Выберите регион
и язык интерфейса
Покажем актуальные для региона
Telegram-каналы и возможности
Регион
avatar

Sheger Press️️

sheger_press
Official channel of sheger press Contact @Birukepromo
Подписчики
35 677
24 часа
243
30 дней
79
Необычный рост (24 часа)
Просмотры
2 731
ER
7,65%
Посты (30д)
326
Символов в посте
920
Инсайты от анализа ИИ по постам канала
Категория канала
Религия и духовность
Пол аудитории
Женский
Возраст аудитории
25-34
Финансовый статус аудитории
Средний
Профессии аудитории
Туризм и гостиничный бизнес
Краткое описание
September 25, 16:32

ኢሰመኮ  መግለጫ አወጣ!»
«በትግራይ፣ አማራ እና አፋር አዋሳኝ አካባቢዎች አደገኛ የትጥቅ ግጭቶች መቀስቀሳቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሁን ይፋ አደረገ!
ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ፦ ህወሓት ያሰማራቸው ታጣቂዎች ወደ አፋርና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች ዘልቀው በመግባት ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ፤ በዋግ ኸምራ እና በሰሜን ወሎ ላስታ ወረዳዎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በታጣቂዎቹ መካከል ከባድ ግጭት መከሰቱን አስታውቋል።
ግጭቱ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እያስከተለ ነው ያለው ኢሰመኮ፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት ፈራሚ አካላት ጦርነቱን በአስቸኳይ እንዲያቆሙና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም አስቸኳይ የዲፕሎማሲ ጣልቃ ገብነት እንዲያደርግ ጠይቋል!»

September 25, 16:13

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን
🙏
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ገና በቅድስት ሐና ማሕጸን ከነበረችበት ወቅት ጀምሮ ተአምራት ታደርግ ነበር፡፡ አንድ አይኗን ያጣች ቤርሳቤህ የተባለች ሴት የሀናን መጽነስ ስትሰማ በደስታ ልትጎበኛት መጣች፡፡ ቅድስት ሐናን እንኳን ደስ አለሽ ብላ ሆዷን ከዳሰሰቻት በኋላ በዚያው እጇ ዓይኗን ብትነካው ዐይኗ በርቶላታል፡፡ ይህን ምሳሌ አደርገው ድውያን እየመጡ ሆዷን ዳሰው ይፈወሱ ነበር፡፡ በመካንነት የነበሩት ወላጆቿ ልጅ ከሰጣቸው ለቤተ እግዚአብሔር ሊሰጡ ስዕለት ገብተው በቅድስት ድንግል ማርያም መወለድ ፍሬ ሲያገኙ ዓለም ደግሞ የመድኃኒቱን እናት አጊኝቷል፡፡ እናታችን ቅድስት ሐና ጸንሳ ሳለች የአጓቷ ልጅ አርፎ እጅግ የአልጋውን ሸንኮር እየዞረች ስታለቅስ ከሞተበት ተነስቶ “የሰማይና የምድር ፈጣሪ አያት ሆይ ላንቺ ክብር ይገባሻል” ብሎ መስክሮ ተመልሶ አርፏል፡፡
አይሁድም “ቀድሞ የእነዚህ ዘር የነበሩ ዳዊትና ሰሎሞን አርባ፣ አርባ ዘመን ገዙን አሁን ከዚህች የሚወለድ ምን ሊያደርገን ነው?” ብለው በድንጋይ ሊወግሯት ተነሱ፡፡ የራማው ልዑል ቅዱሰ ገብርኤል ወደ ሊባኖስ ተራራ ወሰዳቸው፤ በእዚያም በጨለማ ውስጥ የነበረው ዓለም ብርሃን የሚያይባት፣ የእውነተኛው ጸሐይ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡ ኢያቄምና ሐና የተሳሉትን ስእለታቸው አስታውሰው በሦስት ዓመቷ ወስደው ለቤተ እግዚአብሔር ሲሰጧትም ካህኑ ዘካርያስ ስለምግቧ ተጨንቆ፤ ሕዝቡን ሰብስቦ ሳለ መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፤ ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ ሀብት መስሎት ሊቀበል ሲቀርብ ወደ ላይ ራቀበት፡፡ በዚያ በተሰበሰቡትም ቢሞክሩ አልሆነም፡፡
ዘካርያስም ሐናን “እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ” አላት፤ በዚያም ጊዜ ቅድስት ማርያም እናቷን ስትከተል መልአኩ ፋኑኤል ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መግቧት፤ በክብር ዐረገ፡፡ ሊቀ ካህናቱና ሕዝቡም “የምግቧ ነገር ከተያዘልን በቤት እግዚአብሔር ትኑር” ብለው ታህሣስ 3 ቀን ወደ ቤተ መቅደስ አስገቧት፡፡ ለ12 ዓመታትም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች በቤተ መቅደስ ኖረች፡፡ ይህችን ብርሃን፣ የብርሃን እናት ገዳማውያን አባቶችና እናቶች ዘወትር በጸሎታቸው ያስቧታል፡፡ ገዳማቸውን እናግዝ፣ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000766349227
ወይም
አቢሲንያ ባንክ
262281132
የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921

September 25, 16:13
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

September 25, 14:58

በአማራ ክልል የኤልኒኖ ክስተት የሚያደርሰውን ተጽዕኖ ለመከላከል የተቀናጀ ምላሽ እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ
በአማራ ክልል በኤልኒኖ ክስተት ምክንያት ያጋጠመውን የድርቅ ሁኔታ ለመቋቋምና የሚያሳድረውን አሉታዊ ጫና ለመቀነስ ክልላዊ እቅድ ተዘጋጅቶ ዘርፈ-ብዙ የቅድመ መከላከል ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ትብለጥ መንገሻ አስታወቁ።
ኃላፊዋ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ክስተቱ በስፋት በምስራቅ አማራ እንዲሁም በከፊል በምዕራብ አማራ አካባቢዎች ተከስቶ የቆየ ሲሆን፣ በተለይም ከሐምሌ 19 በፊት በነበሩ ጊዜያት በበርካታ ወረዳዎች ላይ የዝናብ እጥረት አጋጥሞ እንደነበር አስታውሰው ይሁን እንጂ ከሐምሌ 19 ወዲህ ባሉት ቀናት በአብዛኛዎቹ ወረዳዎች ዝናብ መዝነብ መጀመሩን ጠቁመዋል።
"አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ስለደረሰው ጉዳትና የሰው ህይወት መጥፋት የሚያሰራጩት መረጃ የተጋነነና መሰረተ-ቢስ ነው" ያሉት ወ/ሮ ትብለጥ፣ የድርቁ ተጽዕኖ በዋናነት በመጪው የምርት ዘመን ላይ ሊያርፍ የሚችል በመሆኑ፣ ገና በጅምር ላይ እያለ “ይህን ያህል ጉዳት አደረሰ” ተብሎ የሚናፈሰው መረጃ ትክክል እንዳልሆነ ገልጸዋል። ሆኖም ችግሩ የለም ማለት እንዳልሆነና መንግሥት አደጋውን ለመቀልበስ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት አፋጣኝ ምላሽ እየሰጠ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ጉዳቱን ለመቀነስ የተዘረጋውን እቅድ በተመለከተም፤ ዝናብ ባገኙ አካባቢዎች የእርጥበት እቀባ ሥራዎችን ማከናወን፣ ወቅቱን የጠበቀ እርሻ ማካሄድ እንዲሁም ሰብልን በአግባቡ የመንከባከብ እርምጃዎች በግብርና፣ በጤና እና በአደጋ መከላከል ዘርፎች በቅንጅት እየተተገበሩ ይገኛሉ ብለዋል። ይህም ድርቁን ከመከላከል ባሻገር ማህበረሰቡን ከተረጂነት አስተሳሰብ ለማላቀቅ የሚያስችል ነው ሲሉም አክለዋል።
በተጨማሪም የኤልኒኞ ክስተት በአንድ በኩል ድርቅን በሌላ በኩል ደግሞ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋን ሊያስከትል ስለሚችል፣ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ተደራሽ የማድረግና የቀውስ ጊዜ ኮሙኒኬሽን እቅድን ተግባራዊ የማድረግ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ምክትል ቢሮ ኃላፊዋ ገልጸዋል።

September 25, 14:46
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

በብሠራተ ገብርኤል  ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንት
በካሬ 115,000 ሺ  ብር በ15% ቅድመ ክፍያ ብቻ በ3 አመት የሚከፍሉት!!!
ቀድመዉ ለሚመጡ ዉስን ደንበኞች የማስታወቂያ ዋጋ
በ 73/27 አከፋፈል  በካሬ 80,500 ብር ብቻ!!!
በፓስቴሽን ቴክኖሎጂ ታግዞ የሚሰራ
ከባለ 1 ከ 82 ካሬ እስከ ባለ 3 ከ 248 ካሬ መኝታ
ባለ 1 መኝታ -82 ካሬ
ቅ/ክፍያ -1,414,500
ሙሉ ክፍያ -9,430,000
100% ለሚከፍል-6,883,900
ባለ ሁለት መኝታ -110ካሬ
ቅ/ክፍያ-1,897,500
ሙሉ ክፍያ-12,650,000
100% ለሚከፍል -9,234,500
ባለ ሶስት መኝታ-163ካሬ
ቅ/ክፍያ-2,811,750
ሙሉ ክፍያ-18,745,000
100% ለሚከፍል-13,683,850
በዚህ መንደር
👉
መዋኛ ገንዳ
👉
ጂምናዚየም
👉
ደረጃቸውን የጠበቁ ሰፋፊ ሊፍቶች
👉
ምቹ እና በቂ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች
👉
ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ
👉
አውቶማቲክ ጀነሬተር የተገጠመለት
👉
የከርሰ ምድር ውሃ እና
👉
ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል ሰገነት  አካቷል
ለበለጠ መረጃ
✅
0973287475
📞
WhatsApp
0973287475
ይደዉሉልን!

September 25, 14:25

የቅድስት ኪዳነ ምህረት ምልጃዋ እና ረድኤቷ  አይለየን
🙏
በራሴ፣ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ”
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጌታችን ምክንያት ያገኛት ሃዘን እጅግ መራራ ነው፡፡ በግብጽ በስደቷ፣ ጌታችን ከተያዘበት ከምሴተ ሐሙስ ጀምሮ በግርፋቱ፣ በስቅለቱና በሞቱ እስከ ትንሣኤው ያፈሰሰችው እንባ ስፍር ቁጥር የለውም፡፡ ከሙታን ከተነሳ በኋላም በጎልጎታ በልጇ መቃብር ላይ “ልጄ ወዳጃ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ፣ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው ስለመኾንህ፣ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስለቻለችህ ማኅፀኔ፣ ከአንተ ጋር ከሀገር ወደ ሀገር ስለመሰደዴ መናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡” በማለት ለተወዳጅ ልጇ ስለኛ ስለሰው ልጆች ፍጹም ልመና አቅርበለች፡፡
ጌታችንም እልፍ አእላፍ መላእክት ጋር መጥቶ “እናቴ ማርያም ሰላም ላንቺ ይኹን! እንዳደርግልሽ የምትለምኚኝ ምንድን ነው?” አላት፡፡ እመቤታችንም በስሟ የሚማጸኑትንና መታሰቢያዋን የሚያደርጉትን፣ ለችግረኛ የሚራሩትን፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያንጹትን፤ ዕጣን ጡዋፍ ዘቢብ መባእ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን፤ ለእርሷና ለሃይማኖታቸው ካላቸው ፍቅር የተነሣ ልጆቻቸውን በስሟ የሚሰይሙትን ሁሉ እንዲምርላትና ከሞተ ነፍስ እንዲያድንላት ጠየቀችው፡፡
ጌታችንም በመዝሙር 88÷3 “ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ” ተብሎ እንደተጻፈ፣ “ይህን ሁሉ እንዳደርግልሽ በራሴ፣ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ” ብሎ የካቲት 16 ቀን ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ እኛም ማደሪያው ትሆን ዘንድ ከመረጣት ከእመቤታችን ጋር ዕለቱን በየወሩ በ16ኛው ቀን በታላቅ ደስታ እናከብረዋለን፡፡ ይህን ቃል ኪዳኗን ያመኑ፣ በእናትነት ፍቅሯ ከምልጃዋ በረከት የተካፈሉ ገዳማውያን ሌሊትና ቀን ቅድስት ሆይ ለምኝንልን ይሏታል፡፡ የቀን ሀሩር የሌሊት ቁር ሳይበግራቸው በጸሎተው ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የእመቤታችን በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

September 25, 14:25
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

September 25, 12:00

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በአፋር እና አማራ ክልል ባሉት አዋሳኝ አካባቢዎች ባሰማራቸው ታጣቂዎች፤ ባለፈው ማክሰኞ መስከረም 12፤ 2019 ከለሊቱ 9 ሰዓት ጀምሮ “ጥቃት መክፈቱን” የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ። በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መካከል እና ህወሓት “ባሰማራቸው ታጣቂዎች” መካከል በዋግ ኸምራ ዞን አካባቢዎች እና በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ “ግጭቶች መከሰታቸውንም” ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ኢሰመኮ ይህን ያስታወቀው በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ፤ ዛሬ አርብ መስከረም 15፤ 2019 ባወጣው መግለጫ ነው። በትግራይ እና በአማራ እንዲሁም በትግራይ እና በአፋር ክልሎች አዋሳኝ ስፍራዎች የነበረው “ውጥረት” “ከጊዜ ወደ ጊዜ” ሲባባስ መቆየቱን በመግለጫው ያስታወሰው ኮሚሽኑ፤ በእነዚህ አካባቢዎች “የትጥቅ ግጭቶች” “መቀስቀሳቸውን” ባሰባሰባቸው “መረጃዎች እና ማስረጃዎች” ማረጋገጡን ገልጿል።
በአካባቢዎች ላይ በአሁኑ ወቅት “የትጥቅ ግጭቶች” “እየተካሄዱ” መሆኑንም መንግስታዊው የሰብአዊ መብቶች ተቋም አመልክቷል። “እነዚህ አካባቢዎች በተደጋጋሚ በትጥቅ ግጭት የተጎዱ እና በበቂ ሁኔታ ያላገገሙ በመሆናቸው፤ የትጥቅ ግጭት ዳግም መከሰቱ የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ሁኔታ ላይ ተደራራቢ ጉዳትን ሊያሳድር የሚችል በመሆኑ እጅግ አሳሳቢ ነው” ሲልም ኢሰመኮ በመግለጫው አስገንዝቧል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

September 25, 05:09

መረጃ
‼️
በትግራይ ክልል የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎቶች መቋረጣቸው ተሰማ
!
#በትግራይ
ክልል እና አዋሳኝ አካባቢዎች እየተደረገ ያለው ውጊያ ተባብሶ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት በክልሉ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ተሰምቷል።
የአገልግሎት መቋረጡ የተከሰተው ትናንት ሌሊት ከ4፡21 ጀምሮ እንደሆነ ታውቋል።ምንጮች እንደገለጹት ከሆነ የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ቢቋረጥም ለጊዜው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የስልክ አገልግሎት አሁንም እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል። ሆኖም ግን የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መዘጋቱ በክልሉ ነዋሪዎች፣ በንግዱ ማህበረሰብ እና በቤተሰብ ግንኙነቶች ላይ ከፍተኛ የመረጃ ክፍተትና ጭንቅ ፈጥሮ ይገኛል።
@Ankuar_mereja
@Ankuar_mereja

September 25, 04:46

ቅዱስ ቂርቆስ የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ
🙏
የሚያገኛቸውን መከራ ሳይፈሩ ስለ ክርስቶስ አምላክነት ከመስከሩ የክብር አክሊል ከተቀዳጁ ሰማዕታት የሦስት ዓመቱ ሕጻን ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ቅድስት ኢየሉጣ የሮም ግዛት በሆነው አንጌቤን በክርስትና ሃይማኖት ጸንታ የምትኖርና ልጇ ቅዱስ ቂርቆስንም በስርዓት ያሳደገችው ደግ ሴት ነበርች፡፡ በዘመኑ የነበረውን አረማዊ አስተዳዳሪ እለእስክንድሮስን በመፍራት ከልጇ ጋር ከሮም ወደ ጠርሴስ ብትሰደድም እለእስክንድሮስ ተከትሎ ባለችበት ቦታም አገኛት።
ወታደሮችም እርሷንና ልጇን ይዘው ወደ መኮንኑ አቀረቧቸው። መኮንኑም "ስምሽን ንገሪኝ" ቢላት "ስሜ ክርስቲያን ነው" አለችው። መኮንኑ በብስጭት ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንም "ስምህን ንገረኝ" ሲለው "ስሜ ክርስቲያን ነው፤ እናቴ የሰየመችኝን ከፈለክ ግን ቂርቆስ ነው" ሲል መለሰለት። ቅድስት ኢየሉጣንም "ለጣዖት ልትሰግጂ ይገባል" ሲላት “የምንሰግድለት አንድ ክርስቶስ ብቻ ነው” አለችው፡፡ ቅዱስ ቂርቆስም እየደጋገመም "እኔ ክርስቲያን ነኝ" ብሎ በመጮሁ ምላሱን ቢያስቆረጠው እግዚአብሔር ፈውሶታል፡፡
መኮንኑ መከራ አጸናባቸው፤ በግርፋት የጀመረ ስቃይ ሊሰሙት ወደ ሚጨንቅ መከራ ቀጠለ። በፈላ ውሃ ውስጥ ሲከታቸውም ቅዱስ ገብርኤል አዳናቸው፡፡ እናትና ልጅ በክርስቶስ ታምነዋልና ጸኑ።
ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላም ጥር 15 ቅዱስ ቂርቆስን ጥር 16 ደግሞ ቅድስት ኢየሉጣን ሰይፏቸው ሰማዕትነት ተቀብለዋል፡፡ የሕጻኑን ሥጋ በሠረገላ ኤልያስ አኑሮታል፣ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል።
ዛሬም በየገዳማቱ ዓለምን ንቀው የሚኖሩ መነኮሳትና ገዳማውያን በጸሎታቸው ኃይል ያደርጋሉ፡፡ ከዓለም ክብር የክርስቶስን ክብር፣ ከሥጋ ደስታ መንግስተ ሰማያትን መርጠዋልና፡፡ ገዳማቸውን እናግዝ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444