Select your region
and interface language
We’ll show relevant
Telegram channels and features
Region
avatar

Nejashi Printing Press

nejashipp
ይህ የነጃሺ ማተሚያ ቤት ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው። የተለያዩ ጠቃሚ መልዕክቶችን፣ አዳዲስ የህትመት ውጤቶቻችንና አገልግሎቶቻችንን ተከታተሉን፣ ለሌላውም ሼር አድርጉ።
Subscribers
4 615
24 hours
1
30 days
-15
Post views
2 571
ER
55,71%
Posts (30d)
10
Characters in post
488
Insights from AI analysis of channel posts
Channel category
Books
Audience gender
Female
Audience age
35-44
Audience financial status
Middle
Audience professions
Education
Summary
October 09, 15:34
Media unavailable
3
Show in Telegram

October 01, 17:38
Media unavailable
1
Show in Telegram

October 01, 17:38

ከጠቢባን አንደበት
ስለ አዕምሮ ዋጋ
**
* ‹አዋቂ ማለት መጥፎና ጥሩን ለይቶ የሚያውቅ ብቻ አይደለም፡፡ አዋቂ ማለት መልካምን ነገር አውቆ የሚከተልና መጥፎ ነገርን አውቆ የሚርቅ ነው፡፡›
(ሱፍያን)
** ‹ኃያሉና የተከበረው አላህ ከአዕምሮ በበለጠ የሚመለክበት ነገር የለም፡፡ አስር ነገሮችን ካልያዘ በስተቀር የአንድ ሰው አዕምሮ የተሟላ ነው ሊባል አይችልም፡፡ የማይኮራ መሆን አለበት፣ ትክክለኛ እይታ ሊኖረው ይገባል፣ የተረፈውን የሚመጸውት መሆኑ ግድ ነው፣ ኩራትን የማይፈልግ ተናናሽ ነው፣ ከመመጻደቅም የራቀ ነው፣ ዕድሜ ልኩን እውቀትን ሲፈልግ ይኖራል፣ ከተማሪነት የራቀ አይደለም፣ ከሌሎች የተበረከተለትን ነገር ትንሽ ብትሆንም አንኳ እንደ ትልቅ አድርጎ ይቆጥራል፣ ብዙ አስተዋጽኦ ቢያደርግም ምንም እንዳላደረገ ያስባል፡፡› (ወህብ ኢብኑ ሙነበህ)
** ‹ከሰዎች መካከል አዕምሮው የተሟላ ነው ሊባል የሚችለው አላህን የማወቅ ሁኔታው ያማረ፣ ለአላህ አብዝቶ የሚታዘዝ እንዲሁም በጉዳዮቹ ላይ ሁሉ የሚታገሰው ነው፡፡› (ዐብዱልመሊክ ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ)
* ‹አላህ (ሱ.ወ.) የባሮችን ነገሮች ሁሉ የበላይ አዕምሯቸውን እንዲጠቀሙ አደረገ፡፡ መሪያቸውን ዕውቀት፣ ነጂያቸውን ሥራ በነገሮች ላይ የሚያበረታቸውን ደግሞ ትዕግስትን አደረገ፡፡› (ሷሊሕ ኢብኑ ዐብዱልከሪም)
‹ሦስት ነገሮችን ያለው ሰው ሌሎችን ቢያጣም መብቃቃት ይችላል፡፡ በአዕምሮ ጤነኛ መሆን፣ እውነትን መያዝና ነፍሱን ከመጥፎ ስሜቶች ማጽዳት መቻል፡፡› (ዐብዱላህ ኢብኑ ሙሐመድ)
** ‹ሰዎች ሶስት ዓይነት ናቸው፡፡ አዋቂ፣ ሞኝ እና ጠማማ፡፡ አዋቂ/ብልህ/ የሆነ ሰው ሲያዳምጥ ከልብ ነው፡፡ ሞኝ ደግሞ ሲናገር ይቸኩላል፣ ሲያወራ ያበላሻል፣ መጥፎ ነገር እንዲሰራ ቢደረግ ይሰራል፡፡ መናጢ ሰው ስታምነው ይከዳሃል፣ ስታወራው ያሳፍርሃል፣ ሚስጥር ብትነግረው ይበትናል፡፡›
(አዩብ አልቀሪያህ)
*** ‹አንድ ዓቂል የሆነ ሰው አራት ነገሮችን ሊያውቅና ሊጠብቃቸው ይገባል፡፡ አደራን፣ እውነትን፣ መልካም ወንድምን እና ሚስጢርን፡፡ ስሜቱ ያሸነፈው ሰው አዕምሮውን መጠቀም አልቻለም፡፡› (አቡ ዐሊ አስ-ሰቀፊይ)
ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ
https://t.me/Nejashipp
https://nejashibooks.com/
ይደውሉና መፃሕፍት ይዘዙ
0945858585

September 30, 15:58

https://www.tiktok.com/@nejashibooks?_r=1&_t=ZS-9AAUrPSpFpf

September 25, 04:16
Media unavailable
1
Show in Telegram

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا **

September 21, 18:54

"ለአላህ ተብሎ የተሠራ ብቻ ሲቀር ሥራ ሁሉ ዋጋ ቢስ ነው።
ዓሊሞች ሲቀሩ ሰዎች ሁሉ ሙታኖች ናቸው ፤
የሠሩበት ሲቀሩ ዓሊሞችም ሁሉ አይረቤዎች ናቸው፤
ለአላህ ብቻ የሠሩት ሲቀሩ የሠሩበትም ቢሆኑ ተጃጃዮች ናቸው።
ለአላህ ብቻ የሠራውም ቢሆን ፍፃሜው በምን እንደሆነ እስኪያውቅ ድረስ ስጋትና ፍራቻ ውስጥ ነው።”
(ሰህል አት-ቱስቱሪ)
https://t.me/Nejashipp

September 18, 17:20
Media unavailable
1
Show in Telegram

September 18, 17:19

የአኺራ ዓሊሞች ምልክቶች
*
የተሳካላቸውና አላህ ዘንድም ቅርበት ያላቸው ናቸው የሚባሉት የአኺራ ዓሊሞች ናቸው። እነርሱም ምልክቶች አሏቸው -
ከምልክቶቻቸው መካከል፡-
አንድ ዓሊም በዕውቀቱ ዓለማዊ ጥቅምን ላይፈልግ ነው። የአንድ ዓሊም ትንሹ ደረጃ የዚህችን ዓለም ትንሽነትና ዋጋ ቢስነት ማወቁ ነው። ከመከራ ያልጠራች ድፍርስ እና አላቂ እንደሆነች መገንዘቡ ነው።
የመጨረሻውን ዓለም ታላቅነትና ዘላለማዊነት ደግሞ መረዳት ነው። ፀጋዋ የላቀ እና ከፍ ያለ እንደሆነ፤ እሷም ትልቅና የገዘፈ ደረጃ እንዳላት ማሰብ ነው።
እንዲሁም ሁለቱ ዓለሞች ተቃራኒ እንደሆኑ የሚረዳ ነው። ዱንያ እና አኺራ ጣውንታሞች ናቸው። አንደኛውን የበለጠ ብትወድ ሌላኛዋን ገሸሽ ማድረግህ ግድ ነው። ዱንያ እና አኺራ ሁለት ክንፍ እንዳለው ሚዛን ናቸው። አንደኛውን ካስበለጥክ ወደ ሌላኛው አጋደልክ ማለት ነው።
ይህንኑ በሚገባ ተረድቶ አኺራን ከዱንያ ያላስበለጠ ዓሊም እሱ የሸይጣን ምርኮኛ ነው። ስሜቱ አሸንፎታል፣ ዕድለቢስነቱ ረቶታል። የዚህ ዓይነቱ ሰው ከቶውኑ ከዓሊሞች ወገን ሊቆጠር አይችልም።
ለዚህም ነው አል-ሐሰን አል-በስሪ (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ይላሉ -
“የዓሊሞች ቅጣት የቀልብ መሞት ነው። የቀልብ መሞት መገለጫው በአኺራ ሥራ ዱንያዊ ጥቅምን መፈለግ ነው።”
ዑመር (ረ.ዐ.) እንዲህ ይላሉ -
“አንድን ዓሊም ዱንያን እጅግ የሚወድ ሆኖ ካገኛችሁት ለዲናችሁ ተጠንቀቁት። እያንዳንዱ ሰው የሚሰማራው በወደደው ነገር ላይ ነውና።”
የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ አር-ራዚ የዱንያ ዓሊሞችን እንዲህ ይሏቸው ነበር -
“ እናንተ የዒልም ሰዎች ሆይ! መኖሪያዎቻችሁ የቀይሶር፣ ቤቶቻችሁ የኪስራ፣ ልብሦቻችሁ የጣሂር፣ ጫማዎቻችሁ የጃሉት፣ መሳፈሪያዎቻችሁ የቃሩን፣ መብያ መጠጫዎቻችሁ የፊርዐውን፣ ምግቦቻችሁ የመሃይማን፣ መዝሀቦቻችሁ የሸይጣን ናቸው። የሙሐመድ ሸሪዓ በናንተ ውስጥ የታለ!”
አንድ ገጣሚ እንዲህ ይላል -
የፍየል እረኛ ፍየሎቹን ከተኩላ ይጠብቃል፣
ጠባቂዎቹ ፍየል የሆኑ ለታስ እንዴት ይክኾናል!?
ከኢማም አል-ገዛሊ ኢሕያእ ዑሉሚዲን መጽሐፍ የተወሰደ
ትርጉም - በሙሐመድ ሰዒድ
ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ!
https://t.me/Nejashipp
https://nejashibooks.com/
ይደውሉ 0945858585

September 14, 07:01

የነጃሺ ማተሚያ ቤት መፃሕፍትን በዌሳይታችን በኩል ይጎብኙ፣ ይዘዙ።
የነጃሺ መፃሕፍትን ከዌብሳይታችን ወይም በአፓችን ከታች ባሉት ሊንኮች ኦንላይን ማዘዝ ይችላሉ :: ቴሌ ብር፣ ኤምፔሳ፣ ሲቢኢ ብር እና ሌሎችም የክፍያ መንገዶች በአማራጭነት የቀረቡ ሲሆን መጽሐፉን ሲረከቡም በካሽ መክፈል ይችላሉ።  አዲስ አበባ ከሆኑ በሞተርሳይክል ያሉበት ድረስ ይመጣልዎታል:: ለክልል ከተሞች በፖስታ ቤት እንልካለን::
https://nejashibooks.com/
https://t.me/Nejashipp
ይደውሉ   0945858585

September 14, 07:00
Media unavailable
3
Show in Telegram

እጅግ ጠቃሚ መልዕክቶች እና ምልከታዎች ጥበባዊ ንግግሮች የሚያገኙበት ምርጥ መጽሐፍ
የማር ጠብታ
በኡስታዝ ሙሐመድ ዑመር
ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ
https://nejashibooks.com/
https://t.me/Nejashipp