
🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸
☝️
የአላህ አላህነቱን
ተመልከት!!
አላህ
በተከበረው ቃሉ ስለ ደጋግ ባሮቹ፣ ስለ ወዳጆቹ፣ ስለ ምርጦቹ ሲናገር አንድም ቦታ ላይ
"ከስህተት የተጠበቁ ፍጹም ናቸው"
ብሎ አይገልፃቸውም።
{አላህ ባዘዛቸው ነገር አያምፁትም፤ የታዘዙትን ይሰራሉ}
ብሎ ፍጹማዊነት የሰጣቸው ለመላኢካዎች ብቻ ነው። ከሰው ልጆች ሆነው ደጋግ ስለሆኑ ባሮቹ ሲናገር ግን
{ከስህተታቸው ምህረት የሚጠይቁ፤ በስህተታቸው ላይ የማይዘወትሩ}
እያለ በዚህ ተመሳሳይ ገለፃ ይገልፃቸዋል።
አላህ………
ከአንተ ፍጹማዊነትን አይሻም፤
ልትሆን ስለማትችል።
አላህ………
ከአንተ የሚፈልገው ከወንጀልህ ተመልሰህ ምህረት እንድትጠይቀው ነው!!
ተመልከት……………
እያንዳንዱ ሀገር ላይ ተደንግገው የተቀመጡ ህገመንግስታዊ ስርዓቶች ብትመለከት፧ የሆነ ወንጀል ይጠቀስና የዝያ ወንጀል ፈፃሚ ቅጣቱ ቀጥሎ ይጠቀሳል። ሁሌም አንድ ወንጀለኛ ከተያዘ ቀጥሎ የሚጠብቀው
[ህጋዊም ይሁን ህገ_ወጥ: ፍትሓዊም ይሁን ኢ_ፍትሐዊ]
ቅጣት ነው።
እያንዳንዱ ቁርኣን ውስጥ እና ሐዲስ ውስጥ የተጠቀሱ የወንጀል ዓይነቶች ብታይ ብትመለከት ግን; ከትልቁ ኩፍርና ሽርክ ጀምሮ ለእያንዳንዱ
አላህ
ለሚታመፅበት ወንጀል የምህረት በር ተከፍቶለታል። የትኛውንም
አላህን
የሚያስቆጣ ወንጀል የፈፀመ አካል ወደ
አላህ
ከተመለሰና ምህረት ከጠየቀ
አላህ
ይምረዋል።
ቀጣዩን አንቀፅ ተመልከት፦
📖
{قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ}
{እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን ሁሉ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና በላቸው፡፡}
[አል_ዙምር:⁵³]
አላህ
በዚህ በተከበረ አንቀጽ ላይ እየተናገረ ያለው ስለ ሰጋጆች ወይም ስለ ጿሚዎች ወይም ስለ ደጋጎች አይደለም። አንድ… ሁለት… ሦሥት… ምናምን ሳይሆን በወንጀል ተጨማልቀው ወንጀላቸው ከመተለቁና ከመብዛቱ
"ነፍሳቸው ላይ ድንበር እስከማለፍ"
ስላደረሳቸው አካሎች ነው።
ሆኖም…………
"እናንተ ሙጅሪሞች፣ አመፀኞች፣ ጥጋበኞች" ወይም በመሳሰሉ ቃላቶች ሳይሆን;
የትኛውም ሙእሚን ቢጠራበት ሊያስደስተውና ሊኮራበት በሚችል ውብ ጥሪ
{ባሮቼ ሆይ!!}
እያለ ይጠራቸዋል።
ምክንያቱም………
እሱ አላህ ነው!! እሱ አዛኝ ነው!!
ሌላው የሚገርመው…………
አላህ ሲቀጣህ በፍትሕ ነው፤ ሲምርህ ደግሞ በችሮታው ነው!!
አንድ ባሪያ ከሰራው ወንጀል ምህረት ሳይጠይቅ
አላህን
ቢገናኝና
አላህም
በዚህ ወንጀሉ ሊቀጣው ቢፈልግ;
የሚሰጠው ቅጣት ከወንጀሉ ተመሳሳይና ተመጣጣኝ የሆነ ነው!!
📖
{وَالَّذِينَ كَسَبُوا السَّيِّئَاتِ جَزَاءُ سَيِّئَةٍ بِمِثْلِهَا}
{ለእነዚያም ኃጢአቶችን ለሠሩት የኃጢኣቲቱ ቅጣት በብጤዋ አለችላቸው፡፡}
[ዩኑስ:²⁷]
ከሰራው ስህተት ወደ
አላህ
ተመልሶ፤
አላህን
የሚያስወደድ ስራ ሰርቶ
አላህን
ለተገናኘ ባሪያ ግን አላህ ሲመነዳው በስራው እኩኩል ሳይሆን አጥፍ ድርብ አርጎ በብዙ አብዝቶና አሳምሮ ነው።
📖
{مَّثَلُ الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ كَمَثَلِ حَبَّةٍ أَنبَتَتْ سَبْعَ سَنَابِلَ فِي كُلِّ سُنبُلَةٍ مِّائَةُ حَبَّةٍ ۗ وَاللَّهُ يُضَاعِفُ لِمَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ}
{የእነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ሰዎች (የልግስናው) ምሳሌ በየዘለላው ሁሉ መቶ ፍሬ ያለባቸውን ሰባት ዘለላዎች እንደ አበቀለች አንዲት ፍሬ ብጤ ነው፡፡ አላህም ለሚሻው ሰው (ከዚህ በላይ) ያነባብራል፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡}
[አል_በቀራ:²⁶¹]
አንዲት መልካም ስራ እስከ ሰባት መቶ ትባዛለች።
አላህ
ለፈለገው ከዚህም በላይ ይጨምርለታል።
ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ ሁለቱም በአንዲት አንቀጽ ይገልፃቸዋል፦
📖
{مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ}
{በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡}
[አንዓም:¹⁶⁰]
እንዲሁም…………
አንድ ባሪያ ለብዙ ጊዜያት ወንጀል ላይ የቆየ ሆኖ በስተመጨረሻም ወደ
አላህ
መመለስ ቢፈልግ…
"አላህ
ሊምርህ ከፈለክ፧ ወንጀል ላይ በቆየኸው ልክ ተውበት ላይ መቆየት አለብህ"
አይባልም። ዐስር፣ ሀያ፣ ሀያ አምስት ዓመታት በወንጀል የኖረ ሰው ወደ
አላህ
ተመልሶ ምህረት እንዲደረግለት ከፈለግ፧ ያንን ሁሉ ዓመት የሰራው ወንጀል በአንዲት ቀን, በአንዲት ሰዓት, ሳይባል በአንዲት ቅፅበት
አላህ
ሁሉንም ይምረዋል።
ምክንያቱም፦
አላህ ከአንተ የሚፈልገው ወደ እሱ የተዘነበለ ንፁህ ልብ ብቻ ነው!!
አንተ ብቻ ወደ አላህ ተመለስ…… ሁሉም ነገር ወደ አንተ ይመለሳል!!
https://t.me/hamdquante
✍
ውበቱ የሚጀምረው ከስሙ ነው!!
🕋
ضيوف الرحمن የአል_ረሕማን እንግዶች
ሲጀመር………
በቋንቋም ይሁን በየትኛውም ማህበረሰብ ተለምዶ
"እንግዳ"
የሚለው ቃል የተከበረና የተዋበ ማዕረግ ያለው መጠሪያ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አንድ እንግዳ በእንግድነቱ የተከበረ ከመሆኑም ጋ………
እንግድነቱ የተቀበለው ወይም ለእንግድነት የጋበዘው አካል ባለው ደረጃ ልክ የእንግዳው ክብርና ደረጃ ከፍ ይላል።
ለዚህም ነው ሰዎች የሆነን እንግዳ መጥራት ወይም መጋበዝ ሲፈልጉ: ቀጥታ ራሳቸው ከመጥራት ይልቅ "እከሌ ጠርቶሃል" ብለው የሚያስልኩት። መልእክተኛውም ቢሆን "ዐለቃዬ ጋብዞሃል" ብሎ ያስተላልፋል እንጂ "ጋብዤሃለሁ" አይልም።
ምክንያቱም፦
ተጋባዡ እንግዳ በሚጋብዘው አካል ደረጃ ልክ ደረጃውን ክብሩን ስለሚወሰን ነው።
ለምሳሌ………
የሀገሪቷ የግብርና ሚኒስቴር ጥሪ አድርጎላቸው የመጡ እንግዶችና የሀገሪቷ ፕሬዝዳንት ጥሪ አድርገውላቸው የመጡ እንግዶች የሚያገኙት ክብር ተመሳሳይ አይደለም። ተጋባዡ እንግዳ ተመሳሳይ ሰው ሆኖ እንኳ የሆነ ሰዓት የገቢዎች ሚኒስቴር ሌላ ጊዜ ደግሞ የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስቴር እንግዳ አድርገው ቢያቀርቡት የሚያገኘው ክብር ተመሳሳይ አይደለም። ተጋባዡ አንድ ሰው ሆኖም የሚጋብዙት አካሎች ስለተለያዩ በእነርሱ መለያየት ምክንያት እሱ የሚያገኘው ክብር ይለያያል።
የሀገራችን ልዑካኖች አሜሪካ ጠርታቸው ቢሄዱና ኬንያ ጠርታቸው ቢሄዱ የሚያገኙት ክብር እኩል አይደለም።
አሁን መልዕክቱ የተገለጠላችሁ ይመስለኛል!!
የምድር የሰማይ ፈጣሪና አስተናባሪ፤ የሁሉም መመኪያና መጠጊያ፤ የትኛውም ነገር ሁን በማለቱ ብቻ የሚሆንለት ልዕለ ሀያሉ አላህ እንግዳ አድርጎ ሲጠራህ፧ ክብርህ ምንኛ የተለቀ ሊሆን ነው??!!
🕋
ضيوف الرحمن የአል_ረሕማን እንግዶች
ሲባል ውበቱ የሚጎላው ለዚህ ነው። አላህ ጠርቶህ፣ አላህ መርጦህ፣ አላህ ጋብዞህ ወደቤቱ ሲጠራህና ጥሪውን ተቀብለህ ስትገኝ………… ከዚህ የበለጠ ክብር የለም!!
🤲
አላህ ደግሞ ደጋግሞ ይወፍቀን
🤲
https://t.me/hamdquante
✍
መጥቶ ስለ አንዱ ክፋት ሲነግርህ……
🤲
አላህ ለእሱም ለእኛም ያስተካክለን
🤲
በለው። ከዚህ ሌላ አትጨምር።
https://t.me/hamdquante
✍
ዐላማህ እንዳይሳካ ከፈለክ፦
👇
👉
ለምትገናኛቸው ሁሉ ስለ ዕቅድህ ንገራቸው¡¡
https://t.me/hamdquante
📖
{لَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ فِي كَبَدٍ}
{ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ሆኖ ፈጠርነው፡፡}
ከከፊል ሰለፎች ተይዞ በተላለፈው፦
አላህ
ከፈጠራቸው ፍጥረታቶች ሁሉ እንደ የሰው ልጅ መከራ የሚበዛበት ፉጡር የለም፤ ከመሆኑም ጋ ከፍጥረታት ሁሉ ደካማው እሱ ነው!!
/ኢማሙ ቁርጡብይ/
https://t.me/hamdquante
✍
በየትኛውም ዓይነት መንሐጅ፤
በየትኛውም የዕውቀት ደረጃ፤
በየትኛውም ሀገር ላይ ያለ ሙስሊም ሁሉ…………
ከላይ የተቀመጡ ቪዲዮዎች ሲመለከት ልቡ በአንድ ቅፅበት ወደ አንዲት ቦታ ይመታል!!
🤲
اللهم عمرة
🤲
🕋
🕋
🕋
🕋
🕋
🕋
🕋
🕋
🕋
🕋
https://t.me/hamdquante
✍
ሴት ልጅ ደብቃ ልቲዘው የምትችለው ብቸኛው ሚስጥር;
ዕድሜዋ ነው
አሉ
።
https://t.me/hamdquante
✍
እቺ ዱንያ………
💫
ዩሱፍ
ﷺ ተሽጦባታል፤
💫
ኑኅ
ﷺ ተስተባብሎባታል፤
💫
ሙሳ
ﷺ
በደጋሚነት ተወርፎባታል፤
💫
ሙሐመድ
ﷺ
በድንጋይ ተወግሮባታል፤
💫
ኢብራሂም
ﷺ
ወደ እሳት ተወርውሮባታል፤
ከዚህ ሁሉ በኋላ ለአንተ እንዴት ምቹ ልትሆን ትችላለች ከቶ???
የዱንያ ሐቂቃዋ ማለት፦
እንደ አንድ ሰው ነው, ከዛፍ ጥላ ስር ተኛ: በህልሙ የሚወደው ነገር አየ: ወድያው ነቃ: ቦታውን ትቶ ሄደ።
https://t.me/hamdquante
🇺🇸
የአሜሪካ ወታደር………
ቁሞ የሚሄድበት የጀርባ አጥንት ካለው በቂው ነው: የሚያስብበት አእምሮ አያስፈልገውም።
/አልበርት አንስቴይን/
የአሜሪካዊያኖች
ድድብና
ና
ጭካኔ
የገለፀባት ድንቅ ዐረፍተነገር ናት።
https://t.me/hamdquante