Выберите регион
и язык интерфейса
Покажем актуальные для региона
Telegram-каналы и возможности
Регион
avatar

ሒጃብ ነው ውበቴ

hijabnewwebta
السلام عليكم وراحمة الله وبركاته ውድ የቻናላችን ተከታታዮች በአላህ ፍቃድ * ተቀርተው ያለቁ ኪታቦች * አስተማሪ ታሪኮች * ዲናዊ ትምርቶች * ምክሮች * ደዐዋወች ይቀርብበታል ኢንሻአላህ ማንኛውንም አስተያየት ለማድረስ @Khewlibot አላህ ዱኒያዬንም አሄራዬንም እንዲያሳምርልኝ ዱዐ አርጉልኝ 👇 👇 👇 Join t.me/HijabNewWebta
Подписчики
11 089
24 часа
-14
30 дней
-273
Просмотры
1 760
ER
15,87%
Посты (30д)
1
Символов в посте
473
Инсайты от анализа ИИ по постам канала
Категория канала
Религия и духовность
Пол аудитории
Женский
Возраст аудитории
25-34
Финансовый статус аудитории
Средний
Профессии аудитории
Языковое обучение
Краткое описание
October 27, 16:59

እስኪ አንድ መጽሐፍ ላስተዋውቃችሁ…
አሁን እያነበብኩት ያለሁት ይህን መጽሐፍ ነው። እውነት ለመናገር፣ መጽሐፉን እያነበብኩ ስሄድ የበለጠ ለማንበብ እንድጓጓ እያደረገኝ ነው።
ስለ ረሱል ﷺ የተጻፈ ብቻ አይደለም…
የረሱል ﷺ ስነ-ምግባርና ባህሪ
አስተምህሮታቸው
ስለእሳቸው የተነገሩ የተዛቡ አስተሳሰቦችና ምላሾቻቸው
ስለእሳቸው ﷺ የተነገሩ አስገራሚ ትንቢቶች
እና ከእኛ ዘመን ጋር የሚያገናኙ ጉዳዮችንም ይዳስሳል።
የሚገርመው ደግሞ አቀራረቡ ነው…
በጣም ሳቢ፣ ቀላል እና አንድ ገጽ ካነበብክ ቀጣዩን ገጽ ለማየት የሚያጓጓ አዘገጃጀት ነው።
እናንተም ስለ ረሱል ﷺ ማወቅ፣ መማር እና ማንበብ የምትወዱ ከሆነ፣ ይህን መጽሐፍ እንድታዩት  እጋብዛችኋለሁ።
📌
መጽሐፉ፦ [ፍፁም ሰው ፍፁም ነብይ]
✍️
ደራሲ፦ [ኡስማን ሙስጠፋ]
📞
0912027023/0921390122
Telegram
@Usmanoman
Telegram channel
👇
https://t.me/usmanic_psychology

September 14, 07:02
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

✨
ልዩ ውበት ከላቀ ጥራት ጋር ከ በድር ጅልባብ!
✨
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
🌸
🛍️
አዳዲስ ምርቶች ገብተዋል!
🤎
አባያ በስትረች – ከሳይዝ 52 እስከ 60
📐
ሙሉ ጅልባብ – የተለያዩ ዲዛይንና ሳይዝ
🖤
ኒቃብ ታሳሪ – ከ90 ሴ.ሜ እስከ 1.50 ሜትር
🖤
ባለ ኮፍያ ኒቃብ – ከ1.15 ሜትር እስከ 1.50 ሜትር (በላስቲክ )
🖤
ባለ ኪማር ኒቃብ – በሁሉም ሳይዝ
🧦
ጥራት ያላቸው ካልሲዎችና ጓንቶች
💎
ጥራት ያለው ጨርቅ፣ ውብ ዲዛይንና ጥሩ ፊኒሽንግ! ከ በድር ጅልባብ
📦
በችርቻሮም በጅምላም እንሸጣለን።
🚚
ለክፍለ ሀገር ደንበኞቻችን እናደርሳለን!
📍
አድራሻ: ቤተል አደባባይ ፊትለፊት፣ ከዑስሚ ዳቦ ቤት አጠገብ፣ ፍሌቨር ካፌ ያለበት ሕንፃ 1ኛ ፎቅ
❌
እጃችን ላይ የሌለ እቃ ፈጽሞ ፖስት አናደርግም!
📞
0960975353
🎵
TikTok:
@bedrjilbab
📲
Telegram:
@BEDRjilbab
🖤
በድር ጅልባብ – ጥራትና ውበት!
#BEDR_JILBAB1
#ጅልባብ
#አባያ
#ኒቃብ
#ካልሲ
#ጓንት
#ቤተል
#ኢስላማዊ_አልባሳት

September 14, 07:02
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

September 05, 13:01

ኒካህ በሴት ልጅ ቢሆን ኖሮ
➢ በሀይድ ወቅት የመፈታት እድልህ 50%
➢ በእርግዝና ወቅት የመፈታት እድልህ 90%
➢ በምጥ ወቅት የመፈታት እድልህ 95%
➢ በሀብት የምትበልጥህ ከሆ ደሞ ስትልክህ
መልስ የምትሰጣት ከሆነ የመፈታት እድልህ 100% ነበር የሚሆነው
ዝም ብለህ አመስግን
🙌

September 03, 17:47
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

ነስር የቁርአን ሒፍዝና ኢስላማዊ ተርቢያ ማዕከል
ልጅዎን በቁርአን ብርሃን ለማነጽ፣ የሸሪዐ እውቀቶችን ለማስጨበጥ እና ከቴክኖሎጂ እውቀት ጋር የሚራመድ መልካም ትውልድ አድርገው ለማሳደግ አስበዋል?
​
ነስር የቁርአን ሒፍዝና ኢስላማዊ ተርቢያ ማዕከል
ልምድ ባላቸው ኡስታዞች
የአዳሪ ሒፍዝ ፕሮግራም
አዘጋጅቶ ተማሪዎችን በመመዝገብ ላይ ይገኛል
​
📌
​
የሚሰጡ ትምህርቶች
• የቁርኣን ሒፍዝ እና ተጅዊድ
• የአቂዳ፣ የሐዲስ፣ የፊቅህ እና የተርቢያህ ደርሶች
• የኮምፒውተር መሰረታዊ ስልጠና
​
📌
የመግቢያ መስፈርቶች
•
እድሜው ከ14 – 20 አመት የሆነ
• ቁርዓንን አስተካክሎ ማንበብ የሚችል
• ከ3 ጁዝ በላይ ቁርአን የሐፈዘ
• ​የመግቢያ ፈተናውን ማለፍ የሚችል
• ​ከማንኛውም ተላላፊ በሽታ ነፃ የሆነ
• ሀገራዊ ምግቦችን ሳይመርጥ መመገብ የሚችል
• ​ለመርከዙ ህግና ደንቦች ሙሉ በሙሉ ተገዢ የሆነ
• ​ቁርአን ለመሐፈዝ ከፍተኛ ፍላጎትና ቁርጠኝነት ያለው
• ​የመርከዙን ወርሃዊ ክፍያ መክፈል የሚችል
​
የምዝገባ ጊዜ፦
ከነሐሴ 25 እስከ መስከረም 5/2019 ዓ.ል
⚠️
ማሳሰቢያ፦
የቦታችን መጠን ውስን በመሆኑ ፈጥነው በመመዝገብ የእድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ
​
📌
​
አድራሻ፦
አዲስ አበባ ቃሊቲ
📞
ለበለጠ መረጃ
0908113344

August 30, 20:13
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

ሒጃብ የለበሰች ሴትና ተራቁታ እርቃኗን የምትሔድ ሴት ልዩነታቸው ልክእንደነዚህናቸው።

August 27, 09:18

ልቤ ሆይ!!
ልቤ ሆይ ልብ አድርግ ለመልካሙ ትጋ ከክፋት ተገታ
ምላሴ ሆይ እረፍ ጦስህ ያስፈራኛል በጧትም በማታ
እጄ ሆይ ተመከር "እጄን በ’ጄ" እንዳልል በሚያስጨንቅ ቦታ
እግሬ እግር አታብዛ ታዋርደኛለህ በጭንቁ ቀን ለታ
አዋጅ ሰምቻለሁ እጅግ የሚያስፈራ ከሰማዩ ጌታ።
(يَوْمَ تَشْهَدُ عَلَيْهِمْ أَلْسِنَتُهُمْ وَأَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُمْ بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ) [النور 24]
"በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሰሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን (ከባድ ቅጣት አላቸው)፡፡"  [አንኑር: 24]
©
ኢብኑ ሙነወር
T.me/HijabNewWebta

August 23, 09:28
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

የወንድ ድንግልና...
~
ዛሬ ላይ ስለ ትዳር ስታስብ የጭንቀት ጥላ የሚያጠልባት፣ በትላንት የጥቃት ጠባሳ ወይም በወጣትነት ስህተት ምክንያት የውስጥ ስብራት ያጋጠማት እህቴ ሆይ፤ አንቺ ለሰዎች የፍርድ ሚዛን ሳይሆን ለፈጣሪሽ ሰፊ እዝነት ቅርብ ነሽ።
እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፤ "ቢክራ" (ድንግልና) የሴት ልጅ ብቻ መለያ ተደርጎ መወሰዱ የማህበረሰባችን ትልቁ የዕይታ ስህተት ነው።
ወንድ ልጅም ድንግልና አለው፤ እርሱም የነፍሱ ንፅህናና ከዝሙት የራቀ ማንነቱ ነው። ልዩነቱ ግን የሴቷ ጉዳይ በሰዎች ዘንድ ግልጽ መሆኑና የወንዱ ግን በምስጢር መጋረጃ መሸፈኑ ብቻ ነው።አንድ ወንድ ሺህ ጊዜ ዝሙት ላይ ወድቆ ራሱን እንደ ንፁህ አድርጎ ሲያቀርብ፣ አንዲት ሴት ግን በትላንት ቁስሏ ምክንያት የጥፋተኝነት ስሜት ተሸክማ ስትማቅቅ ማየት የፍትህ መዛባት ነው።በተለይም በልጅነት ዕድሜያቸው ጥቃት ለደረሰባቸውና በጭካኔ መዳፍ ውስጥ አልፈው ድምፅ ላጡ እህቶች «አማራጭ የላችሁም» የሚል ማህበራዊ ጫና መፍጠር የድንቁርና ቅሪት ነው።
አላህ ዘንድ በትክክለኛ ተውባ የተመለሰች ነፍስ፣ ከቶውንም ስህተት ካልሰራች ነፍስ ጋር እኩል የምትሆንበት ሰፊ የራሕመት ደጅ አለ። ነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) አግብተው የፈቱትንም ሆነ የተለያየ የታሪክ ዳራ ያላቸውን ታላላቅ እናቶቻችንን በማግባት ያስተማሩን ትልቁ ቁምነገር፤ ሴት ልጅ መመዘን ያለባት በሽፋኗ ሳይሆን በውስጥ ማንነቷ መሆኑን ነው።
እህቴ ሆይ፤ አላህ አንቺን የሚመዝንበት መስፈርት ከሰዎች እይታ እጅግ የላቀ ነው። እርሱ የልብሽን ስብራት ያውቃል፣ በምስጢር የምታፈስሽውን የእንባ ዘለላ ያያል። ዛሬ ላይ ብዙዎች ትኩረታቸው አካላዊው ምልክት ላይ ብቻ ሆኖ፣ ከበስተጀርባው ያሉትን ሺህ የሕመም ታሪኮችና የተሰበሩ ተስፋዎችን ዘንግተውታል።
ስለዚህ በትላንት ቁስልሽ ውስጥ ሆነሽ ዛሬን አትቅበሪው። አንቺን በትላንት ታሪክሽ ሳይሆን ዛሬ በያዝሽው የኢማን ጥንካሬና የልብ ንፅህና የሚወድሽ፣ ክብርሽን የሚጠብቅ አማኝ ወንድ አታጪም። አላህ ለታገሱትና ወደ እርሱ ለተመለሱት ድልንና ደስታን ያዘጋጃልና ተስፋ አትቁረጪ። የፈጣሪ እዝነት ከሰዎች ወሬ ይገዝፋል!
~
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1

August 19, 20:12

ሴት ልጅኮ አስቂኝ ፍጥረት ናት....
ስታለቅስ ለራሱ መስታወት ታያለች
አለቃቀሷ እንደሚያምር
እና እንደማያምር ለማወቅ
👀

August 17, 18:16
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

አስደሳች ዜና
የሴቶች መርከዝ አልሙእሚናት
የቁርአን ሂፍዝና የኢስላማዊ እውቀት ማዕከል ለዓመታት በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሴቶች አዳሪ መርከዝ እነሆ ከመጪው ዓመት ጀምሮ በመደበኛ ፕሮግራሙ እድሜያቸው ከ14 እስከ 18 ዓመት ያሉ አዲስ ሴት ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ መጀመሩን ያበስራል፡፡
ስለሆነም በዚህ ፕሮግራም መመዝገብ የምትፈልጉ መርከዙ ወደሚገኝበት ወለቴ መጥታችሁ ምዝገባ እንድታደርጉ እናስታውቃለን።
መሟላት ያላባቸው መስፈርቶች
🔘
ቁርዓንን አስተካክላ ማንበብ የምትችል
🔘
እድሜዋ ከ14–18 የሆነ።
🔘
ከየትኛውም ቋሚ በሽታዎች ነፃ የሆነች።
🔘
ሀገራዊ ምግቦችን ሳትመርጥ መመገብ
የምትችል ።
🔘
የራሷ የሆነ ፍላጎት ያላት።
🔘
የሚሰጠውን ፈተና የምታልፍ።
ለበለጠ መረጃ 0904595077 0912941706