Выберите регион
и язык интерфейса
Покажем актуальные для региона
Telegram-каналы и возможности
Регион
avatar

Seid Social

seidsocial
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል
Подписчики
23 140
24 часа
1
30 дней
-83
Просмотры
4 445
ER
19,21%
Посты (30д)
88
Символов в посте
1 002
Инсайты от анализа ИИ по постам канала
Категория канала
Политика
Пол аудитории
Мужской
Возраст аудитории
35-44
Финансовый статус аудитории
Средний
Профессии аудитории
Медиа и коммуникации
Краткое описание
September 25, 17:15
Файлы недоступны
3
Открыть в Telegram

ቤኒያሚያን ናታኒያሁ ሲናገር ረግጠው የወጡ ሀገራትን እስራኤል ስትመዘግብ የሚያሳየው ቪዲዮ መነጋገሪያ ሆኗል።
የእስራኤሉ ዲፕሎማት ማስታወሻውን ይዞ በየወንበሩ የወጡትን ሲመዘግብ ይታያል ።
ይህ እስራኤል ማን ነኝ ብላ እንደምታስብ ለአለም በግልፅ ያሳየ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን እጅግ አስቂኝ ደካማነትን ያሳየ ነው።
ይህ ክስተት ሌላው የሚያሳየው ሀገራቱ ናታኒያሁ ሲናገር መውጣታቸው የእስራኤል መሪዎችን ምን ያክል ስሜታዊ እንዳደረገ ነው።
ኔታኒያሁ ተበሳጭቶ " ሌሎች ለመውጣተሰ ያሰባችሁ ፈሪዎች ካላችሁም ውጡ " ሲል ነበር።
እስራኤል የምትመዘግባቸውን ሀገራት በአሜሪካ በኩል ለማጥቆር እንደምትንቀሳቀስ መገመት አይከብድም።
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial

September 25, 08:30
Файлы недоступны
3
Открыть в Telegram

እኔ ሳኡዲዎች ለምን ጨፈሩ ቦረቁ ዘፈኑ አልልም መብታቸው ነው። አይመለከተኝም።
ግን ላኢላሀኢለሏህ ሙሀመደረሱሉለሏህ የሚልን የኢስላም መሰረት የጭፈራቸው ማዳመቂያ አድርገው እንዲህ ሲውረገረጉበት ማየት እንደ አንድ ሙስሊም ይሰማኛል።
ሌላው ደግሞ እነዚህን በአላህ ሸአኢሮች ላይ ኢስቲህዛእ እያደረጉ የነርሱን የፕሮፓጋንዳ ፈትዋ እዚህ አምጥተው ኡማው ላይ ፈተና የሚሆኑና "የተውሂድ ሀገር" የሚል ተምኔታዊ ስያሜ ይዘው ኢስላምን በሳኡዲ ነገስታትና ኡለሞቻቼው መነፅር ብቻ መቅረፅ የሚፈልጉ ወንድሞቻችንን ሳይ አዝናለሁ።
እነርሱ ኢስላማዊ ምልክቶቻቼው እየፋቁ ሲሆን የነርሱ ፍሬዎች ደግሞ ሙስሊሞችን ከኢስላም ማስወጣት ላይ ተጠምደዋል!
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial

September 24, 19:48
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

ዛሬ ኔታኒያሁ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ንግግር ሲያደርግ አብዛኛው የአለም ሀገራት ተወካዮች ጥለው ስለወጡ ባዶ አዳራሽ እና ትንሽ ተወካዮች ብቻ ነበር የነበሩት።
ግን እርሱ ምን ቸገረው። እንኳን አዳራሹን ለቆ መውጣት ጨርሰውስ ባይመጡ ምናሻው። አለም እንደሆነ እንደማይወዳቸውና አምርሮ እንደማጠላቸው ያውቃል።
ይሄንን የእስራኤል ፖለቲከኞች በደንብ የሚገነዘቡት ነው። ባለፈው የእስራኤሉ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት ሲናገር " አለም ሊወደን አይችልም ስለዚህ አማራጫችን እንዲፈራን ማድረግ ነው" ብሎ ነበር።
እናም ለእስራኤል አለም ወደዳት ጠላት ደንታዋ አይደለም። አሜሪካን ተቆጣጥረዋል። ዶላርን ተቆጣጥረዋል።አለምአቀፍ የገንዘብ ተቋማትን ተቆጣጥረዋል የአውሮፓ ሀገራትን ብዙዎችን መጠምዘዝ ይችላሉ ፤ የአረብ ነገስታት አገልጋዮቻቼው ናቸው፤ ስለነርሱ የሚማልዱ በርካታ የክርስቲያን ፀሎት አድራጊዎች አሉ ፤ ስለነርሱ በተዘዋዋሪ የሚሰሩና ኡማውን የሚበታትኑላቸው ሙፍቲ እና ኢማሞችን በየአረብ ሀገራት ነገስታት ቤተመንግስትና ዙሪያዎቻቼው አሏቸው ።
ታዲያ ኔታኒያሁ ይሄንን ስውር ስራቸውን ስለሚያውቅ ዲፕሎማቶቹ ጥለውት ሲሄዱ አይደናገጥ ምን አይመስለው ፈገግ ብሎ ንግግሩን ይቀጥላል።
ከመወደድ ይልቅ መፈራት ያለውን ሀያልነት እዚህ ጋር ታያለህ።
አቅም ከምንም በላይ መሳሪያ ነው።
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial

September 24, 17:52
Файлы недоступны
3
Открыть в Telegram

ይህ የትራምፕ የፍረሀትና ድንጋጤ እና የዢ ጂንፒንግ ልበሙሉነት ቪዲዮ ዛሬ የአለም መነጋገያ ሆኖ ነው የዋለው።
ትራምፕ ፕሬዝዳንት ዢን የተቀበለው በወታራዊ ስነስርአትና በአየር ላይ ትርኢት ነበር። ትርኢቱን ከሚያሳዩ ግዙፍ የጦር ጄቶች ታዲያ B-1 የተሰኘው የአሜሪካው ቦምበር ይገኝበታል። እናም ቦምበሩ በላያቸው ላይ ሲያልፍ ብረሀት የደነገጠው ታዲያ እንግዳው ዢ ጂንፒንግ ሳይሆን ተቀባዩ ትራምፕ ነበር። እንደጀግና ወታደራዊ ሰላምታ እየሰጠ የነበረው ፈሪው ትራምፕ በፍረሀት ሲደነግጥ ብዙዎችን አስቋል። ዢ የነበረው በራስ መተማመን ግን የሚገርም ነበር።
የጋዛ ንፁሀንን ፣ የኢራን የሊባኖስ የየመን ንፁሀንን የሚያስጨፈጭፈው ትራምፕ ለራሱ ጊዜ የሚገባበት ጠፋው።
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial

September 23, 18:30
Файлы недоступны
2
Открыть в Telegram

መንግስት የሰራው ትልቁ ብስለት የጦርነቱን ነጋሪት እየጎሰመ ህወሀት እንዲጀምር ማድረጉ ነው።
ያም አሜሪካ እና አጋሮቿ ፊታቸውን በመንግስት ላይ ከማድረግ ይልቅ በህወሐት እናፐአጋሮቿ ላይ እንዲያደርጉ አድርጓል።
እናም በዚህ አካሔዱ ትልቅ የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲ ድል አስመዝግቧል።
የዛሬው የአሜሪካ መግለጫም ይህን በሚገባ ያንፀባረቀ ነው። አሜሪካ በህወሓት ላይ ጣቷን ቀስራለች። ተጨማሪ ማእቀብም ለመጣል ዝታለች። ከህወሓት ጋር ጥምረት ፈጥረው ኢትዮጵያን እንወጋለን የሚሉ ታጣቂ ሀይሎችንም አስጠንቅቃለች። ብትታቀቡ ይሻላችሗል አለበለዚያ የማእቀብ መሳሪያዎች አሉን ብላለች።
በመጀመሪያው ጦርነት መንግስት ከአሜሪካ እና አጋሮቿ ጋር መጣላቱ ያስከፈለውን ዋጋ የምናውቀው ነው። ያን ዋጋ በርግጥ ሁላችንም ከፍለናል።
ህወሐት አሁን የትግራይ ህዝብ የተፋው ፣ ቁልፍ አመራሮቹ የከዱት ፣ በሞራል የላሸቀ ታጣቂ የያዘ ፤ እርሱን የሚዋጋ ከትግራይ የተውጣጣ ታጣቂ ሀይል ከፊቱ የተሰለፈበት ጣእረሞት የሆነ ድርጅት ነው።
ብቻ ይህ ጦርነት ብዙ ህዝባችንን ሳይጎዳ ብዙ ሳይራዘም የሚቋጭ ያድርገው።
ከዚህ በሗላ የጦርነት ዜና የማንሰማበትም ያድርገው።
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial

September 23, 16:27

ሳኡዲ አረቢያ እንደ ሀገር የተመሰረተችበትን 96ኛ አመት እያከበረች ነው። ለመሆኑ ሳኡዲ አረቢያ ማን ናት? እንደትስ ተመሰረተች? ከተውሂድ ሀገርነትስ ጋር ምን ያገናኛታል?
ሁሉንም አብረን እንመለከታለን !
ስለ ሳኡዲ አረቢያ ሲነሳ የመስራቾቿን የሳኡዲ ቤተሰቦችና የሸህ አብዱልወሀብ ቤተሰቦችን አለማንሳት አይቻልም ። እነዚህ ሁለት ቤተሰቦች በአካላቸው በአምሳላቸውና በስማቸው ለመፍጠር ከ ሁለት መቶ አመት በላይ ታግለዋል ። ሁለት ጊዜ የመሰረቱት መንግስት ተበታትኖ ፈርሶባቸው በሶስተኛው ጥረት እንግሊዝን አጋር በማግኘታቸው የመንግስት መመስረት የመቶ አመታት ህልምና ትግላቸውን እውን አድርገዋል ።
ሳኡዲ አረቢያ ሳኡዲ አረቢያ ከመባሏ በፊት ምእራቡ ክፍል ሂጃዝ ይባል ነበር ማእከላዊው ክፍል ነጅድ ሲባል ምስራቁ አል አህሳ ደቡቡ ክፍል ደግሞ አልአሲር ይባል ነበር ። ዋናው የአካባቢው ግዛት የቅዱሳን ከተሞች መገኛ የኢስላምም ማእከል የሆነው ግዛት ግን ሂጃዝ ነበር ስሙ ። በስሩ መካን መድናን እና ጂዳን የመሳሰሉ ቅዱሳንና ግዙፍ ከተሞችን አጠቃሏል።
ሂጃዝ ከነጅድ በመጡት በሳኡዲ ጎሳ ስር ሳይገባ በፊት ኦቶማን ኺላፋ በትልቅ ልእልና የሚያስተዳድረው ቀጠና ነበር ። ኦቶማኖች የሂጃዝ ቀጠናን የተረከቡት ማምሉኮችን ካሸነፉ በሗላ ነበር። ከነርሱ በፊት የሺአ መዝሀብ ተከታዩ የፋጢሚያ ስርወመንግስት መካ እና መዲናን ለበርካታ አመታት አስተዳድረዋል።
ሳኡዲ አንድ የአረብ ጎሳ ቤተሰብ ስም ነው ። በዚህ ጎሳ ውስጥ እስከ ሰባ የሚሆኑ አባዋራዎች የሚኖሩ ሲሆን መቀመጫ መንደራቸውም ድርኢያህ ትባላለች ። በነጅድ ቀጠና የምትገኝ መንደር ወይንም ትንሽ ከተማ ነች ። ሳኡዲን አስተዳደራዊ መዋቅር እንዲይዝ አድርጎ የመሰረተው ሙሀመድ ቢን ሳኡድ ይባላል ። የሳኡዲ ብተሰቦች ዝርያቸው ከበኑ ሀኒፋ ጎሳ ይመዘዛል ። በኑ ሀኒፋ ከነብያችን ሶ.ዐ.ወ ጋር ተዋግተው በሗላም እጅ ሰጥተው የሰለሙ ጎሳዎች ነበሩ ። ግና ነብያችን እንደሞቱ ሙሰይለመተል ከዛብን ነብይ አድርገው ከእስልምና ወጡ ። አቡበክርም ኻሊድን አዝምቸውባቸው ሙሰይለማን ገደሉት ። በኑ ሀኒፋዎችም ከዚያ በሗላ ከሙስሊሙ አለም ተገልለው ተቀመጡ ። ወደ ኢስላምም መልሰው ተቀላቀሉ ። ይሁን እንጅ አቡበክር እነርሱን አምኖ አንድም ሰው ወደ ኢስላም ዘመቻ እንዳያቀላቅሏቸው አዝዘው ነበር ።
የሳኡዲዎች ዝርያ ከዚያ ይመዘዛል ። ሙሀመድ ቢን ሳኡድ የሳኡዲን ጎሳዊ አስተዳደር ሲመሰርት ከአካባቢ አስተዳደር የማይዘል አስተዳደር እንደማይመሰርት ያውቀዋል ። ምክንያቱም ጎሳው በኢኮኖሚ ደካማ በአስተዳደርም ልምድ የሌለው ስለነበር ነው ።
እንግድህ በዚያ ወቅት ነው ከነጅድ አካባቢ ሸህ ሙሀመድ አብዱል ወሀብ የተሰኘ ዳኢ የተነሳው ።
ሙሀመድ ኢብን አብዱልወሀብ በነጅድ ሰፍረው የሚኖሩት የበኑተሚም ጎሳ አባል ነበሩ ። ቤተሰባቸው በኢልም የማይታማ ቢሆንም በቂ ኢልም ሊሰጣቸው የሚችል ግን አልነበረም ። እናም ሸህ ሙሀመድ አብዱል ወሀብ ወደ መድና እና በስራ ኢልም ፍለጋ መሄድ ነበረባቸው ። ድህነቱም ከባድ ስለነበር በዚያውም ኢኮኖሚያዊ መፍትሄም ማግኘት አላማቸው ነበር ። እናም ተምረው ሲመጡ አላህን አንድ አድርጎ ብቻ መገዛት ከዚያ ውጭ ያሉ ተወሱላቶች በሙሉ ከኢስላም ያስወጣሉ ሲሉ አስተምህሮአቸውን በኡወይና ጀመሩ ። የዘመናቸው ሙስሊሞች በጅህልናና በሽርክ ውስጥ እንደተዘፈቁና እንዴውም ሙሽሪክነታቸው ከነብያችን መላክ በፊት ከነበረውም የከፋ መሆኑን አወጁ። أن مشركي زماننا أغلظ شركًا من الأولين؛ لأن الأولين يشركون في الرخاء ويخلصون في الشدة، ومشركو زماننا شركهم دائمًا في الرخاء والشدة
በማለት አስተምህሮቶቻቼውን አጧጡፈው ቀጠሉ።
ቢዲአን ሁሉ ውግዝ አድርገው ከዚያ ውጭ ምንም እንዳይሰራ አስተማሩ ግና የኡወይና አስተዳዳሪ ኡስማን ኢብኑ ሙአመር እርሳቸውን ኢስላም አለቅጥ ድንበር ያለፈና ሙተነጢእ አስተምሮ ነው በማለት አባረራቸውና ወደ ሙሀመድ ቢን ሳኡድ ተሰደዱ ።
ሙሀመድ ቢን ሳኡድ ጋር ሲሄዱ በክብር ተቀበላቸው ። እዚያ የተስማሙት ነገርም የአሁኑን ሳኡዲ አረቢያ የመፈጠርን ፅንስ ፀነሰ ። በ 1744 እ.ኤ.አ በሙሀመድ ኢብን አብዱል ወሀብና በሙሀመድ ቢን ሳኡድ መካከል የተፈረመው ስምምነት የሀገር መምራት ጉዳይን ሙሀመድ ቢን ሳኡድ ሊመራ የሀይማኖታዊ ጉዳዩን ደግሞ ሸህ ሙሀመድ አብዱልዋሀብ ሊመሩ ተስማሙ። እናም አንድ ላይ ሆነን በከሀ¶¶¶]ዲያን ላይ ጅሀድ እንከፍታለን ሲሉ ቃል ተገባቡ ። ዘካ እና ግብርም ለሳኡዲ ብቻ እንዲከፈል ሸህ ሙሀመድ አብዱልዋሀብ ፈትዋ ሰጡ ። ይህ የሙሀመድ ቢን ሳኡዲን ኢኮኖሚያዊ አቅም አፈረጠመለትና የአረብ ጎሳዎችን መውረር ጀመረ ።
ስምምነቱ ገቢር መሆን ጀመረ ። የሚያሳዝነው ግን ጅሀድ ተብሎ የሚታወጅባቸው ሙስሊም መሆናቸው ነበረ ። እናም የሁለቱ ሙሀመዶች ጥምረት ሳኡዲ-ወሀቢ አገዛዝ ተባለና በሂጃዝና በነጅድ ቀጠና ጦርነታቸውን አስፋፉት ። በዚህ ጊዜ የኦቶማን ኺላፋ ለሳኡዲ-ወሀቢ ጅሀድ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
ግና የሳኡዲ ጎሳዎችና የሸህ ሙሀመድ ተከታዮች ዘመቻቼውን አጠናክረው ቀጠሉ ። በድርኢያ ከተማ የሸሁን ደርስ የማይከታተል ላይ ቅጣት ተላለፈበት ። የእርሳቸውን አስተምህሮ በማይከተሉ ሙሉ ላይም ጅሀድ ተከፈተባቸው ። ዘመቻው እንደቀጠለም ሁለቱም መሪዎች ሞቱና ልጆቻቼው ተተኩ ።
በዚህ ጊዜ ትእግስቱን ያጣው የኦቶማን ኺላፋ በኢብራሂም ፓሻ የሚመራውን ጦሩን ወደ ነጅድ አንቀሳቀሰ ። እናም የሙሀመድ ቢን ሳኡድ ልጅ አብዱሏህ አልሳኡድ የሳኡዲ ወሀቢን ጦር እየመራ ተጋጠሙ ። የኦቶማን ጦርም ጦራቸውን በታትኖ በርካታ የሸህ ኢብን አብዱልወሀብ ተከታይ ሸሆችንና ታጋዮችን ገደለ ። መሪውን አብዱሏህንም ወደ ካይሮ ተይዞ ሄደ ። ከዚያ ከካይሮ ወደ ኢስታንቡል ተላከና እዚያ ተፈርዶበት አንገቱ ተቀልቶ እንዲገደል ተደረገ ። የመጀመሪያው የሳኡዲ ኢማራትም በዚህ መልኩ ተጠናቀቀ ።
ከዚያ በሗላ ሁለተኛው የሳኡዲ ኢማራት በሟቹ ልጅ በቱርኪ ቢን አብዱሏህ ተመሰረተ ። ይሁን እንጅ ይህንንም የኦቶማን ኺላፋ በታተነውና ደመሰሳቸው ።
አሁን ሶስተኛው የሳኡዲ ኢማራት ላይ ደርሰናል ። አሁን ሁሉ ነገር የተመቻቼላቸው ይመስላል ። የኦቶማን ኺላፋን ለማፍረስ ምእራባዊያን ከምእራብ ሩሲያ ከሰሜን በአንድነት ጦርነት ከፍተዋል። የኦቶማን ኺላፋ ከሊቢያ እስከ ሀንጋሪ ፤ ከአዘርባጃን እስከ የመን ፤ ከኤስትራ እስከ ኢራቅ ከኢስላም ጠላቶች ጋር እጅግ ከባዱን ጦርነት እየተዋጋ ነው ። ይህንን እንደ አጋጣሚ ያገኙት የሳኡዲ ጎሳዎች ከእንግሊዝ ጋር ጥምረት ፈጠሩ ። እንግሊዝም አጋጣሚውን እልል ብላ ተቀበለቺው ።
ግና እንግሊዝ ብልጥ ነበረች ። እናም እንግሊዝ ሁለት የአካባቢው አረብ ጎሳዎችን በኦቶማን ኺላፋ ላይ አስታጥቃ ለቀቻቼው ። እነዚህ ሁለት ጎሳዎች የሸሪፍ ጎሳዎችኛ የሳኡዲ ጎሳዎች ነበሩ ።  እነ ሎውረንስ ኦፍ አረቢያ ሙስሊም መስለው የሳኡዲ አማፂያን ውስጥ በመግባት የእስልምና አስተምህሮን እነርሱ እንዲመቻቼው በማድረግ በሙስሊም ላይ ሙስሊም ጅሀድ እንዲያደርግ አስደረጉ ።

September 23, 16:27

በእንግሊዝ የሚደገፉት የሸሪፍ ጎሳዎች መድናን እና መካን በመውረር ከፍተኛ ውድመት አደረሱ ። ይሁን እንጅ በፈኽረዲን ፓሻ የሚመራው የኦቶማን ጦር ያለ የሌለ ሀይሉን ተጠቅሞ መካና መድና በረሀብና ጥም እየተሰቃየ ለ 70 ቀናት ተዋጋ ። ጦርነቱ እየከበደ ነው ። የመድና ፍቅር ያነሆለለው ህይወቴ ስለቅዱሳን ከተሞች ፊዳእ ትሁን ያለው ፈኽረዲን ፓሻ የእንግሊዝን መሳሪያዎችና የጦር አመራሮች ዘመቻ በታዛዦቻቼው አረቦች የተከፈተውን እልህ አስጨራሽ ትግል እየተፋለመ ነው ። ግን በዚህ ሁሉ መካከል ድንገት ሸሂድ ብንሆን ብሎ የነብያችንን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ውድ ቅርሶች የእርሳቸውን መገልገያዎችና ቅዱሳን ነገሮቻቼው እንዳይወድሙ በድብቅ ወደ ኢስታንቡል ላካቸው እናም ፍልሚያው ቀጠለ ። ግና መሰሪዎቹ እንግሊዞች ከራሱ ሰዎች ውስጥ አንዱን አስከድተው ፈኽረድንን ተቆጣጠሩት ። መካና መድናም ለ ሺህ ከመታት በሗላ በጎሳዎች እጅ ወደቀች ።
የሸሪፍ ጎሳዎች ከእንግሊዝ ጋር በአንድ ነገር ተጣሉ እርሱውም ሸሪፎች የእስራኤልን በፍልስጤም ምድር መመስረት አንፈልግም የአረብ አስተዳዳሪዎችም እኛ ነን ሲሉ እንግሊዝ የሳኡዲ ጎሳዎችን አዘመተችባቸው ። እናም የሳኡዲ ጎሳዎች የሸሪፍ ጎሳዎችን ደምስሰው መካና መድናን በ 1924 እና በ 1925 ለመጀመሪያ በታሪክ ተቆጣጠሩ ። እንግሊዝ ይህንን የፈቀደችላቸው ሳኡዲዎች የእንግሊዝን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ በመቀበላቸውና የእስራኤልንም መመስረት ባለመቃወማቸው ነበረ።
እናም በ 1932 እንግሊዝና ፈረንሳይ ባሰመሩላቸው መስመር በአብደላህ ኢብን ሳኡድ የሚመሩት የሳኡዲ ጎሳዎች የአሁኗን ሳኡዲ አረቢያን መሰረቱ ።
እናም ሳኡዲነትና ነብያችንን የሚያገናኛቸው የለም ። ሳኡዲዎች የነብያችንን ከተሞች መካና መድናን በእንግላዞች እርዳታ የተቆጣጠሩ ጎሳዎች እንጅ ነብያችን ሳኡዲ አረቢያ የምትባል ሀገርም አያውቋትም ።
አሁን ላይ ሳኡዲ አረቢያ የተባረኩትን የሂጃዝ ከተሞች መካና መዲናን እንዲሁም ያልተባረኩትን የነጅድ ግዛቶችን የያዘች ሀገር ነች። ሳኡዲ በአለም ላይ የአንድ ጎሳ ሀገር ከሆኑ ሀገሮች አንዷ ነች። በርግጥ አብዛኛው የአረብ ሀገራት በጎሳዎች የሚተዳደሩ ሀገራት ናቸው። ኳታር በአል ታኒ ጎሳ፣ ኢማራት በአልናህያን ጎሳ ፣ ሳኡዲ አረቢያ በአልሳኡዲ ጎሳዎ ፣ ባህሬን በአልኸሊፋ ጎሳ ፤ ኩዌይት በአልሳባህ ጎሳ ፣ ጆርዳን በአልሀሽማይት ጎሳ ፣ ሞሮኮ በአል አለዊ ጎሳ የሚመሩ ሀገራት ናቸው።
እነዚህ ሀገራት ዳር ድንበራቸው ተለክቶና ተሰፍሮ የተሰጣቸው በእንግሊዝ እና ፈረንሳይ ሲሆን በሗላም ሞግዚትነቱን አሜሪካ ተረክባለች።
👉
t.me/Seidsocial

September 22, 18:36
Файлы недоступны
3
Открыть в Telegram

ህወሓት አሁን የትግራይ ወጣቶችን ይዤ ልጥፋ ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ነገሩ የጠፋበትና ግና ከመጋደል ውጭ ምንም የማይታየው ድርጅት ነው።
የዛሬው የአላማጣ ውሎ ከዚህ የተለየ ነገር የለውም።
የግድ እንሙት ካልሆነ ሁሉም የህወሐት ተዋጊዎች ይሄን ጦርነት እናሸንፋለን የሚል እምነትም ወኔም የላቸውም። በግዳጅ ባሉበት በዚህ ግንባር ዛሬ ነገ ድሮን መጥቶ ጨረሰን እያሉ ከመጠበቅ የዘለለ አሁን ሽምቅም ቆረጣም የሚያደርጉበት የጦርነት አቅም የላቸውም።
የትግራይ ህዝብ በብዙ የኢኮኖሚ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ውስጥ በሚገኝበትና ከሁሉ በላይ ከጦርነት ፋታ ማግኘትን እንደ ሰማይ መና በሚጠብቅበት ወቅት ዛሬም እንዋጋለን ብሎ የገገመው ህወሐት ወጣቶቹን የድሮን ሲሳይ እያደረጋቸው ነው።
ድሮኖቹ በየእለቱ ከኤርትራ ድንበር ጀምሮ አጠቃላይ ትግራይን ሲቃኙ ነው የሚውሉት። ሁሉም የህወሐት እንቅስቃሴ በድሮኖች ሰርቪሊያንስ እይታ ስር ነው። ይሄን እነርሱም ያውቁታል። ግን አማራጭ የላቸውም። አንዋጋም ቢሉ አመራሮቹ ያስመቷቸዋል ቢዋጉ ሳይተኩሱ ያልቃሉ።
ዛሬ አላማጣ እና አካባቢው ላይ ካለቁት የህወሐት ታጣቂዎች ውስጥ አንዋጋም ብለው ትጥቃቸው የተገፈፈባቸውና ወደ መሰብሰቢያ የተወሰዱ አብረው እንዳሉበት ስምቻለሁ።
ይሄ የሞት አዙሪት ይብቃ የሚለው ዘመቻ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊስተጋባ ይገባል። አማፂያኑ ትኩስ ያቁሙ ጦርነት ያቁሙ የሚል ህዝባዊ ዘመቻ በሁሉም ኢትዮጵያን ሊጠናከር ይገባል።
እንደ ሀገር ሊኖረን የሚገባው አንድ ሰራዊት ብቻ ነው። ከመንግስት ጋር ያሉብንን የኢኮኖሚ የመልካም አስተዳደር እና ሌሎችም ችግሮች በህዝባዊ ሰላማዊ ትግል እንጅ በዚህ መልኩ እንደ እሳት እራት ለሚሞትበት ጦርነት አይደለም።
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial

September 22, 09:05
Файлы недоступны
2
Открыть в Telegram

አሜሪካ በኢራን አየር መንገድ ላይ ማእቀብ መጣሏን ተከትሎ ሀገራት የኢራን አይሮፕላኖችን ከበረራ ክልላቸው ማገድ ጀምረዋል።
በዚህም መሰረት ቱርክ እና ኢራቅን ጨምሮ የአረብ ሀገራት የአየር ክልላቸውን ለኢራን አየር መንገድ ዝግ አድርገዋል።
የአውሮፓ ህብረት ቀድሞም አየር ክልሉን ለኢራን ዝግ አድርጎ ስለነበር ወደዚያ የሚደረግ በረራም አይኖርም።
የቱርክ አየር መንገድን ጨምሮ የአረብ ሀገራት አየር መንገዶችም ከኢራን እና ወደ ኢራን የሚደረጉ በረራዎችን እንደሚያቋርጡ አስታውቀዋል።
ይህም ለኢራን ከባድ ፈተናን ይዞባት የሚመጣ ይሆናል።
አሜሪካ የኢራንን አይሮፕላኖች በክልላቸው የሚያሳልፉ በአየር ማረፊያዎቻቼው የሚያስተናግዱ ሀገራትን ከዶላር ግብይት ውጭ ከማድረግ ጀምሮ በርካታ የኢኮኖሚ ማእቀቦችን እንደምትጥል አሳውቃለች።
ይህን የአሜሪካ እቀባ ማለፍ የምትችለው ቻይና ስትሆን ቻይና የአሜሪካን ማእቀብ እንደማትቀበለው አሳውቃለች።
እናም አለም ለአሜሪካ ትእዛዝ እጅ ሰጥቶ ኢራንን አግልሏል።
ኢራንም ሆርሙዝን እና ቀይ ባህርን ቆርጣ አለምን ትበቀላለች ተብሎ ይጠበቃል።
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial

September 22, 05:36
Файлы недоступны
2
Открыть в Telegram

አሁንስ ፋኖ እና ኦነግ ሸኔ በትብብርና ለፖለቲካ ቁማራቸው የወለጋ አማራዎችን አልጨፈጨፉም ብሎ የሚያስተባብለኝ ይኖር ይሆን?
አዎ እነዚህ የሽብር ድርጅቶች ከደራ እስከ ወለጋ እየተናበቡ በንፁሀን ደም ነግደዋል ተጫውተዋል ለመንገር የሚከብዱ ግፎችን ፈፅመዋል።
ይህንን ግፍም ለፖለቲካ ቅስቀሳቸው በሚገባ ተጠቅመውታል።
ይሄው መጨረሻ ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ያለውን ጥብቅ ቁርኝታቸውን ይፋ አውጥተውት ተከስተዋል።
አጀንዳ ሲያጡ አንተ አማራን ግደል አንተ ኦሮሞን ግደል ተባብለው በህዝብ ደም ይህን ሁሉ የደም ንግድ ሲያካሒዱ ኖረዋል።
በጊዜ ሂደት ሁሉም የግፍ ሴራዎች እየፈጠጡ ይመጣሉ።
ቴሌግራም
👉
t.me/Seidsocial