Выберите регион
и язык интерфейса
Покажем актуальные для региона
Telegram-каналы и возможности
Регион
avatar

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

yasin_nuru
የ ያሲን ኑሩ ሐዲሶች Yasin Nuru "ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ) "የበጎ ስራ ምላሹ በጎ እንጂ ሌላ አይደለም " የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል :>> { አል -ዘልዘለህ 7} UNOFFICIAL ለአስተያየት 👇 👇 @Hasabbbbot ሀዲሶችን ከፈለጋችሁ 👇 👇 @yasin_nuru_hadis
Подписчики
42 405
24 часа
-13
30 дней
83
Просмотры
7 382
ER
17,41%
Посты (30д)
21
Символов в посте
974
Инсайты от анализа ИИ по постам канала
Категория канала
Религия и духовность
Пол аудитории
Мужской
Возраст аудитории
25-34
Финансовый статус аудитории
Средний
Профессии аудитории
Образование
Краткое описание
September 25, 14:16
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

የዱሃ ሶላት...
ነቢዩ (ﷺ) እንዳስተማሩን በሰውነታችን ውስጥ 360 መገጣጠሚያዎች ያሉ ሲሆን፣ በየቀኑ በሰላም ለተንቀሳቀሰበት ለእያንዳንዱ
መገጣጠሚያችን ምስጋናና ሰደቃ ማቅረብ ይጠበቅብናል።
ይሁን እንጂ የአላህ እዝነት ሰፊ ነውና—በረፋድ ሰዓት የምንሰግዳት ሁለት ረከዓ የዱሃ ሶላት ብቻዋን ለእነዚህ ሁሉ 360
መገጣጠሚያዎች እንደ ሙሉ ሰደቃና ምስጋና ሆና በቂ ሆና ትተካለች።
የመስገጃ ወቅቱም ፀሐይ ወጥታ ከፍ ካለችበት (ረፋድ) ጀምሮ እስከ ዙህር ጥቂት ደቂቃዎች እስኪቀረው ድረስ ነው። በየቀኑ ጥቂት ደቂቃዎችን ሰጥተን ይህችን ውድ ሶላት በማዘውተር የሰውነታችንን ጤና ጸጋ እናመስግን!
@yasin_nuru
@yasin_nuru

September 24, 06:56

ኻሊድ ቢን በርመክ እንዲህ ይላል፦
❝ዝሙት የክፋት ፀባዮችን በሙሉ አጠቃልሎ የያዘ ነው። አንድ ዝሙተኛ ዘንድ አላህን መፍራት፣ ቃል ኪዳን ማክበርም ሆነ ለጓደኛ ታማኝ መሆንን አታገኝም።
— ከኢብኑል ጀውዚ «አኽባሩ-ኒሳእ» ኪታብ የተወሰደ
وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَا ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًا
"ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ! "
❝ከጋብቻ ያስፈራሩሃል፤ከዝሙት ግን አያስፈራሩህም።❞
@yasin_nuru
@yasin_nuru

September 23, 13:37

ረመዷን 4ወራት ከቀናት ይቀሩታል።
#Terawih
#Suhur
#The
doors of jannah will be open
#Iftar
#Shaytan
❌
#RAMADAN
🥰
❤
@yasin_nuru
@yasin_nuru

September 22, 04:52

ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር ( ረድየሏሁ ዓንሁማ) ከዕለታት አንድ ቀን ሚስቱን ፈታት።
እሷም
፦ «ከእኔ የምትጠላውን ነገር አይተህብኛልን?» ስትል ጠየቀችው።
እሱም፦
«አልየሁም» አላት።
እሷም፦
«ታዲያ ምን አግኝተህ ነው አንዲትን ንጹሕ እና ትእግስተኛ የሆነች ሙስሊም ሴት የምትፈታው?!» አለችው።
ኢብኑ ዑመርም (የሷ ንግግር ልቡን ነክቶት) ከፍቺው ተመለሰ።
📕
ምንጭ-ሱነን ሰዒድ ኢብኑ መንሱር፡
1099)
@yasin_nuru
@yasin_nuru

September 19, 07:53

አስተውል........
👉
‹‹ፍቅር ማለት በሀላል ተገናኝተህ የምትመሰርተው ትዳር ውስጥ የምታገኘው ምድራዊ ገነት ነው።›
..........
👉
‹ባልሽ ግማሹን ኢማንሽን ሊሞላልሽ የሚፈልግ ሲሆን ከኒካህ በፊት የሚገኝ ጓደኛ ግን ቀሪውን ህይወትሽን ለማበላሸት የሚፈልግ ነው፡፡››
..........
👉
‹ዲኑንና ባህሪውን (አኽላቁን) የምትወዱለት ሰው ከጠየቃችሁ አጋቡት ( ካልሆነ በምድር ላይ ፈሳድ ጥፋትና ፊትናን እያንሰራፋችሁ መሆኑን ተገንዘቡ)፡፡›› ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ)
.......
👉
‹‹ጋብቻ በኔ ዘንድ የሚወደድ ተግባር ነው፡፡ እኔ ለምወደው ነገር ጀርባውን የሰጠ ለኔ ጀርባውን እንደሰጠ ነው፡፡›› ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ)
........
👉
‹‹በኒካህ (ትዳር በመመስረት) አላህን ታዘዙት፤ቃል የገባላችኁን ይሰጣችኋልና› አቡበከር ሲዲቅ*(ረዲያአላሁ.ዐንሁ).
.......
👉
‹‹ከእናንተ መካከል በላጩ ሰው በሚስቱ መልካም አያያዝ*በላጫችሁ ነው›› ረሱል (አለይሂ ሠላቱ ወሠላም))
@yasin_nuru
@yasin_nuru

September 18, 18:51
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

በቁርኣን ውስጥ የመዲና ስም ማን ነው?
@yasin_nuru
@yasin_nuru

September 17, 14:37

"ወደ ቢሊየነርነት የሚያመሩ፣ በትንሽ ካፒታል ተጀምረው ትልቅ ተስፋ ያላቸውን 30 ዘመናዊ የቢዝነስ አማራጮች ለሚሊነሮች "
1.ዘመናዊ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ
🔸
ቦታ፦ የእንስሳት እርባታ ባለባቸው የከተማ ዳርቻዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "በ3 ወር የላምዎን ወተት በእጥፍ ይጨምሩ የሚል ቪዲዮ::
2.ዘመናዊ የሸክላና የሴራሚክ ውጤቶች ማምረቻ
🔸
ቦታ፦ የሸክላ አፈር በብዛት በሚገኝባቸው ገጠራማ ከተሞች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ባህልና ዘመናዊነት በአንድ ላይ" በሚል ውብ የጌጥ እቃዎችን ማስተዋወቅ።
3.የታሸገ የተፈጨ በርበሬና ቅመማ ቅመም ፋብሪካ
🔸
ቦታ፦ ለጥሬ እቃ ምንጭ ቅርብ በሆነ የኢንዱስትሪ ዞን።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ከቆሻሻና ከቀለም ነፃ" በሚል ንፅህናውን በላብራቶሪ ምርመራ ማሳየት።
4.የተጣራ የሱፍና የኑግ ዘይት ማምረቻ
🔸
ቦታ፦ የሰሊጥና የኑግ ምርት ባለባቸው አካባቢዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ለጤናዎ ቅድሚያ—ሳይቀላቀል የመጣ ዘይት" በሚል የምርት ሂደቱን ማሳየት።
5.ዘመናዊ የዶሮ መፈልፈያ (Hatchery)
🔸
ቦታ፦ መለስተኛ የአየር ንብረት ባለባቸው ቦታዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ጥራት ያላቸው ዝርያዎችን በብዛት እናቀርባለን" በሚል ለገበሬዎች ስልጠና መስጠት።
6.የፕላስቲክ መስኖ እቃዎች ማምረቻ (Drip Irrigation)
🔸
ቦታ፦ ግብርና በስፋት በሚሰራባቸው አካባቢዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "በጥቂት ውሃ ብዙ ምርት" የሚል የመስኖ ውጤት ማሳያ ቪዲዮ።
7.ዘመናዊ የቡና ቆሎና ፓኬጅንግ
🔸
ቦታ፦ የንግድ ማዕከላትና ወደ ውጭ መላኪያ መጋዘኖች አካባቢ።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "የኢትዮጵያን ቡና በብራንድ" በሚል ማራኪ ማሸጊያዎችን ማሳየት።
8.የዱቄትና የጥራጥሬ ፋብሪካ
🔸
ቦታ፦ ስንዴና በቆሎ በሚመረትባቸው አካባቢዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ለዳቦ ቤቶችና ለቤተሰብ የታሸገ ጥራት" በሚል ጅምላ ሻጮችን መሳብ።
9.ዘመናዊ የንፅህና መጠበቂያ (ቲሹና ሶፍት) ፋብሪካ
🔸
ቦታ፦ ለውሃና ለትራንስፖርት ምቹ የሆኑ የኢንዱስትሪ ቦታዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ለስላሳና ጥንካሬ ያለው" በሚል በቲክቶክ ላይ ጥራቱን መፈተሽ።
10.የፀሀይ ብርሃን የውሃ ፓምፖች (Solar Pumps)
🔸
ቦታ፦ ውሃ በራቀባቸው የእርሻ መሬቶች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ያለ ነዳጅና ያለ ኤሌክትሪክ እርሻዎን ያጠጡ" የሚል የቆጠባ ዘዴ።
11.ዘመናዊ የቆዳ ጫማ ማምረቻ
🔸
ቦታ፦ ለቆዳ ፋብሪካዎች ቅርብ በሆኑ ከተሞች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "የሀገር ውስጥ ምርት ከኢታሊያ ጥራት ጋር" በሚል ዲዛይኖችን ማሳየት።
12.የታሸገ የተፈጥሮ ማዕድን ውሃ
🔸
ቦታ፦ የተፈጥሮ ፍልውሃ ወይም የከርሰ ምድር ውሃ ባለባቸው አካባቢዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ንፅህናው የተጠበቀና ማዕድን የበዛበት" በሚል የፋብሪካውን ሂደት ማሳየት።
13.ዘመናዊ የቤት እቃዎች ማምረቻ (MDF Furniture)
🔸
ቦታ፦ አዳዲስ ከተሞችና ግንባታ በሚበዛባቸው አካባቢዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "የቱርክ ዲዛይን በሀገር ውስጥ ዋጋ" በሚል ውበቱን ማሳየት።
14.የአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ (Juice & Jam)
🔸
ቦታ፦ ለፍራፍሬ እርሻዎች ቅርብ በሆኑ ቦታዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ያለ ስኳርና ኬሚካል የተዘጋጀ" በሚል ጤናማነትን መስበክ።
15.ዘመናዊ የእንጨት ውጤቶች (parquet/plywood)
🔸
ቦታ፦ የደን ሀብትና የኢንዱስትሪ ዞን ባለባቸው አካባቢዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ቤትዎን በውድ እቃዎች ያስውቡ" በሚል ዲዛይን ማሳየት።
16.የግንባታ ኬሚካሎች ማምረቻ (Paint & Glue)
🔸
ቦታ፦ የግንባታ ግብአት ማከፋፈያ አካባቢዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ቀለም አይለቅም፣ ግድግዳ አይሰነጠቅም" በሚል ጥራቱን ማሳየት።
17.ዘመናዊ የልብስ ስፌትና ጋርመንት
🔸
ቦታ፦ ለሰው ሃይልና ለገበያ ምቹ የሆኑ ቦታዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ለድርጅቶችና ለትምህርት ቤቶች ጥራት ያለው ዩኒፎርም" በሚል መቅረብ።
18.የወረቀትና የካርቶን ማሸጊያ ፋብሪካ
🔸
ቦታ፦ ሌሎች ፋብሪካዎች በብዛት በሚገኙበት አካባቢ።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ምርትዎን በዘመናዊ ካርቶን ያስውቡ" በሚል ቢዝነስ ለቢዝነስ (B2B) መስራት።
19.የኤሌክትሪክ ገመድና መለዋወጫ ማምረቻ
🔸
ቦታ፦ የኤሌክትሪክ ኃይልና ጥሬ እቃ በሚገኝበት የኢንዱስትሪ ዞን።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ደህንነቱ የተጠበቀና እሳት የማይፈራ" በሚል ጥንካሬውን ማሳየት።
20.ዘመናዊ የእብነበረድና የድንጋይ መቁረጫ
🔸
ቦታ፦ ለማዕድን ማውጫዎች ቅርብ በሆኑ ቦታዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ተፈጥሮአዊ ውበት ለቤትዎ ወለል" በሚል ቪላ ቤቶችን መሳብ።
21.የታሸገ ማርና የንብ ሰም ኤክስፖርት
🔸
ቦታ፦ ከፍተኛ የማር ምርት ባለባቸው የደጋ አካባቢዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ኦርጋኒክ ማር ለዓለም ገበያ" በሚል በቲክቶክ ላይ ሂደቱን ማሳየት።
22.የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክልና ባጃጅ መገጣጠሚያ
🔸
ቦታ፦ የትራንስፖርት መጨናነቅ ባለባቸው የንግድ ከተሞች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ነዳጅ መፈለግ አበቃ—በቻርጅ ብቻ ይጓዙ" በሚል የቆጠባ ስሌትን ማሳየት።
23.የመኪና ባትሪና ጎማ ማደሻ
🔸
ቦታ፦ የመኪና ጥገና በብዛት በሚሰራባቸው መገንጠያ መንገዶች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "የቆየውን ባትሪዎን አድሰን ዋስትና እንሰጣለን" በሚል የቁጠባ ዘዴ።
24.ዘመናዊ የመስኖ ግድብና ጉድጓድ ቁፋሮ
🔸
ቦታ፦ ግብርና በስፋት በሚሰራባቸው ቆላማ አካባቢዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "በበጋም በክረምትም ምርታማ ይሁኑ" በሚል ገበሬዎችን መሳብ።
25.የእንስሳት መድኃኒትና ክትባት አቅርቦት
🔸
ቦታ፦ የእርባታ ማዕከላት በብዛት ባሉባቸው ከተሞች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "እንስሳትዎ እንዳይሞቱባችሁ ቀድመው ይከተቡ" በሚል ግንዛቤ መፍጠር።
26.ዘመናዊ የህፃናት አልሚ ምግቦች ማቀነባበሪያ
🔸
ቦታ፦ ለጥራጥሬ ምርት ቅርብ የሆኑ የንግድ ማዕከላት።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ጤናማ ትውልድ በኦርጋኒክ ምግብ" በሚል የእድገት ለውጥን በምስል ማሳየት።
27.የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማቀነባበሪያ (Compost)
🔸
ቦታ፦ ከእርሻ ተረፈ ምርት የሚገኝባቸው አካባቢዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "መሬትዎን ሳያበላሹ ምርትዎን ይጨምሩ" የሚል ኦርጋኒክ ዘዴ።
28.ዘመናዊ የቤት ውስጥ መብራትና ጌጣጌጥ (LED)
🔸
ቦታ፦ ግንባታና ማስዋብ በሚበዛባቸው የንግድ ቦታዎች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ቤትዎን በብርሃን ይቀይሩት" በሚል ምሽት ላይ የሚያማምሩ ቪዲዮዎችን ማሳየት።
29.የተጣራ ጨውና አዮዲን ማሸጊያ
🔸
ቦታ፦ ለጨው ማዕድን ቅርብ በሆኑ መጋዘኖች።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "ለቤተሰብዎ ጤና ንፁህ ጨው" በሚል ግንዛቤ መፍጠር።
30.ዘመናዊ የእቃ ማጓጓዣና ፓኬጅንግ (Logistics)
🔸
ቦታ፦ የጭነት መኪናዎች መነሻና መድረሻ ላይ።
🔹
ሰው መሳቢያ፦ "እቃዎ በፍጥነት እና በታማኘት እናደርሳለን" በሚል እምነት መገንባት።
🔺
ሀብት ማለት የገንዘብ ክምችት ብቻ ሳይሆን፣ የሰዎችን ችግር በዘመናዊ መንገድ መፍታት ነው። ከላይ የተጠቀሱት 30 ዘርፎች በሀገራችን ገበያ ላይ ከፍተኛ ክፍተት ያለባቸውና ተፈላጊ የቢዝነስ ሃሳቦች ናቸው። ስኬት የሚመጣው በመመኘት ብቻ ሳይሆን በመጀመር ነው።
#copied
@yasin_nuru
@yasin_nuru

September 16, 09:08

⚠️
በኢስላም የሴት ልጅ ክብርና መብቶች[ኢስላም ሴትን ልጅ እንዴት አከበራት?]
⁉️
ብዙዎች "
ስልጣኔ
" ብለው በሚጠሩት ዓለም ውስጥ ሴት ልጅ እንደ ሸቀጥ ስትታይ፤ ኢስላም ግን
ከ1,400
ዓመታት በፊት የሚከተሉትን መለኮታዊ መብቶች ሰጥቷታል፦
1️⃣
ከታማኝነት አኳያ፦
አንድ ያገባ ወንድ ሚስቱን አታልሎ ዝሙት ቢፈጽም ቅጣቱ እስከ ሞት ድረስ  ተቀጥቅጦ መገደል ነው።
2️⃣
ከፍትህ አኳያ፦
ከአንድ በላይ አግብቶ በመካከላቸው ፍትሃዊ ካልሆነ፤ በትንሣኤ ቀን አንድ ጎኑ ሽባ ሆኖ ይቀሰቅሳል።
3️⃣
ከመህር አኳያ፦
መህሯን (የጋብቻ ስጦታዋን) ወስኖ ካልሰጣት፤ አላህ ዘንድ እንደ "ሌባ" ይቆጠራል።
4️⃣
ከፍቺ በኋላ፦
ቢፈታት እንኳ የሰጣትን ስጦታዎች መልሶ የመውሰድ መብት የለውም።
5️⃣
ከውርስ አኳያ፦
የውርስ መብቷን የበላ የአላህን ድንበር ተላልፏል፤ ራሱንም በድሏል።
6️⃣
ከስነ-ምግባር አኳያ፦
ሚስቱን የሚያዋርድና የሚመታ እርሱ "ክፉ/ወራዳም" ነው፤ የሚያከብራት ደግሞ "ክቡር" የተከበረ ነው።
7️⃣
ከመብት አኳያ፦
ያላንዳች ምክንያት ከአራት ወር በላይ ትቷት ከራቀ፤ የመለያየት (የመፈታት) መብት አላት።
8️⃣
ከክብር አኳያ፦
እንደ እናቱ በመቁጠር (ዚሃር)አድርጎ ቢርቃት፤ ለቅጣቱ 60 ቀን መጾም ወይም 60 ምስኪን መመገብ አለበት።
9️⃣
በትዕግስት አኳያ፦
ቢጠላት እንኳ ይታገሳት፤ አላህ እርሷ ዘንድ ብዙ መልካም ነገርን ሊያደርግ ይችላልና ተብሏል።
🔟
ከመለያየት በኋላ፦
ቢፈታት እንኳ የነበራትን ውለታና መልካም ነገር መዘንጋት የለበትም።
11
ከልጆች አኳያ፦
ቢለያዩ እንኳ ልጆቿን ሊነጥቃት አይገባም፤ ወጪያቸውንም የመሸፈን ግዴታ አለበት።
12
ከገንዘብ አኳያ፦
የራሷ ገንዘብ ባለቤት ናት፤ ለባሏ ሰደቃ ብትሰጥ ድርብርብ አጅር አላት፣ ካልፈለገች ግን ሊነካባት አይችልም።
13
ከጥቃት አኳያ፦
በእሷ ላይ የሚፈጸም ማንኛውም ጥቃት ልክ በእሱ ላይ እንደተፈጸመ ተቆጥሮ ይቀጣል።
14
ከመተዳደሪያ አኳያ፦
እንደ አቅሙ ምግቧን፣ መጠጧን፣ ልብሷንና መጠለያዋን የማሟላት ግዴታ አለበት።
15
ከአመራር አኳያ፦
እሱ እሷን የመንከባከብ ኃላፊነት (ተክሊፍ) አለበት፤ እሷ ለእሱ (በመልካም ነገር) መታዘዟ በአላህ መንገድ እንደ መታገል (ጂሃድ) ይቆጠርላታል።
16
ከጋሻነት አኳያ፦
ለእሷ ክብር ሲባል ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በበኑ ቀይኑቃዕ ላይ ጦርነት አውጀዋል።
17
ከመሥዋዕትነት አኳያ፦
የእሷን ክብር ለመከላከል ሲል የሞተ ሰው "ሸሂድ" (መሥዋዕት) ይባላል።
18
ከጀግንነት አኳያ፦
ለአንዲት ሴት ጩኸት ሲል "አል-ሙዕተሲም" ታላቅ ጦርን አንቀሳቅሷል።
19
ከሰብዕና አኳያ፦
ስሟን ላጠፋና ላናወረ ሰው 80 ግርፋት እንዲገረፍ አላህ ህግ ደንግጓል።
20
ከመታዘዝ አኳያ፦
በመልካም ነገር ካዘዛት ትታዘዘዋለች፤ አላህን በሚያስቆጣ ነገር ግን "ለፈጣሪ በማመጽ ለፍጡር መታዘዝ የለምና "።
⚠️
ይህ ነው እንግዲህ በኢስላም የሴት ልጅ መብት!
⁉️
ለመሆኑ ሴትን ልጅ "
ነጻ አወጣን
" በሚሉ የምዕራባውያን አስተሳሰቦችም ሆነ በሌሎች ሃይማኖቶች ውስጥ እንዲህ ያለ ክብር የት ይገኛል?
ይህንን መረጃ ለሴት ልጆቻችሁ አሳውቋቸው፤ በዲናቸው እንዲኮሩና መብታቸውን እንዲያውቁ አስተምሯቸው። በዚህ ዘመን በባህልና በባዕድ አስተሳሰብ እንዳይዋጡ የዲን እውቀት ጋሻ ይሁናቸው።
ያ አላህ! በእውነት ላይ አጽናን፤ እህቶቻችንንም በዲናቸው ኩሩዎችና ጠንካራዎች አድርጋቸው።
Abu_hibetillah
@yasin_nuru
@yasin_nuru

September 14, 09:49

🔆
#ካህሊል_ጂብራን
🔆
🔱
‹‹ ቁንጅና ያለው ፊት ላይ አይደለም፡፡ ቁንጅና በውስጣችን የሚገኝ የልብ ብርሃን ነው፡፡ ››
🔱
‹‹ አዋቂ ሠው ሁለት ልብ አለው፡፡ አንዱ ሲደማበት በሁለተኛው ይታገሳል፡፡››
🔱
‹‹ እምነት እውነትነቱን ከማረጋገጥ ባሻገር በልብ ውስጥ የሚገኝ እውቀት ነው፡፡ ››
🔱
‹‹ ኢምንቷ የደግነት ስራ ትልቁን ነገር ለማድረግ ከማሰብ በላይ ዋጋ አላት፡፡ ››
🔱
‹‹ ፍቅር የሚያንቀጠቅጥ ደስታ ነው፡፡ ››
🔱
‹‹ እውነት እርቃኑን በባዶው መራመድ ይችላል፡፡ ውሸት ግን ሁልጊዜ አምሮና ደምቆ መልበስን ይፈልጋል፡፡ ››
🔱
‹‹ ኩሩ መሆን ማለት ከምትፈልገው በታች መውሰድ ማለት ነው፡፡ ››
🔱
‹‹ ፍቅር የመለያያ ሠዓቱ እስኪደርስ ድረስ የራሱን ጥልቀት አይረዳም፡፡ ››
🔱
‹‹ ወንድ ሁለት ሴቶችን ይወዳል፡፡ አንደኛዋ በአዕምሮው የሚስላት ስትሆን ሁለተኛዋ ግን ገና አልተወለደችም፡፡ ››
🔱
‹‹ ልክ እንደ አበባ ሁን፡፡ ፊትህን ወደ ፀሃይ ብርሃን አዙር፡፡ ››
🔱
‹‹ ሐዘንና ደስታ የማይነጣጠሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ሁለቱም አብረው ይመጣሉ፡፡ ነገር ግን አንዱ ብቻውን ከጎንህ ሲሆን አንደኛው መኝታ ቤትህ እንደተጋደመ አትርሳ፡፡››
🔱
‹‹ በአንድ ሕይወት ውስጥ ወደ ኋላ እየተመለከቱ መደሠት መቻል ሁለቴ መኖር ማለት ነው፡፡ ››
🔱
‹‹ ፍቅርና ደግነት የድክመትና የተስፋ መቁረጥ ምልክቶች ሳይሆኑ የጥንካሬና የውሳኔ ሠጪነት መገለጫ ናቸው፡፡
🔱
‹‹ ትናንት ለዛሬ ትዝታ ነው፡፡ ነገ ደግሞ የዛሬ ህልም ነው፡፡ ››
🔱
‹‹ ጓደኛህ የፍላጎትህ መልስ ነው፡፡ ››
🔱
‹‹ የሠውን ልጅ ልብና አዕምሮ ለመረዳት እስካሁን ያሳካቸውን አትይ፡፡ ከእሱ ይልቅ ወደፊት ሊያደርጋቸው እና የሚመኛቸውን ተመልከት፡፡ ››
🔱
‹‹ የምትወደውን ሠው የፈለገበት ይሄድ ዘንድ ተወው፡፡ ሄዶ ወደአንተ ከተመለሠ ቀድሞውኑ ያንተ ነበር፡፡ ካልተመለሠ ግን ቀድሞውኑም የአንተ አልነበረም፡፡ ››
🔱
‹‹ ልክ ወንዝና ባህር አንድ እንደሆኑት ሁሉ ሕይወትና ሞትም አንድ ናቸው፡፡
🔱
‹‹ ጓደኝነት የሁልጊዜ ጣፋጭ ሃላፊነት እንጂ አጋጣሚ አይደለም፡፡ ››
#የትኛው_መቻችሁ
።
@yasin_nuru
@yasin_nuru

September 13, 12:44

🪴
ኢስቲቃማን እንዴት እናምጣ?
በእስልምና ኢስቲቃማ (الاستقامة) ማለት በአላህ ትእዛዝ ላይ ጸንቶ መቆም፣ ከኃጢአት መራቅና በመልካም ሥራ ላይ መቀጠል ነው። በነገራችን ላይ ኢስቲቃማ ማምጣት በተለይ በችግር ጊዜ ትልቅ መፍትሔ ነው።
💎
ነገር ግን ኢስቲቃማ ማለት ችግር ፈጽሞ አይመጣም ማለት አይደለም፤ ችግር ሲመጣ በአላህ ላይ ተማምኖ፣ በትዕግሥትና በትክክለኛ መንገድ መቆም ነው።
ኢስቲቃማን እንዴት እናምጣ?
1. እምነትን ማስተካከል – ተውሂድን ማጠናከርና ልብን ከአላህ ጋር ማያያዝ።
2. ግዴታዎችን መጠበቅ – በተለይ አምስቱን ሶላቶች በጊዜያቸው መስገድ።
3. ኃጢአትን መተው – ትንሽ ነው ብሎ ኃጢአትን አለመናቅ።
4. በቁርአንና በሱና ላይ መጠንከር።
5. ዱዓን ማብዛት። ነቢዩ ﷺ በብዛት ይሉ ነበር፦
«يا مقلب القلوب ثبت قلبي على دينك»
“የልቦች ቀያሪ ሆይ! ልቤን በዲንህ ላይ አጽናው።”
6. መልካም ጓደኞችን መምረጥ – ሰው በሚያደርገው አካባቢና ጓደኛ በጣም ይጎዳል ወይም ይጠቀማል።
7. ትንሽ ትንሽ ቢሆንም በመልካም ሥራ መቀጠል። ዋናው ነገር ብዙ ጀምሮ ቶሎ መተው ሳይሆን በቀጣይነት መሥራት ነው።
አላህ ሲል፦
> ﴿إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا﴾
“ጌታችን አላህ ነው ካሉ በኋላም ጸኑ፣ መላእክት በእነርሱ ላይ ይወርዳሉ፤ ‘አትፍሩ፣ አትዘኑም’ ይሏቸዋል።” (ፉሲለት 41፥30)
ስለዚህ ኢስቲቃማ በችግር ላይ የሚሰጠን መፍትሔ ነው፣ ነገር ግን ችግሩን በአንድ ጊዜ የሚያጠፋ ፈጣን መፍትሔ አይደለም። ችግሩን እንዴት እንደምንጋፈጠው የሚያስተካክል የልብ ጥንካሬና የሕይወት መንገድ ነው።
@yasin_nuru
@yasin_nuru