
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
🟢
ማንን ፈልገህበት ነው?
በአሽሙር ሰለፊዮችን የሚወጋን እና ለማንቋሸሽ ዳር ዳር የሚለውን ስትሰማው "
እውነተኛ መካሪ ከሆንክ ማንን ፈልገህበት ነው?
" "ማነው ይህን የተናገረው "በለው። ጀግና ከሆነ ለምን ይፈራል?!
እንደ ኤሊያስ 30ምክሮች መካሪ መስሎ መሰሪ ሊሆን ይችላልና ተጠንቀቀው።
👉
በዚህች የኢብኑልቀይም ምክርም ገስፀው፡
"فَعَليكَ بالتَّفْصِيلِ والتَّمييزِ فالـ ... إِطْلَاقُ والإجْمَالُ دُونَ بَيَانِ
قَدْ أَفْسَدَا هَذَا الوُجودَ وَخَبَّطَا الـ ... أَذْهَانَ والآراءَ كُلَّ زَمَانِ"
📜
(الكافية الشافية في الانتصار للفرقة الناجية)
አደራህን ዘርዝርና ለየው
ድፍንና ጥቅል የምታማስለው
ዓለም አበላሸ አደበላለቀው
ግራ ማጋባቱ የተለመደ ነው
http://t.me/Abuhemewiya
👉
ኢስቲግፋር ከማብዛት አለመዘናጋት !
አንድ ሙእሚን መልካም ስራ ሰርቻለሁ ብሎ ሊመፃደቅ አይገባውም ። የትኛውም ያክል መልካም ስራ ቢሰራ ከወንጀል መራቅ ስለማይችል ሁል ጊዜ ኢስቲግፋር ሊያበዛ ይገባል ። ሙእሚን እንደማንኛውም ሰው በአይኑ ፣ በጆሮው ፣ በእጁ ፣ በምላሱ ፣ በልቡም ጭምር ወንጀል ሊሰራ ይችላል ። በየትኛውም ሰከንድ አውቆም ይሁን ሳያውቅ ለወንጀል የቀረበ ነውና ። ምናልባት እሱ ቀላል ነው ያለው ንግግር ወይም ተግባር አላህ ዘንድ ከባድ ሆኖ ዱንያውም አኼራውም የሚያጠፋ ሊሆን ይችላል ።
አላህ ለዚህ ነው ይህን አስመልክቶ በመለኮታዊ ቃሉ እንዲህ ያለን : –
{ إِذْ تَلَقَّوْنَهُ بِأَلْسِنَتِكُمْ وَتَقُولُونَ بِأَفْوَاهِكُم مَّا لَيْسَ لَكُم بِهِ عِلْمٌ وَتَحْسَبُونَهُ هَيِّنًا وَهُوَ عِندَ اللَّهِ عَظِيمٌ }
سورة النور ( 15 )
" በምላሶቻችሁ በምትቅበባሉት ጊዜ ለእናንተም በእርሱ ዕውቀት በሌላችሁ ነገር በአፎቻችሁ በተናገራችሁና እርሱ አላህ ዘንድ ከባድ ኀጢአት ኾኖ ሳለ ቀላል አድርጋችሁ ባሰባችሁት ጊዜ (ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር )" ፡፡
አንድ ሙእሚን የሚናገረውም ሆነ የሚሰራውን ሒሳብ ማድረግ ይኖርበታል ። ነገር ግን አዛኙ አምላካችን ይህ ከባድ እንደሚሆንበት ስለሚያውቅ በማንኛውም አጋጣሚ ኢስቲግፋር በማድረግ ወንጀሉን እንዲምረው መጠየቅ እንዳለበት ይነግረዋል ። ስለኢስቲግፋር የመጡ የቁርኣንና ሐዲስ ኑሱሶች ተቆጥረው አይዘለቁም የተወሰኑትን ለማየት :–
{ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيم }
سورة الزمر ( 53 )
" በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና "፡፡
ይህ ከአላህ ለአማኞች የተሰጠ ትልቅ የተስፋ ቃል ነው ። ከወንጀል እራሳችንን መጠበቅ ካቃተን ኢስቲግፋር ማድረግ እንዴት ያቅተናል ? አላህ ምህረትን ጠይቁኝ እያለን ?
ለዚህ ነው የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – እኔ በቀን ከሰባ እስከ መቶ ጊዜ ወደ አላህ ተመልሼ ምህረት እጠይቃለሁ ያሉት ። ይህንንም በሚከተለው አቡ ሁረይራ ባወሩትና ኢማሙ ቡኻሪ በዘገቡት ሐዲስ እናገኘዋለን : –
عن أبي هريرة رضي الله عنه سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول :–
" والله إني لأستغفر الله وأتوب إليه في اليوم أكثر من سبعين مرة "
رواه البخاري
የአለህ መለእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም –እንዲህ ይላሉ : –
" በአላህ ይሁንብኝ እኔ በቀን ከሰባ ጊዜ በላይ ወደ አላህ ተመልሼ ምህረትን እጠይቃለሁ " ።
በሌላ አቡ ሁረይራ ባወሩትና ኢብኑ ማጃህ በዘገቡት ሸኽ አልባኒ ሶሒህ ባሉት ሐዲስ ደግሞ እንዲህ ይላሉ :–
" إني لأستغفر الله وأتوب إليه في اليوم مائة مرة "
رواه ابن ماجه وصححه الألباني
" እኔ በቀን መቶ ጊዜ ወደ አላህ ተመልሼ ምህረትን እጠይቃለሁ " ።
ይህ እንግዲህ እሳቸው ያለፈውም የሚመጣውም ወንጀልህ ተምረሃል ተብለው ሳለ ነው ። !!!! እኛስ ምን ያክል ጊዜ ይበቃናል ?
ስራችን አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ከተለያዩ ስራን ከሚያበላሹ የወንጀል ቆሻሻዎች ለመፅዳት ኢስቲግፋር ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው ። ኢስቲግፋር ወንጀልን ለማሳበስ ብቻ አይደለም ጠቀሜታው ለተለያዩ ዱንያዊ ችግሮችንም ለመፍታት መፍትሄ ነው ። ለድርቅ ፣ ለሀብት ፣ ለልጅ ፣ ለሰብል ፣ ለሀይል ( ለአቅም ) እና ለመሳሰሉት እጦት ብቸኛ መፍትሄ መሆኑ በሚከተሉት የቁርኣን አንቀፆች መመልከት ይቻላል ።
{ فَقُلْتُ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ إِنَّهُ كَانَ غَفَّارًا }
سورة نوح ( 10)
«አልኳቸውም ፡- ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት ፡፡ እርሱ በጣም መሐሪ ነውና " ፡፡
{ يُرْسِلِ السَّمَاءَ عَلَيْكُم مِّدْرَارًا }
سورة نوح ( 11)
«በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል" ፡፡
{ وَيُمْدِدْكُم بِأَمْوَالٍ وَبَنِينَ وَيَجْعَل لَّكُمْ جَنَّاتٍ وَيَجْعَل لَّكُمْ أَنْهَارًا }
سورة نوح ( 12 )
«በገንዘቦችና በልጆችም ይለግሰላችኋል፡፡ ለእናንተም አትክልቶችን ያደርግላችኋል ፡፡ ለእናንተም ወንዞችን ያደርግላችኋል ፡፡»
{ وَيَا قَوْمِ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ يُرْسِلِ السَّمَاءَ عَلَيْكُم مِّدْرَارًا وَيَزِدْكُمْ قُوَّةً إِلَىٰ قُوَّتِكُمْ وَلَا تَتَوَلَّوْا مُجْرِمِين َ}
سورة هود ( 52 )
«ሕዝቦቼም ሆይ! ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት ፡፡ ከዚያም ወደርሱ ተጸጸቱ፡፡ ዝናብን በእናንተ ላይ ተከታታይ አድርጎ ይልክላችኋልና ፡፡ ወደ ኃይላችሁም ኃይልን ይጨምርላችኋል ፡፡ አመጸኞችም ሆናችሁ አትሽሹ ፡፡»
እነዚህ የቁርአን አንቀፆች አማኞችን ወደ ኢስቲግፋር የሚጠሩና ከዱንያዊ ችግራቸው በኢስተግፋር መላቀቅ እንደሚችሉ ያመላክታሉ ። ልጅ ያጣ ፣ ሀብት ያጣ ፣ በድርቅ የተሰቃየ ፣ አቅም ያጣ ፣ ዝናብ ጠፍቶ ሰብል ወድሞ የተራበ ገበሬ ፣ ወደ አላህ ምህረት ፍለጋ ኢስቲግፋር ማድረግ በእጁ ያለ መፍትሄ ነው ። በመሆኑም የመልካም ስራችን መጨረሻ ያማረ እንዲሆን ኢስቲግፋር እናብዛ ። አላህ ወንጀላቸውን ምሮ ስራቸውን ከተቀበላቸው ባሮቹ ያድርገን ።
http://t.me/bahruteka
🚫
ስለ ኢኽዋን ምን ታውቃለህ
⁉️
ኢኽዋን የሚባለው ቡድን ግብፅ ውስጥ የተቋቋመ የፖለቲካ ድርጅት ሲሆን ፖለቲካዊ አላማውን ለማሳካት የትኛውንም አማራጭ ይጠቀማል ። ከፈለገ እንደ እስስት መልኩን ይቀይራል, ከፈለገ ሐራምን ሐላል ያደርጋል, ከፈለገ ወደ እምነት አንድነት ይጣራል, ከፈለገ አላማውን ለማሳካት የባጢል ጂሃድ ያውጃል ።
ሌላውና አደገኛው መርሁ አል ጋየቱ ቱበሪሩ አል ወሳኢል ( ልትደርስበት ያሰብከው አላማ በዛ መንገድ የምትሰራውን ሀጢያት ሁሉ የተፈቀደ ያደርገዋል ) የሚለው ሲሆን ኢኽዋኖች ያለውን መንግስት ጥለው ወደ ስልጣን ለመውጣት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሰላዮችን ቢበትኑ እነዛ ሰላዮች አላማቸው የላካቸውን ወደ ስልጣን ማምጣት ስለሆነ በስለላው ሂደት ከሴትኛዳሪ ቢያድር ፣ አስካሪ መጠጥ ቢጠጣ ሀላል ይሆንለታል እንደማለት ነው
‼
።
አሁንም ሌላኛው ከሚከተሉት መርህ ውስጥ ነተፊቁ ፊመተፈቅና ፊሂ ወዩዕዚሩ በዕዱና በዕደን ፊመኽተለፍና ፊሂ ( በተስማማንበት እንስማማ ባልተስማማንበት ደግሞ ከፊላችን ለከፊሉ ዑዝር ይስጥ) የሚለው ነው ። ይህ ማለት ከአዩሁድም ፣ ከነሷራም ፣ ከሙሽሪክም ፣ ከቢዳዓ ባለቤትም ጋር መወጋገዝ ፣ መተቻቸት ሳይኖር ፣ አብረን እንስራ የሚል ነው ። እነዚህ የኢኽዋን ማንነቶች ናቸው ዛሬ በተናጠልም በጀማዓም የሚሰሩትን ስራ ሲሰሩ እንድናይ ያደረገን ልብ ያለው ልብ ይበል ።
https://t.me/bahruteka
👉
ሐጅና ህግጋቱ
ክፍል አራት
በሐጅ ስራ አርካን የሆኑ ካልተሰሩ ሐጁ የሚበላሽባቸው ነገሮች እንዳሉና የሐጅ አርካኖችን በክፍል ሶስት አይተናል ። አላህ ካለ በዛሬው ማስታወሻችን ላይ ደግሞ በሐጅ ላይ ዋጅብ የሆኑ ነገሮችን ለማየት እንሞክራለን ። በሐጅ ስራ ላይ ዋጂብ የሚባሉ ነገሮች ከተተዉ ለመጠገን ደም የሚያስወጅቡ የሆኑ ነገሮች ናቸው ። እነርሱም የሚከተሉት ናቸው : –
አንደኛ – ከሚቃት ኢሕራም ማድረግ ። ባሳለፍነው ክፍል እንዳየነው ለሐጅ ወይም ዑምራ ወይም ሁለቱንም ነይቶ ከሀገሩ ወደ መካ ጉዞ የጀመረ ሰው ሚቃት በሚደርስ ጊዜ መነየት ይኖርበታል ። ኢሕራም ማለት በልብ መነየት ማለት ሲሆን ድምፅ አውጥቶ ለበይከ አላሁመ ሐጀን ወይም ሐጀን ወዑምረተን ወይም ለበይከ አላሁመ ዑምረተን የሚባለው በዛ ስራ ውስጥ የተገባ መሆኑን ለማሳወቅ ነው ። በዚህ ጊዜ የሚለበሰው ሁለት የከፈን አይነት ልብስ የኢሕራም ልብስ ነው እንጂ ኢሕራም አይደለም ።
ሁለተኛ – በዓረፋ ሜዳ ላይ ፀሀይ እስጊገባ መቆየት ። በሐጅ ወር ዘጠነኛው ቀን ዐራፋት ላይ መቆም ሩክን መሆኑን አይተናል ። ነገር ግን ፀሀይ እስኪገባ መቆሙ ዋጂብ ነው ። ያለ ዑዝር ፀሀይ ከመግባቱ በፊት ዐራፋትን ለቆ ከወጣ ደም ይወጅብበታል ።
ሶስተኛ – ሙዝደሊፋ ላይ ማደር ። በሐጅ ስራ ላይ ያለ ሰው በዙል ሒጃ ዘጠነኛው ቀን ዐረፋት ላይ ውሎ ፀሀይ ስትገባ ወደ ሙዝደሊፋ ይሄድና መግሪብና ዒሻእን አጣምሮ ይሰግድና እዛው ያድራል ። ይሄ ከሐጅ ዋጂቦች አንዱ ነው ።
አራተኛ – የአያመ ተሽሪቅን ለሊቶችን በሚና ማደር ። አያሙ ተሽሪቅ የሚባሉት የዙል ሒጃ 11ኛ,12ኛ,13ኛ ቀናቶች ናቸው ። አላህ የተቆጠሩ ቀናቶች ብሎ ጠርቷቸዋል ። የእነዚህን ቀናት ለሊቶች ሚና ላይ ማደር ዋጂብ ነው ።
አምስተኛ – ከዙል ሒጃ 10ኛው ቀን ጀምሮ እስከ 13ኛው ቀን ድረስ ሚና ጀመራት በሚባለው ጉድጓድ ላይ ጠጠር መወርወር ። ሐጅ ስራ ላይ ያለ ሰው ሙዝደሊፋ አድሮ ወደ ሚና ይመጣና በ10ኛው ቀን ከጠዋት እስከ ማታ ባለው ክ/ጊዜ ሰባት ጠጠሮችን በጀመረተል ኩብራ ( በመጀመሪያው ጉድጓድ ) አንድ በአንድ ይወረውራል ። በተቀሩት አያመ ተሽሪቅ በሶስቱም ጉድጓዶች በየቀኑ ሰባት ሰባት 21 ጠጠሮችን ይወረውራል ። እየአንዳንዱን ጠጠር ቢስሚላህ አላሁ አክበር እያለ ይወረውራል ። እነዚህን ጠጠሮች በእነዚህ ቀናት መወርወር ከሐጅ ዋጂቦች ውስጥ አንዱ ነው ።
ስድስተኛ – ፀጉርን መላጨት ወይም ማሳጠር
በሐጅ ስራ ላይ ያለ ሰው ስራውን ሲጨርስ ፀጉሩን መላጨት ወይም ማሳጠር ዋጂብ ነው ። ለሐጅ የሚሄድ ሰው የነየተው ተመቱዕ ከሆነ መጀመሪያ ዑምራውን እንደጨረሰ አሳጥሮ ነፃ ከሆነ በኋላ በስምንተኛው ቀን ወደ ሐጅ ስራው ገብቶ ሲጨርስ ቢላጭ ይወደድለታል ።
ስባተኛ – ጠዋፈል ወዳዕ ( የስንብት ጠዋፍ) በሐጅ ስራ ላይ የነበረ ሰው የሐጅ ስራውን ጨርሶ መካን ለቆ ሲወጣ የመሰናበቻ ጠዋፍ በካዕባ ዙሪያ ሰባት ጊዜ ዞሮ መውጣቱ ዋጂብ ነው ። አንድ የሐጅ ስራ ላይ የቆየ ሰው የመሰናበቻ ጠዋፉን ካደረገ በኋላ መካ ውስጥ መቆየት የለበትም ። ጉዳዩን ጨርሶ ሲወጣ ነው ጠዋፉን ማድረግ ያለበት ።
አላህ ካለ ይቀጥላል ።
https://t.me/bahruteka
🔷
ከመንገድ ላይ የምታነሳው አዛ ለጀነት መግቢያነት ሰበብ ሲሆን!
قال ﷺ :–
" لقد رأيت رجلا يتقلب في الجنة في شجرة قطعها من ظهر الطريق كانت تؤذي المسلمين".
رواه مسلم
🔷
የአላህ መልእክተኛ - ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ ይላሉ :-
" መንገድ ላይ ሙስሊሞችን ስታስቸግር የነበረችን ዛፍ በመቁረጡ ምክንያት በርግጥ አንድ ሰው በጀነት ውስጥ ሲገላበጥ አይቻለሁ
" ።
https://t.me/bahruteka
👉
በዱንያ ላይ ስጁድ የምታደርግበት ቦታ የቂያማ ቀን ይመሰክርልሀል ስትሞት ያለቅስልሀል !
قال: عطاء الخراساني رحمه الله : –
" ما من عبد يسجد لله سجدة في بقعة
من بقاع الأرض، إلا شهدت له يوم القيامة، وبكت عليه يوم يموت ".
حلية الأولياء ( ١٩٧/٥ ).
🔷
ዐጣእ አል ኹራሳኒይ ረሂመሁላሁ እንዲህ ይላል :-
" አንድ የአላህ ባሪያ ቤትኛውም ቦታ ላይ ለአላህ ስጁድ አያደርግም ያ ቦታ የቂያማ ቀን የሚመሰክርለት የሞተም ቀን የሚያለቅስለት ቢሆን እንጂ "
https://t.me/bahruteka
🔷
ይህ አባባል አልገባኝም ላላችሁ !
በደሳሳ ጎጆ መኖር የድህነት ብቻ ሳይሆን የፅናትም ምልክት ሊሆን ይችላል ማለት በደሳሳ ጎጆ የሚኖሩት ድሆች ብቻ አይደሉም ለማለት ነው ። ለምሳሌ የነብያት ውርስ በሆነው የዒልም ድልብ የታጨቁ ብዙ ዑለሞች በደሳሳ ጎጆ ውስጥ ይኖራሉ ።! እነዚህ በዱንያ ላይ ከነብያትና ከሶሓቦች በኋላ ከእነርሱ በላይ ሀብታም የሌለ ዑለሞች የነብያት ውር የሆነው ሸሪዓን የማስተላለፍ ፅናታቸው እንጂ በደሳሳ ጎጆ እንዲኖሩ ያደረጋቸው ድህነት አይደለም ።
እነዚህ ዑለሞች ገንዘብንና የቅርቢቱን ዐለም ጌጥ ቢፈልጉ ኖሮ በወርቅ ቤት መኖር ይችሉ ነበር ። ነገር ግን ከነብያት የወረሱት ዒልም በዱንያ ብልጭልጭ ሳይታለሉ የያዙትን መለኮታዊ ተልእኮ ለማድረስ የዱንያን ፈተና በፅናት እንዲወጡ ያደርጋቸዋል ። በመሆኑም ተልእኳቸውን እንዲያደርሱ በቅርቢቱ ዐለም በደሳሳ ጎጆ እየኖሩ የተጣለባቸውን አማና ለመወጣት የመረጡት ህይወት ይህ ነው ። በዱንያ ላይ መሪዉም ተመሪዉም የያዙትን ነገር እንዲፈልግ ያደረገውም ይህ ነው ። ዑለሞችን የማይፈልግ ንጉስም ይሁን ሀብታም እውነተኛ ድሃ ማለት እሱ ነውና ።
በተወሰነ መልኩ መልእክቱ የደረሰ ይመስለኛል አላህ ያሳውቀን ።
https://t.me/bahruteka
👉
ዱንያ ለእርካታ ብቻ ተፈጥራ ቢሆን ኖሮ በሷ ላይ ለሙእሚን ድርሻ አይኖረውም ነበር !
قال ابن الجوزي رحمه الله :
" رأيت عموم الناس ينزعجون لنزول البلاء انزعاجًا يزيد عن الحد، كأنهم ما علموا أن الدنيا على ذا وضعت،
وهل ينتظر الصحيح إلا السقم، والكبير إلا الهرم، والموجود سوى العدم، ولولا أن الدنيا دار ابتلاء لم تَعْتَوِرْ فيها الأمراضُ والأكدار، ولم يضق العيش فيها على الأنبياء والأخيار، ولو خُلِقت الدنيا للذة لم يكن حظّ للمؤمن منها ".
موسوعة فقه الابتلاء: [4/ 129]
🔹
ኢብኑል ጀውዚ ከተናገራቸው ድንቅ ንግግሮች ውስጥ ;-
" የቅርቢቱ ሀገር ( ዱንያ ) ለበላእ የተኖረች መሆኗን ያላወቁ ይመስል ሰዎች ለበላእ ከወሰን ባለፈ መልኩ ሲረበሹ አየሁ !
ለመሆኑ ጤነኛ በሽታን,ትልቅ ሰው እርጅናን, ያለ ነገር መጥፋትን እንጂ ይጠብቃልን ?
የቅርቢቱ ዓለም የፈተና ሀገር ባትሆን ኖሮ ብርታትና በሽታ ባልተፋለሙ, በሷ ላይ በነብያቶችና በመልካሞች ላይ ኑሮ ባልጠበበ ነበር ። የቅርቢቱ ሀገር ለእርካታ ተፈጥራ ቢሆን ኖሮ ከርሷ ለአማኝ ድርሻ አይኖረውም ነበር "
https://t.me/bahruteka