avatar

አል ሀበሻ እስላሚክ ቻናል

ethio_muslim_media
Подписчики
1 010
24 часа
-6
30 дней
-87
Просмотры
155
ER
15,35%
Посты (30д)
5
Символов в посте
1 103
Инсайты от анализа ИИ по постам канала
Категория канала
Религия и духовность
Пол аудитории
Мужской
Возраст аудитории
25-34
Финансовый статус аудитории
Средний
Профессии аудитории
Образование
Краткое описание
September 18, 20:11
Файлы недоступны
3
Открыть в Telegram

🔧
🔥
SAFETY RELIEF VALVE | PRESSURE RELIEF VALVE
🏭
የኢንዱስትሪ የግፊት መቆጣጠሪያ እና የደህንነት ቫልቭ!
ይህ እቃ በሲስተም ውስጥ ያለው ግፊት ከተወሰነ ደረጃ ሲያልፍ ግፊቱን ለመልቀቅ የሚያገለግል Safety Relief Valve ሊሆን ይችላል።
✅
ለኢንዱስትሪ የቧንቧ መስመሮች
✅
የግፊት ደህንነት ሲስተም
✅
ለተለያዩ የኢንዱስትሪ መሳሪያዎች
🔧
Available Products:
Ball Valve • Gate Valve • Check Valve
Flanges • Pipe Fittings • Safety Valves
📍
Addis Ababa, Ethiopia
🇪🇹
📞
Order Now:
0910 514 503
📩
ለትዕዛዝና ለተጨማሪ መረጃ ያግኙን!
🏭
FLANGEZONE_ETH — Industrial Valves & Pipe Fittings
🔩
#SafetyReliefValve
#PressureValve
#IndustrialValves
#FlangeZoneEth
#Ethiopia
🇪🇹

September 17, 10:27
Файлы недоступны
4
Открыть в Telegram

📢
🔥
አስቸካይ ማስታወቂያ ለጥቂት ቀናት የሚቆይ
💧
ለቤትዎ እና ለክስተቶችዎ ልዩ ውበትንና ዘመናዊነትን ያክሉ!
Wave Coupe Glass (የአበባ ቅርጽ ብርጭቆ) — ለማንኛውም ለቤት፣ ለካፌ፣ እና ለሬስቶራንት አገልግሎት ላይ ለሆቴሎች፣ ለተለያዩ ለስላሰ መጠጦች፣ አይስክሬምና ጣፋጭ ምግቦችን (Desserts) እጅግ ማራኪ በሆነ መልኩ ለማቅረብ እና ለገበታዎ ልዩ ድምቀት ለመስጠት የሚያገለግል የጥራት መለኪያ።
✅
Borosilicate High Quality Glass (ቀላል፣ ግልጽና ረጅም ዘመን የሚቆይ ጠንካራ ብርጭቆ)
✅
Elegant Wave Design (ማራኪና ልዩ የሆነ የሞገድ/የአበባ ቅርጽ አሠራር)
✅
(በምስሉ ላይ እንደሚታየው በውብ ቅርጽ ያጌጠ እግር ያለው)
✅
For Cocktails & Desserts (ለኮክቴል፣ ለሻምፓኝ፣ ለአይስክሬምና ለተለያዩ ጣፋጮች የሚሆን)
📞
ለዋጋና ተጨማሪ መረጃ አሁኑኑ ፈጥነው ይደውሉልን በብዛት አለን፦
0912672626 ወይም 0913948209
⬇️
🔥
#WaveGlass
#CoupeGlass
#HomeDecor
#LuxuryGlassware
#Ethiopia
#Fyp

September 15, 09:21
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

September 13, 14:23

ማሳሰቢያ ይህ ቻናል የንግድ ብቻ አይደለም ባረከለሁ ፊኩም የሱናም ጭምር ነው።
አንዳንድ ወንድሞችና እህቶች ከቻናሉ እየለቀቁ መሆኑን ስለደረሰን ነው

September 13, 14:21

​
🔴
አስቾኳይ የዱዓ ጥሪ!
​የቀድሞው የፉርቃን እና የአሳር መስጂድ ሙአዚን
አብዱረህማን አል-ሙአዚን
በጠና ታሞ ነገ የጭንቅላት ሰርጀሪ (ኦፕሬሽን) ይደረግለታል።
​
🤲
በዱዓችሁ አስቡት!
አላህ  ሙሉ ዐፊያውን ለግሶ በሰላም ወደ ቤተሰቦቹ እንዲመልሰው እንለምናለን።
​
🙏
በህክምናው ሂደት እና እርዳታ ላይ እየተንቀሳቀሱ ላሉ ወንድሞቻችንም አላህ እጥፍ ድርብ አድርጎ ይመንዳቸው፤ በሁለቱም ዓለም ደስታን ያጎናፅፋቸው።
​
http://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio
https://t.me/Abu_Muhammed_MuhammedSed/

September 10, 10:42
Файлы недоступны
3
Открыть в Telegram

💧
የውሃ፣ የዘይት እና የጋዝ ፍሰቶችን በጥራትና በቁጥጥር ይምሩ!
🔧
Lug Type Butterfly Valve (ባተርፍላይ ቫልቭ) — ለማንኛውም የኢንዱስትሪ፣ የውሃ መስመር፣ የፓይፕ መስመር ግንኙነቶች እና የፈሳሽ ፍሰት ቁጥጥር ስርዓት ከተለያዩ የፍላንጅ ዓይነቶች ጋር በጠንካራ ሁኔታ ለማያያዝ እና አስተማማኝ ጥንካሬን ለመስጠት የሚያገለግል የጥራት መለኪያ።
✅
Epoxy Coated Ductile Iron Body (ዝገትና መበላሸትን የሚቋቋም ጠንካራ አካል)
✅
ጌር ኦፕሬተድ (Gear Operated Handwheel ለቀላል እና ለስላሳ አጠቃቀም)
✅
Lug Style Body (ለደህንነቱ
የተጠበቀ እና ፍሳሽ አልባ ግንኙነት የተመቸ)
✅
For Waterworks & Industry (ለኢንዱስትሪ፣ ለፓይፕ መስመር እና ለውሃ ማከሚያ የሚሆን)
📞
ለዋጋና ተጨማሪ መረጃ፦
⬇️
🔥
#ButterflyValve
#Industrial
#Piping
#Ethiopia
#Fyp
⬇️

September 07, 19:21
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

⛔
⛔
ሰበር ብስራት
⛔
⛔
ቅዳሜ እና እሁድ መስከረም
🥰
እና
🥰
በመስጂድ አል_ፉርቃን;
የስላብ ሙሌት ይደረጋል!!
🔜
🔙
ቅርብም ይሁን ሩቅ ያላችሁ……
…
የመስጁዱን ግንባታ መጠናቀቅ በጉጉት ለምትጠባበቁና በቻላችሁት መጠን የድጋፍ ተሳትፎ ለማድረግ ለምትጥሩ ወንድሞች ሁሉ በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ።
የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ መስከረም
🥰
እና
🥰
ሁላችንም በተለመደው የኸይረኞች መሽቀዳደሚያ ሜዳ ላይ እንገናኝ!!
🤌
እንደሚታወቀው……………
ቀናቶቹ በምናምን ምክንያት ስራ የማይኖርባቸው ቀናቶች በመሆናቸው፧
መልካም አጋጣሚውን በመጠቀም ሁላችሁም በሞራልና በነሻጣ እንድትገኙ የአክብሮት ጥሪያችን እናስተላልፋለን።
🥰
🥰
🥰
🥰
🥰
https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/20974

August 25, 09:06

መውሊድን ማክበር የሌለብን 50 ምክንያቶች
‼
=============================
(የእውነት ነቢያችንን ﷺ የምትወዱ ከሆነ ይህን አንብቡ!)
||
✍️
🖊
ክፍል 1፡ ከቁርኣንና ከሐዲሥ አንጻር፦
1️⃣
.ዲናችን ሙሉ ነው፦
አላህ በቁርኣኑ «ዛሬ ኃይማኖታችሁን ለእናንተ ሞላሁላችሁ፤ ጸጋዬንም በላያችሁ ላይ ፈጸምኩ» (አል-ማኢዳህ፡ 3) ብሏል። መውሊድ መልካም ተግባር ቢሆን ኖሮ ያኔውኑ በዲናችን ውስጥ በተካተተ ነበር።
3️⃣
. ነቢዩ ﷺ «በዚህ በዲናችን ውስጥ ከርሱ ያልሆነን አዲስ ነገር የፈጠረ ሥራው ተመላሽ (ውድቅ) ነው» ብለዋል (ቡኻሪና ሙስሊም)።
3️⃣
. ነቢዩ ﷺ በየሳምንቱ ኹጥባቸው ላይ «አደራችሁን በዲን ላይ አዳዲስ ፈጠራዎችን! ማንኛውም ፈጠራ ቢድዐ ነው፤ ማንኛውም ቢድዐ ደግሞ ጥመት ነው» እያሉ ያስጠነቅቁ ነበር።
4️⃣
.የፍቅር መለኪያ መከተል ብቻ ነው፡ አላህ የፍቅሩን ማረጋገጫ ያደረገው መከተልን (ኢቲባዕን) እንጂ አዲስ አከባበር መፍጠርን አይደለም፦ «አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና» (አሊ-ዒምራን፡ 31)።
5️⃣
.በዲን ውስጥ ድንበር ማለፍ ተከልክሏል። ነቢዩ ﷺ «ክርስቲያኖች የመርየምን ልጅ (ዒሳን) ድንበር አልፈው እንዳወደሱት እኔን ድንበር አልፋችሁ እንዳታወድሱኝ» ብለው አስጠንቅቀዋል (ቡኻሪ)።
6️⃣
.ነቢዩ ﷺ በ23 ዓመታት የነቢይነት ዘመናቸው አንድም ቀን የልደት ቀናቸውን በዓል አድርገው አክብረው ወይም እንዲከበር አዘው አያውቁም።
7️⃣
.የልደት ቀናቸውን ያሳለፉት በጾም ነበር፡ ነቢዩ ﷺ ስለ ሰኞ ቀን ጾም ተጠይቀው «… የተወለድኩበት ቀን ነው» ብለዋል (ሙስሊም)። ታዲያ ፍቅራቸው የሚገለጸው ሰኞን በመጾም ነው ወይስ በዓመት አንዴ በጭፈራና በድግስ?
8️⃣
. በዲን ህግ የማውጣት ስልጣን የአላህ ብቻ ነው፡ «ለእነርሱ አላህ ያልፈቀደውን ከኃይማኖት የደነገጉላቸው ተጋሪዎች አሉዋቸውን?» (አሽ-ሹራ፡ 21)።
9️⃣
.በኢስላም ማንኛውም የአምልኮ ተግባር (ዒባዳህ) ትክክለኛ የቁርኣን ወይም የሐዲሥ መረጃ ካልመጣበት በስተቀር ማድረግ አይፈቀድም። ለመውሊድ ደግሞ አንድም መረጃ የለም።
1️⃣
0️⃣
የኸሊፋዎችን መንገድ ያዙ ተብለናል። ነቢዩ (ኘለﷺ) «የእኔን ሱና እና ከእኔ በኋላ ያሉትን ቅን ኸሊፋዎች ሱንና አጥብቃችሁ ያዙ» ብለዋል፤ እነርሱ ደግሞ መውሊድን አላከበሩም።
🖊
ክፍል 2፡ ከሶሐቦች፣ ከታቢዒዮችና ከኢማሞች አንጻር (11–20)፦
1️⃣
1️⃣
አቡበክር ሲዲቅ ይህን በዓል አላከበሩትም። ከነቢያት ቀጥሎ በምድር ላይ ከማንም በላይ ነቢዩን ﷺ የሚወዱት አቡበክር መውሊድን አላከበሩም።
1️⃣
3️⃣
ዑመር ኢብኑል ኸጣብ አላከበሩትም፡ ዲንን ከፍ ያደረጉት ዑመር ለነቢዩ ልደት በዓል አላቋቋሙም።
1️⃣
3️⃣
ዑሥማን ኢብኑ ዐፋን  አላከበሩትም። ሁለት የነቢዩን ልጆች ያገቡት ዑሥማን ይህን አላደረጉም።
1️⃣
4️⃣
. ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ አላከበሩትም፡ የነቢዩ የቅርብ ቤተሰብ (አህለል በይት) መሪ የሆኑት ዐሊይም  አላከበሩትም።
1️⃣
5️⃣
. ሐሰንና ሑሰይን (ረ.ዐ) አላከበሩትም፡ የነቢዩ የልጅ ልጆችና የጀነት ወጣቶች አለቆች የሆኑት እነርሱ እንኳን የውድ አያታቸውን ልደት አላከበሩም።
1️⃣
6️⃣
. የሙእሚኖች እናቶች (የነቢዩ ሚስቶች) አላከበሩትም፡ ከማንም በላይ የነቢዩን የቤት ውስጥ ህይወት የሚያውቁት እናቶቻችን (ዐኢሻ፣ ኸዲጃ...) አላከበሩትም።
1️⃣
7️⃣
. ሶሐቦች ከእኛ በላይ ነቢዩን ይወዱ ነበር፡ እኛ ሶሐቦች ለነቢዩ ከነበራቸው ፍቅር አንድ ቅንጣት እንኳን አይኖረንም። እነርሱ ያልሰሩትን በጎ ስራ እኛ አገኘን ማለት ራስን ማታለል ነው።
1️⃣
8️⃣
. ምርጦቹ ሦስት ክፍለ ዘመናት (ኸይሩል ቁሩን)፡ ነቢዩ (ﷺ) «ከሁሉ በላጩ ትውልድ የእኔ ትውልድ ነው፤ ከዚያም የሚከተሏቸው...» ያሉላቸው ሦስቱ ትውልዶች መውሊድ የሚባል ነገር አያውቁም ነበር።
1️⃣
9️⃣
. አራቱ ታላላቅ መዝሃብ ኢማሞች አላከበሩትም፡ ኢማም አቡ ሐኒፋ፣ ኢማም ማሊክ፣ ኢማም ሻፊዒይ እና ኢማም አሕመድ መውሊድን አላከበሩም፤ በኪታቦቻቸውም አላዘዙም።
3️⃣
0️⃣
ኢማም ማሊክ «በኢስላም ውስጥ ነቢዩ ﷺ ያላደረጉትን አዲስ ነገር 'ጥሩ ነው' ብሎ የፈጠረ ሰው፣ ሙሐመድ ﷺ መልእክቱን አጓድለዋል (ከድተዋል) ብሎ እንደመሰከረ ይቆጠራል» ብለዋል።
🖊
ክፍል 3፡ ከሎጂክ አንጻር (21–30)
3️⃣
1️⃣
. ዒባዳ ነው ወይስ ባህል? መውሊድ አጅር የሚያስገኝ ዒባዳ ነው ካልክ መረጃ የለህም፤ ዒባዳ ካልሆነ ደግሞ ለምን አጅር ፍለጋ ትደክማለህ?
3️⃣
3️⃣
. ቀኑ የልደት ነው ወይስ የሞት? በታሪክ ተመራማሪዎች ዘንድ ነቢዩ (ﷺ) የተወለዱበት ቀን (ረቢዐል አወል 9፣ 12 ወይስ ሌላ?) አከራካሪ ነው። የሞቱበት ቀን ግን በእርግጠኝነት ረቢዐል አወል 12 ነው። ታዲያ በሞቱበት ቀን እንዴት ደስታ ይደረጋል?
3️⃣
3️⃣
. ፍቅር የ365 ቀናት እንጂ የአንድ ቀን አይደለም፡ ነቢዩን ማፍቀር በየሰከንዱ፣ በየቀኑ በሱናቸው በመመራት የሚገለጽ እንጂ በዓመት አንድ ቀን ጣፋጭ በመብላትና በመጨፈር የሚገለጽ አይደለም።
3️⃣
4️⃣
. ፍቅርን በዘፈቀደ መግለጽ አይቻልም፡ አንድ ሰው «ነቢዩን ስለምወድ የሱብሒን ሶላት 3 ረከዓ ላድርገው» ቢል ስሜቱ ጥሩ ቢሆንም ስራው ግን ውድቅ ነው። መውሊድም እንዲሁ ነው።
3️⃣
5️⃣
ነቢዩ ﷺ እኛን ከማንም በላይ ያውቁናል፤ የልደታቸው ቀን ማክበር መልካም ቢሆን ኖሮ አንድም ቀን እንኳን እንዲህ አድርጉ ብለው ባስተማሩን ነበር።
3️⃣
6️⃣
አላህ ለሙስሊሞች ሁለት ዓመታዊ በዓላትን (ዒደል ፊጥር እና ዒደል አድሓ) እንዲሁም አንድ ሳምንታዊ (ጁምዓን) ብቻ ሰጥቷል። አራተኛ በዓል መጨመር የሸሪዓን ድንበር መጣስ ነው።
3️⃣
7️⃣
. የነቢዩን ፈለግ መናቅ ይመስላል፡ «እነርሱ ያላደረጉትን እኔ አደርጋለሁ» ማለት በተዘዋዋሪ «እነርሱ ያላወቁትን መልካም ነገር እኔ አውቄያለሁ» የማለት ያህል ትዕቢት ነው።
3️⃣
8️⃣
. የስነ-ልቦና ማታለያ፡ መውሊድ የሚያከብሩ ሰዎች «ነቢዩን አፈቀርን፣ ግዴታችንን ተወጣን» የሚል የውሸት መንፈሳዊ እርካታ ስለሚሰጣቸው እውነተኛውን የሱና ህይወት ቸል እንዲሉ ያደርጋቸዋል።
3️⃣
9️⃣
. ቅድሚያ የሚሰጠው ተዛብቷል፡ ሱናቸውን በትክክል ከመተግበር ይልቅ በዓመት አንዴ በሚደረግ ስነ-ስርዓት ላይ ትኩረት ማድረግ የቅድሚያ ቅደም-ተከተል መዛባት ነው።
3️⃣
0️⃣
. የሌሎች ሃይማኖቶች ቅጅ ነው፡ ልደትን ማክበር የነቢያት መንገድ ሳይሆን የሮማውያንና የፋርሶች አረማዊ ባህል ነው።
🖊
ክፍል 4፡ ከታሪክ ምንጭ እና ከመጤነት አንጻር (31–40)
3️⃣
1️⃣
. መቼ ተጀመረ? መውሊድ የተጀመረው ነቢዩ ﷺ በሞቱ በ4ኛው ክፍለ ዘመን (ከ300 ዓመታት በኋላ) ነው።
3️⃣
3️⃣
. ማን ጀመረው? የጀመሩት አህለ-ሱንናዎች ሳይሆኑ፣ በኢስላም ታሪክ እጅግ የተወገዙት እና አፈንጋጮቹ ፋጢሚዮች (የኡበይዲያ መንግስት) ናቸው።
3️⃣
3️⃣
. ፋጢሚዮች ምን አይነት ሰዎች ነበሩ? የነቢዩን ሶሐቦች የሚረግሙ፣ የራሳቸውን ንጉሶች ልክ እንደ አምላክ የሚያዩ ከሃዲዎች ነበሩ። ታዲያ የነርሱን ፈሊጥ እንዴት እንከተላለን?
3️⃣
4️⃣
. የክርስቲያኖች አምሳያ (ተሸቡህ)፡ ፋጢሚዮች መውሊድን የፈጠሩት ክርስቲያኖች የኢየሱስን (ዒሳን) ልደት (ገና/Christmas) ሲያከብሩ አይተው እነሱን ለመምሰል ነው።
3️⃣
5️⃣
. ነቢዩ (ﷺ) ከካፊሮች መመሳሰልን ከልክለዋል፡ «የአንድን ሕዝብ ወግና ልማድ የተከተለ እርሱ ከእነርሱው ነው» ብለዋል (አቡ ዳዉድ)።
3️⃣
6️⃣
. የሌሎች መውሊዶች መፈጠር፡ የነቢዩ መውሊድ ሲፈቀድ፣ ቀጥሎ የሸይኾች፣ የደብተራዎችና የቃሊቾች መውሊድ ተፈጠረ፤ ሽርክም በሰፊው ተስፋፋ።
3️⃣
7️⃣
በአራቱ የሐዲሥ እና የፊቅህ መጻሕፍት ውስጥ «ኪታቡል መውሊድ» (የመውሊድ ምዕራፍ) የሚባል አንድም ነገር የለም።
3️⃣
8️⃣
. መከፋፈልን ፈጠረ፡ መውሊድ በሙስሊሙ ማህበረሰብ መካከል የልዩነት እና የጭቅጭቅ በር ከፈተ እንጂ አንድነትን አላመጣም።
3️⃣
9️⃣
. የቢድዐ ተፈጥሮ፡ አንድ ቢድዐ በህዝብ ዘንድ በነገሰ ቁጥር፣ በዚያው ልክ አንድ የነቢዩ ሱንና ይሞታል (ይረሳል)።
4️⃣
0️⃣
. የቀደምት ዑለማዎች ማውገዝ፡ እንደ ኢብኑ ተይሚያህ፣ ኢብኑል ቀይም፣ ኢማም አል-ሻጢቢ እና ሌሎችም ታላላቅ የኡማው ሊቃውንት መውሊድ ፈጠራ መሆኑን በመረጃ አረጋግጠዋል።
🖊
ክፍል 5፡ በውስጡ ካሉ አደጋዎችና ተጨባጭ ሁኔታዎች አንጻር (41–50)
4️⃣
1️⃣
. የሽርክ ስንኞች መኖር፡ በመውሊድ ላይ በሚቀሩ መንዙማዎችና ጽሑፎች (እንደ ቡርዳህ) ውስጥ ነቢዩን ከአላህ እኩል የሚያደርጉ፣ የሩቅ አዋቂ እና ሀጃ አውጪ የሚያደርጉ ግልጽ የሽርክ ቃላት ይገኛሉ።
4️⃣
3️⃣
. የወንዶችና የሴቶች ቅልቅል (ኢኽቲላጥ)፡ በአብዛኞቹ የመውሊድ ስፍራዎች ወንዶችና ሴቶች ተቀላቅለው ይጨፍራሉ፤ ይህም በሸሪዓ ክልክል ነው።
4️⃣
3️⃣
. የከበሮና የሙዚቃ መሳሪያዎች፡ መስጂዶችና አደባባዮች ለዝክር ሳይሆን ለከበሮ ድለቃና ለጭፈራ መዋላቸው የአምልኮን ክብር ያዋርዳል።
4️⃣
4️⃣
. የንብረት ብክነት፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለጣፋጭ፣ ለጫት እና ለድግስ ሲባክን፣ በርካታ የተራቡና የተቸገሩ ሙስሊሞች ግን የሚበሉት አጥተው ይማቅቃሉ።
4️⃣
5️⃣
. ሶላት መተው፡ ብዙ የመውሊድ ታዳሚዎች ሌሊቱን ሲጨፍሩ አድረው የሱብሂን ፈርድ ሶላት ያመልጣቸዋል።
4️⃣
6️⃣
. ጫት እና አደንዛዥ እጾች፡ በአንዳንድ አካባቢዎች መውሊድ ያለ ጫትና ጭስ አይታሰብም፤ ይህም ራስን መበከል ነው።
4️⃣
7️⃣
. የሐውድ (የወንዙ) አደጋ፡ በቂያማ ቀን ነቢዩ (ﷺ) ከሐውዳቸው ውሃ ሊያጠጡን ሲሉ መላእክት አንዳንድ ሰዎችን ያባርሯቸዋል። ነቢዩም «እነሱ እኮ ተከታዮቼ ናቸው» ሲሉ መላእክቱ «ከአንተ በኋላ በዲንህ ላይ ምን እንደፈጠሩ አታውቅም» ይሏቸዋል (ቡኻሪ)። በቢድዐ ምክንያት ከነቢዩ እጅ መጠጣት እንዳንከለከል አንፈራምን?
4️⃣
8️⃣
. «ሰዎችን እንመግባለን» የሚለው ሰበብ፡ ምስኪኖችን መመገብ ታላቅ ዒባዳ ነው፤ ነገር ግን ይህ በማንኛውም ቀን በሱንና መንገድ መደረግ ያለበት እንጂ ካልተደነገገ በዓል ጋር ሊያያዝ አይገባም።
4️⃣
9️⃣
. አላህ ፊት ስንቆም ምን እንመልሳለን? ነገ አላህ ፊት ቀርበህ «ይህን የመውሊድ በዓል እንድታከብር ከቁርኣንና ከነቢዬ ምን ማስረጃ አገኘህ
❓
» ተብለህ ስትጠየቅ የምትሰጠው መልስ የለህም!
5️⃣
0️⃣
. እውነተኛው ፍቅር የትኛው ነው? ነቢዩን
🩷
በእውነት የሚወድ ሰው እርሳቸው ያዘዙትን ይሰራል፣ የከለከሉትን ይተዋል፣ ሱንናቸውን ያስፋፋል፤ ከፈጠራ (ቢድዐ) ሁሉ ራሱን ያርቃል።
ውድ ወንድሜና እህቴ ሆይ!
ልብህን ጠይቅ፦
ነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) ዛሬ በአይናችን ፊት ቢገኙ ኖሮ፣ እሳቸውም ሆኑ ምርጥ ባልደረቦቻቸው ፈጽመው የማያውቁትን ይህን በዓል እንድናከብር ይፈቅዱልን ነበር? ወይስ «ይህ ፈጠራ ነው ተዉት!» ብለው ይቆጡን ነበር?
መልሱ ግልጽ ነው። እውነተኛ ፍቅር መከተል እንጂ መፍጠር አይደለም!
ስለዚህ ዛሬውኑ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ወስነህ/ሽ የመውሊድ እቅድህን ሰርዝ፤ ይልቁንም ያንን ቀን ነቢዩ ባዘዙት መሠረት በጾም፣ ቁርኣን በማንበብ፣ ሱናቸውን በማጥናት እና በእርሳቸው ላይ ሶለዋት በማውረድ እውነተኛውን የፍቅር መንገድ ምረጥ!
አላህ እውነተኛውን የነቢዩን ﷺ ፈለግ የምንከተል ያድርገን።
||
t.me/MuradTadesse

August 24, 14:41
Файлы недоступны
2
Открыть в Telegram

📮
መውሊድ ቢድዓ ነው!
🔗
t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/20936

August 22, 04:51
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram