Выберите регион
и язык интерфейса
Покажем актуальные для региона
Telegram-каналы и возможности
Регион
avatar

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

bahruteka
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahruteka
Подписчики
41 184
24 часа
6
30 дней
106
Просмотры
3 310
ER
8,04%
Посты (30д)
128
Символов в посте
869
Инсайты от анализа ИИ по постам канала
Категория канала
Религия и духовность
Пол аудитории
Мужской
Возраст аудитории
35-44
Финансовый статус аудитории
Низкий
Профессии аудитории
Прочие
Краткое описание
September 24, 18:49

👉
የሙስሊሞችን ሐቅ ያለ ፈቃዳቸው መጠቀም !
قال الشافعي – رحمه الله – :
"من مر لرجل بزرع أو ثمر أو ماشية أو غير ذلك من ماله لم يكن له أخذ شيء منه إلا بإذنه ؛ لأن هذا مما لم يأت فيه كتاب ولا سنة ثابتة بإباحته، فهو ممنوع إلا بإذن مالكه"
"المجموع" (9/ 55).
ኢማሙ ሻፍዕይ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላሉ : –
" በአንድ ሰው በአዝመራው ወይም በፍሬው ወይም በተንቀሳቃሽ ከብቶችም ይሁን በሌላም በግል ንብረት በኩል ያለፈ ሰው ከሱ ምንም ያለ ፈቃዱ መውሰድ አይፈቀድለትም ። ይህ ቁርኣንም ይሁን ሐዲስ የተፈቀደ በመሆኑ ያልመጣበት ነው ። በመሆኑም ያለ ባለቤቱ ፈቃድ የተከለከለ ነው " ።
የኢማሙ ሻፍዕይ ንግግር የአንድ ሙስሊም ገንዘብ ያለ ፍላጎቱ መውሰድ አይፈቀድም ከሚለው ከነብዩ ሐዲስ የተወሰደ ለመሆኑ ግልፅ ነው ። ገንዘብ ወይም ንብረት ማለት መጠቃቀሚያ ነው ። ማንኛውም አንድ ሰው በተፈቀደ መልኩ የግሉ አድርጎ የሚጠቀምበትን ነገር ያለሱ ፈቃድ የተለያዩ ዘዴዮችን ተጠቅሞ መጠቀም ክልክል መሆኑን ያመለክታል ። በመሆኑም የአንድ ሰው የግል ቻናልን ያለ ባለቤቱ ፈቃድ ለሌላ አካል በመክፈል በእጃዙር መጠቀም በምንም መልኩ የሚፈቀድ አይደለም ።
በጣም የሚገርመው የማፌያ ቡድኖች የሚሰሩትን አይነት ተግባር በመስራት የሰዎችን የግል ቻናል ያለፈቃዳቸው የራሳቸውን የሚፈልጉትን አካል ቻናል ማስተዋወቂያነት እየተጠቀሙ ይህን እንደጀብድ በመቁጠር ችሎታችንን ተመልከቱ የሚሉ ጉደኞችን እያየን ነው ። አው ከሸሪዓ የራቃችሁ የማፌያ ቡድኖች መሆናችሁን አውቀናል ነው መልሳችን ።
https://t.me/bahruteka

September 24, 14:38

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ወድ ወንድምና እህቶች ቴሌግራም የተለያዩ ማስታወቂያዎችን ያለ ባለቤቱ ፈቃድ እያስከፈለ ይለቃል። በመሆኑም እኔ ያለጠፍኩት ማስታወቂያ እኔን አይወክልም።  ማስታወቂያውን ሪፖርት አድርጋችሁ ለማስጠፋት ከጎን ያለውን ሶስት ነጥብ ነክታችሁ ምጫዎች ሲመጡ spam ብላች ላኩ።
https://t.me/bahruteka

September 24, 12:06

👉
ሙሐመድ ሓሚዲን የሰይድ ቁጥብ ጠበቃ !
ክፍል አስራ ሁለት
ሰይድ ቁጥብ የነብዩን ሶሓቦች የሚሳደብ ለመሆኑ ከራሱ መፅሐፍ ማረጋገጥ !
ሁለተኛ : ሙዓዊያንና ዐምር ኢብኑ ዓስን ሲሳደብ !
ባሳለፍናቸው ክፍሎች ለማየት እንደሞከርነው የነብዩን ሶሓቦች መውደድ ኢማን ሲሆን እነርሱን መጥላት ደግሞ ኩፍርና ኒፋቅ ነው ። ይህ ማለት የሚወዳቸው ሙእሚን ነው ማለት ነው የሚጠላቸው ደግሞ ሙናፊቅ ! ምክንያቱ ደግሞ የአላህ መልእክተኛ አደራና ኑዛዜ ነው ። ሶሓቦቼን በመጥፎ አታንሱ አትጥሏቸው ብለው አደራ ብለውናልና ። ከዚህም በላይ የወደዳቸው እኔን ለመውደዱ ነው የሚጠላቸውም እኔን ለመጥላቱ ነው ብለውናል ። እንደሚታወቀው ነብዩን መጥላት ኩፍር ነው ። ሶሓቦችን መጥላት ደግሞ ነብዩን መጥላት ነው ።
የነብዩን ሶሓቦች የምንወደው አላህ መርጦ የሳቸው ባልደረባ ስላደረጋቸውና ለእስልምና ህይወታቸውን ፣ ክብራቸውን ፣ ጉልበታቸውን ፣ እውቀታቸውን ፣ ገንዘባቸውን ጭምር ቤዛ ስላደረጉ ነው ። ለነብዩ ሸሪዓ ብለው ተሰደዋል ፣ ተርበዋል ፣ ተጠምተዋል ፣ ተገርፈዋል ፣ በእሳት ተቃጥለዋል ፣ በመካ ሀሩር የነደደ ቋጥኝ በእነርሱ ደም እንዲቀዘቅዝ ተደርጓል ። ለዚህ ነው አላህ ያላቃቸው ያከበራቸውና ዝናቸው ከፍ እንዲል ያደረገው ። በዚህ አላበቃም አመኞችን በመልካም እንዲያነሱዋቸውና ፈለጋቸውን እንዲከተሉ አዟል ። ይህ ነው የመወደዳቸው ሚስጢር ። ለዚህ ነው ሙእሚን እንጂ አይወዳቸውም ሙናፊቅ እንጂ አይጠላቸውም የተባለው ።
እነዚህን የአላህ መልእክተኛ ባልደረቦችን ነው ሰይድ ቁጥብ የሚያዋርደውና የሚያንቋሽሸው ። በአላህ ይሁንብኝ የሙሐመድ ሓሚዲን ጥብቅና ባይኖርና ወጣቶች እሱን ሰምተው የሰይድ ቁጥብን ተግባር ቀለል አድርገው በማየት ልባቸው ይታመማል ሳያውቁት ኒፋቅ ሊገባባቸው ይችላል የሚለው ስጋት ባይኖር ኖሮ የሰይድ ቁጥብን ቅርሻት ባልፃፍኩኝ ነበር ። ነገር ግን የዚህ ሰው ማንነት ሙሐመድ ሓሚዲን ከሚለውና ከሚገልፀው በጣም የራቀ ይልቁንም ራሱ አምኖበት በተናገረው ንግግሩና ፅሑፉ የአላህ መልእክተኛን ሶሓቦች የሚያዋርድና የሺዓዎችን አንጀት የሚያርስ በሶሓቦች ክብር ተረማምዶ በራፊዳዎች ሜዳሊያ የተሸለመ ግለሰብ መሆኑ እንዲታወቅ ነው ። ለማንኛውም ማየት ማመን ነውና እስኪ በነብዩ ላይ ይወርድ የነበረውን ወሕይ ከሚፅፉት የነበረውን ፣ የመጀመሪያውን በባህር ላይ የተደረገውን ዘመቻ የመራውን ፣ የምእመናን አጎት የሆነውንና የአላህ መልእክተኛ ዱዓእ ያደረጉለትን ብርቅዬ ሶሓብይ ሙዓውያንና ጓደኛውን ታላቁን ሶሓብይ ዐምር ኢብኑ ዓስም ምን እንደሚላቸውና እንዴት እንደሚያዋርዳቸው እንመልከት : –
"إن معاوية وزميله عَمْراً لم يغلبا علياً لأنهما أعرف منه بدخائل النفوس، وأخبر منه بالتصرف النافع في الظرف المناسب . ولكن لأنهما طليقان في استخدام كل سلاح، وهو مقيد بأخلاقه في اختيار وسائل الصراع . وحين يركن معاوية وزميله إلى الكذب والغش والخديعة والنفاق والرشوة وشراء الذمم لا يملك عليٌ أن يتدلى إلى هذا الدرك الأسفل فلا عجب ينجحان ويفشل، وإنه لفشل أشرف من كل نجاح ".
كتب وشخصيات ص (242)
" ሙዓዊያና ጓደኛው ዓምር ዐልይን ያሸነፉት ከሱ የበለጠ በሰዎች ውስጥ ያለውን በማወቃቸው ወይም በክስተቶች ጠቃሚ የሆነውን መንገድ በመከተል ከሱ የበለጠ እውቀት ኖሯቸው አይደለም ። ነገር ግን እነርሱ ለማሸነፍ የሚያስችለውን የትኛውንም መንገድ በመከተል ልቅ ስለሆኑና እሱ ግን በፍልሚያ ጊዜ መጠቀም ያለበትን መንገድ እንዲመርጥ በባህሪው የተገደበ ስለነበረ ነው ። ሙዓዊያና ጓደኛው ወደ ውሸት ፣ ማታለል ፣ ክህደት ፣ ንፍቅናና ፣ ጉቦ በመስጠት የሰዎችን ጫንቃ ወደመግዛት በተዘነበሉ ጊዜ ዐልይ ወደዚህ ዝቅጠት መዝቀጥ አይችልም ነበርና እነርሱ በማሸነፋቸውና እሱ በመሸነፉ መገረም አያስፈልግም ። መሸነፉ ከየትኛውም ማሸነፍ በላይ ክብር ነበርና " ።
ተመልከቱ ሰይድ ቁጥብ ሙዓዊያንና ዐምር ኢብኑ ዓስን በውሸት ፣ በማታለል ፣ በክህደት ፣ በሙናፊቅነት ፣ ጉቦ ሰጥቶ ሰዎችን በመግዛት ያሸነፉ ብሎ እንዴት እንደሚወርፋቸው
‼
ሱብሓነላህ ! እንዴት ይሆን ነገ አላህ ፊት ከሙዓዊያና ኢብኑል ዓስ ጋር ከሳሽና ተከሳሽ ሆኖ የሚቀርበው ? ለዛው ጠበቃቸው የአላህ መልእክተኛ ሆነው እሱ ነብዩ ለምን ሶሓቦቼን ሰደብክብኝ ሲሉት መልስ ሊሰጥ ! ከዚህ በላይ የሚገርመው ደግሞ የሶሓቦች ጠበቃ የአላህ መልእክተኛ ሆነው የሰይድ ቁጥብ ጠበቃ ደግሞ ሙሐመድ ሓሚዲን ሆኖ አላህ ፊት መገናኘታቸው ነው ።
አላህ ሆይ አንተ ጠብቀን !
አላህ ካለ ይቀጥላል ።
https://t.me/bahruteka

September 24, 08:23
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

September 24, 08:18
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

🔹
ሐሰኑል በስርይ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –
( በሰለፎች ዘመን) አንድ ሰው እሾክ ይወጋዋል ። እሱም እንዲህ ይል ነበር :–
" አንቺ እሾክ ሆይ የወጋሽኝ በወንጀሌ እንደሆነና ልቅና የተገባው አምላኬ እንዳልበደለኝ አውቃለሁ " ።
https://t.me/bahruteka

September 23, 15:21
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

September 23, 15:07

👉
ለተበዳይ ልብ እረፍት የሆነ አንቀፅ !
ከቁርኣን አንቀፆች ውስጥ በበዳይ ላይ ቀስት ለተበዳይ ቀልብ ደግሞ እረፍት የሆነች አንቀፅ አለች አሉ ኢማሙ ሻፍዕይ ።
የትኛዋ አንቀፅ ናት ተብለው ጢጠየቁ እንዲህ የምትለዋ አሉ : –
{ …وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّا }
مريم (64)
«… ጌታህም ረሺ አይደለም " ፡፡
https://t.me/bahruteka

September 23, 14:48
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

🎙
🎙
🎙
ታለቅ ብስራት ለሰለፊዮች በሙሉ
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ እና የደዕዋ ፕሮግራም
ለሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሙስሊም ተማሪዎች የመስጅድ ቦታ ግዢ ።
እነሆ የፊታችን ሀሙስ ረቢዓ ሳኒ /13/ 1448 ወይም መስከረም 14/2019 ከምሽቱ በእትዮ #3:00 ጀምሮ የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሙስሊም ተማሪዎች የመስጅድ ቦታ ግዢ ገቢ ማሰባሰቢያ እና የደዕዋ ፕሮግራም በኢሞ# ሩም ተዘጋጅቷል። በዚህ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ እና የደዕዋ ፕሮግራም በመሳተፍ የበኩልዎን አስተዋጽኦ ያበርክቱ የታሪክ ተካፋይ ይሁኑ እያልን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
➡
የእለቱ ተጋበዥ እንግዶቻችን
🎙️
ታላቁ ሸይኻችን ሸይኽ አብዱልሀሚድ አለተሚይ {ሀፊዘሁሏህ}
🎙️
ኡስታዝ ሙሀመድ ኪርማኒ{ሀፊዘሁሏህ}
🎙
ኡስታዝ አቡመርዋን ከሳንኩራ{ሀፊዘሁሏህ}
🎙
ኡስታዝ ሙህይዲን በድሩ {ሀፊዛሁሏህ}
🎙️
ኡስታዝ አብዱሹኩር ካሚል ከፎንቆ {ሀፊዘሁሏህ}
🎙
ኡስታዝ ሙሀመድ ወልቂጢይ
የፕሮግራሙ አስተባባሪ
➢ኡስታዝ ሙህይዲን ከሌራ እና ሌሎች ወንድሞችም ይኖራሉ
💺
:- አዘጋጅ :-ሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሙስሊም ተማሪዎች ጀምዓ።
ሆሳእናን ተባብረን ከኩፍር ጨለማ እንታደጋት
በሀዲያ ዞን ላይ አሻራ ማስቀመጥ እነደሌላው ቦታ አይደለም
🕒
የፕሮግራሙ ሰዓት፦
🇪🇹
*በኢትዮ* *3:00pm*
🇸🇦
*በሳዑዲ* *9:00pm*
🇰🇼
*ዱባይ* *10:00pm*
*የመገናኛ ልንክ
We're in room የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሙስሊም ተማሪዎች የገቢ ማሰባሰቢያ. Join us!
https://s.imoim.net/4fG2Is?from=copy_link
*የወትሳፕ ልንክ
👇🏻
👇🏻
https://chat.whatsapp.com/FapnD7O97xlLbZXPQTLFWK
ቴሌግራም
https://t.me/HHSMSCJ

September 23, 14:39

💢
💢
💢
አስደሳች ሰበር ዜና
‼️
‼️
‼️
በታላቅ ጉጉት በሚጠበቀው አለም አቀፉ የዳእዋ ፕሮግራም ላይ የሚቀርቡ አሊሞች÷ መሻኢኾች÷ ኡስታዞችና ዳኢዎች ዝርዝር ይፋ ሆነ
‼️
☄️
የዚህ ብርቅዬ ፕሮግራም÷ እንቁ ተሳታፊዎች
☄️
1.   የተከበሩ ሸይኽ ዶክተር ኻሊድ ቢን ሙሐመድ አል-ጉፈይሊ... ከሪያድ/ሳውዲ
2.   ሸይኽ ሐሰን ገላው ሐሰን .... ከባህር ዳር
3.   ሸይኽ አብዱልሀሚድ... ከስልጤ/ለተሞ
4.   ሸይኽ ዶክተር ሁሴን ሙሐመድ … ከአዲስ አበባ
5. ሸይኽ ጡሃ ኸድር.... ከአዲስ አበባ
6. ሸይኽ ሙሀመድ ጀማል.... ከኮምቦልቻ
7. ሸይኽ  አቡዘር ሐሰን... ከኮምቦልቻ
8.  ሸይኽ ሙሀመድ ሀያት... ከሀራ
9. ሸይኽ ሁሴን ከረም... ከሀራ
10. ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ.... ከባህር ዳር
11.   ሸይኽ መህቡብ... ከወራቤ
12. ሸይኽ  ሰይፋሏህ… ከምስራቅ ስልጤ
13. ሸይኽ ሙባረክ... ከወልቂጤ
14. ሸይኽ አህመድ... ወረታ/ከአዲስ አበባ
15. ሸይኽ ሙሀመድ ሲራጅ… ከሀሮ
16. ኡስታዝ ሙሀመድ ኢብራሂም... ከመዲና
17. ኡስታዝ ሰልማን... ከመዲና
18. ኡስታዝ ሻኪር ሱልጣን.... ከአዲስ አበባ
19. ኡስታዝ አብዱልቃድር ሐሰን...  ከአዳማ
20. ኡስታዝ  ሙሀመድ እባቡ... ከቻግኒ
21. ወንድም አቡ ሷሊህ አል ኡስይሚን ኢልያስ… ከኩዌት
☄️
የ
ፕሮግራሙ መሪዎች
☄️
1.   ኡስታዝ ባህሩ ተካ.... ከአዲስ አበባ
2.   ኡስታዝ አብዱረህማን ሰኢድ....  ከመርሳ
3.   ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሐሰን... ከደሴ
4.   ኡስታዝ አቡቦክር ዩሱፍ … ከባህር ዳር
5.   ኡስታዝ ሬድዋን ዳውድ… ከባህር ዳር
[ሁሉንም አሏህ ይጠብቃቸው]
ፕሮግራሙ የሚተላለፍበት:-
🔻
ቀን - መስከረም 16
🔻
ሰአት - ከቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ መገባደጃ
🔻
የሚተላለፍባቸው ቻናሎች:-
Telegram
https://t.me/bilalmesji
Imo
https://s.imoim.net/RKt0rh?from=copy_link
💢
💢
💢
ሰለፍይነት ያብባል
ተውሂድ ይነግሳል
💢
💢
💢

September 20, 19:03

👉
የማይጠገን ስብራት ማለት !
يقول عبدالله بن سليمان – رحمه الله –
ليست المصيبة أن يصاب الإنسان بنفسه أو ماله أو ولده، وإنما المصيبة العظيمة والجبر الذي لا ينجبر ، أن يصاب الإنسان بدينه، فيحل الشك محل اليقين ، فيرى الباطل حقا، والحق باطلا، والمعروف منكرا والمنكر معروفا "
الدرر السنية ( 15/466)
ዐብዱላሂ ኢብኑ ሱለይማን የተባለ ዓሊም እንዲህ ይላል : –
" ሙሲባ ማለት አንድ ሰው በነፍሱ ወይም በገንዘቡ ወይም በልጁ የሚደርስበት ሙሲባ አይደለም ። ነገር ግን ትልቁ የማይጠገነው ሙሲባ ማለት አንድ ሰው በዲኑ ሙሲባ ሲደርስበት ነው ። ጥርጣሬ የእርግጠኝነት ቦታ ሲዪዝ ፣ ባጢል ሐቅ, ሐቅ ደግሞ ባጢል , የሚታወቅ ነገር የማይታወቅ,የማይታወቅ ነገር ደግሞ የሚታወቅ ( ሱናው ቢዳዓ, ቢዳዓው ሱና) ሲመስለው ነው " ።
https://t.me/bahruteka