Выберите регион
и язык интерфейса
Покажем актуальные для региона
Telegram-каналы и возможности
Регион
avatar

ፍቅር እስከ ጀነት | ራማስ አል ሀናኒ

fkr_eske_jenet
ሀላሌ ነሺ አሉ !! ከወንዶች ሁሉ አይንሺ ለኔ አድልቶ ልብሽ ከወደደኝ ሁሉን ነገር ትቶ ወላጅም ከሰጠ ሽማግሌ መጥቶ ኒካህ ከታሰረ ሁሉም ተመቻችቶ ልቤም ይረጋጋል ያሰብኩት ተሟልቶ፡፡ 📝 ወንድማችሁ ራማስ አልሀናኒ 🍃 ለአስታያየትዎ ☞ @Ramas_Alhanani_bot
Подписчики
29 901
24 часа
35
30 дней
1 054
Просмотры
2 555
ER
8,54%
Посты (30д)
338
Символов в посте
570
Инсайты от анализа ИИ по постам канала
Категория канала
Религия и духовность
Пол аудитории
Женский
Возраст аудитории
25-34
Финансовый статус аудитории
Средний
Профессии аудитории
Прочие
Краткое описание
September 25, 04:11
Файлы недоступны
1
1
Открыть в Telegram

የዱንያ እውነታ
ይህች አለም አላህ ሊፈትነንና ሊሞክረን የሰራት ጊዜያዊ ማረፊያ እንጂ የዘላለም መኖሪያችን አይደለችም። ከህፃንነት እስከ እርጅና ከፅንስ እስከ መቃብር ያለው የህይወት ሂደታችን በቅጽበት እንደምትነፍስ ነፋስ ፈጣን ነው። እስኪ አስተውል የህይወታችን የልብ ምትና የአተነፋፈሳችን ቁጥር ሙሉ በሙሉ በአላህ  ችሎታና እጅ ስር ያለ ሆኖ ሳለ በዱንያ ውበትና በጊዜያዊ ጥቅም ተታለን ወደ ፈጣሪያችን የምንመለስበትን ታላቅ ቀን እንዴት እንረሳዋለን? አላህ በቁርዓኑ
«إنَّ إلَى رَبِّكَ الرُّجْعَى»
(በእርግጥ ወደ ጌታህ መመለስ አለ)
ሲል ያስጠነቀቀን የትም ብንሄድና ምንም ያህል ብንኖር የመጨረሻ መዳረሻችን እሱ ዘንድ መሆኑን ልባችን እንዲያውቀውና እንዲነቃ ነው።
ስለሆነም ከዚህ ታላቅ ማሳሰቢያ የምንወስደው ትምህርት የሞት ጥሪ ሳይመጣ ። ሰዓታችን ሳይጠናቀቅ ዛሬውኑ ወደ አላህ በመመለስ ታላቁን ስንቅ ልንይዝ ይገባል። ትዕቢትንና የአለምን አላፊ ፍላጎት ወደ ጎን በመተው  ልባችንን በተውሂድና በአላህ ፍርሃት፣ እጃችንን ደግሞ በመልካም ስራ እና በቅንነት ልናስጌጠው ይገባል።
እናም ወደ አላህ መመለስን ለነገ አንበል! ምክንያቱም የመጨረሻዋ ቀን መቼ እንደምትወጣ የምናውቀው ነገር የለምና , ከጌታችን ጋር ያለንን ግንኙነት በተውበት እና በመልካም ስነ ምግባር እናድስ።
👈
ራማስ አል ሀናኒ
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

September 25, 04:11
Файлы недоступны
1
1
Открыть в Telegram

September 23, 18:15
Файлы недоступны
1
1
Открыть в Telegram

✅
ከጭንቀት በኋላ እፎይታ አለ!
በዚህች የፈተና ዓለም ውስጥ ስትኖር አንድ ትልቅ እውነት ሁልጊዜ በልብህ ውስጥ ሊታተም ይገባል እሱም፦ ምንም ነገር ባለበት አይቀጥልም  የሚለው ነው። ሕይወትህ ዛሬ በጭንቀት ጥብብ ቢልህ  ነገ እፎይታው መምጣቱ አይቀርም ይህ የፈጣሪ ህግ ነው ።
አሏህ (ﷻ) በቁርዓን ውስጥ ሁለት ጊዜ ደጋግሞ እንዲህ በማለት ቃል ገብቶልናል፦
فَإِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا ۝ إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ  يُسْرًا
ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት (እፎይታ) አለ ከችግር ጋር ምቾት (እፎይታ) በእርግጥ አለ።
ዛሬ በእንባ የታጠበው ጉንጭህ ነገ በፈገግታ መድመቁ አይቀርም። የነብዩ ያዕቁብ ዐለይሂ ሰላም ዓይኖች በልጃቸው በነብዩ ዩሱፍ ናፍቆትና ለቅሶ ቢጠፉም አሏህ (ﷻ) ግን ከዓመታት በኋላ ልጃቸውንም መለሰላቸው ዓይናቸውንም አበራላቸው።
ያንተም ለቅሶ ጊዜያዊ ነው አብሽር የአሏህ (ﷻ) እዝነት ሲመጣ  ለምን እንዳለቀስክ እንኳ ትረሳዋለህ። ዛሬ አካልህ በህመም ቢሰቃይና ተስፋ ብትቆርጥ እንኳ ፈዋሹ አሏህ (ﷻ) መሆኑን አትዘንጋ።
ነብዩ አዩብ ዐለይሂ ሰላም ለዓመታት በበሽታ ተፈትነው መጨረሻ ላይ አሏህ (ﷻ) ሙሉ ጤናቸውንና ሀብታቸውን መለሰላቸው። ህመም የወንጀል ማጠቢያ ነው ፈውስ ደግሞ የአሏህ (ﷻ) ስጦታ ነው።
በስራ እጥረት ብትንገላታ በሰው ፊት ብትዋረድና በኪስህ ምንም ባይኖር እንኳ ተስፋ አትቁረጥ። ሪዝቅህ ያለው በሰው እጅ ሳይሆን በ አሏህ (ﷻ)እጅ ነው። ዛሬ የምታየው መከራ ነገ ለምታገኘው ትልቅ በረካ መሸጋገሪያ ድልድይ ነው። የማያልቅ ሲሳይ ያለው ረዛቁ በአንድ ጀምበር ሕይወትህን ሊቀይረው ይችላል።
ነብዩ ዩሱፍ ዐለይሂ ሰላም ያለምንም ጥፋታቸው ለዓመታት በእስር ቤት ተገፍተው ነበር። ነገር ግን የአሏህ (ﷻ) ህግ መጣና ከእስር ወጥተው የግብፅ ንጉስ ሆኑ። ማንኛውም አይነት እስር የአካልም ይሁን የጭንቀት እስር መጨረሻው መፈታት ነው።
ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ እንደምትወጣው ሁሉ ችግርህም አልፎ ደስታህ መምጣቱ አይቀሬ ነው። ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ድል በትዕግስት ውስጥ ነው እፎይታም ከጭንቀት ጋር ነው ከችግርም ጋር ምቾት አለ።
ስለዚህ ዛሬ ባለህበት ሁኔታ አትዘን። ነገ ሌላ ቀን ነው ነገ አዲስ ተስፋ ነው ነገ የአሏህ (ﷻ) እዝነት በር የሚከፈትበት ቀን ነው። ብቻ አንተ በጌታህ ላይ ያለህን ተወኩል አታጥፋ!
👈
ወንድማችሁ ራማስ
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

September 23, 18:15
Файлы недоступны
1
1
Открыть в Telegram

September 23, 17:25

ግ ጥ ም
➻➻➻➻➻➻➻➻➻
ሁሉም ባዶ
ሁሉም ዜሮ
ሁሉም መና
➪➪➪➪➪➪➪➪
ሀብታም ቢሆን ዱንያው አምሮ
ዶክተር ቢሆን ተመራምሮ
ቆንጆ ሴትጋ ቢኖር አብሮ
ልጀች ቢወልድ ትዳር ሰምሮ
ንጉሥ ቢሆን ምድርን ዞሮ
ያለ ኢስላም ሁሉም ዜሮ
" " " " "
ምን ቢለፋ ኽይርን ወዶ
ቀኑን ቢፆም ለይሉን ሰግዶ
ሁሉን ቀድሞ ቢጓዝ ማልዶ
ሀጅ ቢያደርግ መካ ሄዶ
ያለ ተውሂድ ሁሉም ባዶ
" " " " "
ሌትቀን ለፍቶ ምን ቢፅና
ቢኖረውም ቅን ልቦና
ንያው አድጎ ምን ቢቃና
ቢደጋገም በምርቃና
ቢያሳምረው እንደገና
ያለ ሱና ሁሉም መና
➞➞➞➞➞➞➞➞➞,
= t.me/FKR_ESKE_JENET

September 23, 17:25
Файлы недоступны
1
1
Открыть в Telegram

September 21, 15:21
Файлы недоступны
1
1
Открыть в Telegram

September 21, 15:21
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

የሰዎችን ጥፋት እንደ ጌታ ሆናቹ የራሳችሁን ጥፋት እንደ ባርያ ሆናቹ አትመልከቱ በወንጀል የተፈተኑ ሰዎችን ስታዩ እዘኑላቸው። አሏህ ከዛ ስለጠበቃችሁም አመስግኑት !!!
ኢማሙ ማሊክ
📡
t.me/FKR_ESKE_JENET

September 20, 12:44
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

ካለፈ
በጊዜው ነዉ እንጂ ይቅርታ እሚጠግን ፣
በወቅቱ ነዉ እንጂ መፀፀት የሚያድን ።
በዚያዉ ቅፅበት እንጂ ፀፀት ያለው ጉልበት፣
እንኳንም ይቅርታ
መድኃኒት መርዝ ነዉ ጊዜው ካለፈበት ።
╭┈─────── ೄ
🌹
ྀ࿐ ˊˎ-
=
t.me/FKR_ESKE_JENET

September 20, 12:44
Файлы недоступны
1
1
Открыть в Telegram