Select your region
and interface language
We’ll show relevant
Telegram channels and features
Region
avatar

وذكر አስታውስ

abdulhafiz_mitiku
ለማንኛውም አስተያየት ለጥያቄ ለጥቆማ @ABU_Atiika
Subscribers
1 060
24 hours
6
30 days
16
Unusual 24 hours growth
Post views
205
ER
19,34%
Posts (30d)
7
Characters in post
152
Insights from AI analysis of channel posts
Channel category
Religion and Spirituality
Audience gender
Female
Audience age
25-34
Audience financial status
Middle
Audience professions
Education
Summary
August 24, 18:42
Media unavailable
1
Show in Telegram

"ሴትን ልጅ በባሏ ላይ ያሳመፀ ከኛ አይደለም"
ዐለይሂ አፍደሉ ሰላቲ ወሰላም

August 21, 14:28
Media unavailable
1
Show in Telegram

"ጌታቹን እስክትገናኙ ድረስ ታገሱ በናንተ ላይ ዘመን አይመጣም ከሱ ቡሃላ ያለው የባሰ መጥፎ ቢሆን እንጂ"
ቡኻሪይ ዘግበውታል

August 11, 18:38
Media unavailable
1
Show in Telegram

ከነገራት ሁሉ ታላላቆቹ ሶስት ናቸው
1. ያለችን ትንሽ ብትሆንም ከሷ ላይ መለገስ
2. ብቻችን በተገለልን ወቅት አላህን መፍራት
3. የሚከጀል ና ሚፈራ አካል ዘንድ ሃቅን መናገር

August 06, 05:32
Media unavailable
1
Show in Telegram

"ተውበት ማለት /ወንጀል ላይ/ መዘውተርን መተው ነው " ማለት ነው ይላሉ ሃፊዝ ኢብኑ ረጀብ
አላህ ሙተቆችን ፈሪሀ አላሆችን በቁርአኑ ሲገልፅ መጥፎ ነገር ሰርተው ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን አስታውሰው መሀርታውን ሚጠይቁና በስራቸው ላይ ያልዘወተሩ ናቸው የሰው ልጅ ወንጀል ከመስራት ሊድን አይችልም ዛሬ ተውበት አርጎ ነገም ሊወነጅል ይችላል ፈሪሀ አላሆችን ከሌላው የሰው ልጅ ሚለያቸው ግን ወንጀልን ሲሰሩ ውስጣቸው ይረበሻል ምድር ከመስፋቷጋ ትጠባቸዋለች ወዲያውም የተናነሱ ሆነው ማያልቅ ወደሆነው ወደ ጌታቸው መሀርታ ክጃሎት ይመለሳሉ ጌታቸውም አያሳፍራቸውም ወንጀላቸውን መማር ብቻ ሳይሆን ያንኑ ወንጀል አላህ ወደ መልካም ስራ ቀይሮ ይፅፍላቸዋል
አቡ ዘር እንዳስተላለፉ "የቂያማ ቀን አንድን ሰው ወደ አላህ ይመጣል ጌታውም የባሪያዬን ትናንሽ ወንጀሎች አቅርቡለት ይላል ይህን ይህን ፈፅመሃል ይባላል እሱም ማስተባበል አይቻለውም ትላልቅ ወንጀሎቹን እያሰበ ይጨነቃል በሁሉም ወንጀሎችህ ቦታ መልካም ስራ ተቀይሮልሃል ሲባል ግን ጌታዬ እዚህ ማላያቸው የተለያዩ ወንጀሎችን ሰርቻለው ይላል ከዛም የአላህ መልክተኛ ድዶቻቸው እስኪታዩ ሳቁ"
ሙስሊም ዘግበውታል
ኢማም ዐሊይ ዐለይሂ ሰላም እንዲህ አሉ "ከናንተ በላጩ /በወንጀል/ ተፈትኖ ተውበት ያረገው ነው ወደ ወንጀሉ ከተመለሰስ ተባሉ አላህን መሀርታ ይጠይቃል ወደሱም ይመለሳል አሉ እስከሚሞት አሉዋቸው ከሳሪው አዛኙ ሸይጣን እስኪሆን ድረስ አሉ"

August 05, 04:31
Media unavailable
1
Show in Telegram

ሸይጣን በሰዎች ላይ ሚገባባቸው ዋነኛዎቹ በሮች ሶስት ናቸው ይላሉ
1. ዝንጉነት
2. ስሜት
3. ቁጣ

August 04, 18:48

"በምቾትም በችግርም ወቅት በሚወደውም በማይወደውም ነገር ላይ በዒባዳ ላይ የፀና ፍራቻና ሀዘን ከሌለባቸው ባሪያዎች ውስጥ ይሆናል"
ሙኽተሰር ፊቂሀል ኢስላሚይ

August 03, 04:33

"ስለ ተቅዋ አላህን መፍራት ሚመክሩ ብዙ ናቸው ሚተገብሩ ግን ጥቂት ናቸው"
አሚሩል ሙዕሚኒን ዑመር ኢብኑ አብዱልዐዚዝ

July 27, 05:14

"አንተ ዘንድ ወንጀልህ ቀሎ በታየህ ቁጥር አላህ ፊት ይገዝፋል አንተ ዘንድ በገዘፈ ቁጥር አላህ ፊት ይቀላል"
ፉደይል ኢብኑ ዒያድ

July 22, 16:34

"ኸይር ነገራት 3 ናቸው በአላህ ማመን ዲንን መማርና ሷሊህ የሆነች ሚስት"
ኢማም ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ ዐለይሂሰላም

July 22, 05:27

ከባዱና ትልቅ ኢማን ሚጠይቀው ነገር በአስቸጋሪ ወቅቶች ወደ አላህ ከመሸሽ በላይ በምቾት ገዜያት ወደ አላህ መሸሽ ነው