Select your region
and interface language
We’ll show relevant
Telegram channels and features
Region
avatar

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

sultan_54
ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻ : https://api.whatsapp.com/send?phone=
Subscribers
13 500
24 hours
30 days
-100
Post views
793
ER
5,87%
Posts (30d)
93
Characters in post
818
Insights from AI analysis of channel posts
Channel category
Religion and Spirituality
Audience gender
Male
Audience age
25-34
Audience financial status
Middle
Audience professions
Education
Summary
June 10, 03:45
Media unavailable
1
Show in Telegram

> አካልህ ቢቆራረጥ እንኳ የጠዋትና የማታ አዝካሮችን አትተው! በፍጹም እንዳትተው።
> ከምሽት ዚክሮች መካከል አንዱን እንኳ ብትል እንኳ አድርገው።
ለምሳሌ፦
'በስሚላሂለዚ ላ የዱሩ መዓ ኢስሚሂ ሸይኡን ፊል አርዲ ወላ ፊ አስ–ሰማኢ ወሁወስሰሚኡል ዓሊም'
(በስሙ በምድርም ሆነ በሰማይ ምንም ነገር የማይጎዳውን በአላህ ስም እጀምራለሁ፤ እርሱም ሰሚውና አዋቂው ነው) የሚለውን ዱአ ብቻ ብትል እንኳ የጠዋትና የማታ ዚክርን እንዳደረግክ ይቆጠርልሃል። በምሽትም እንዲሁ።
> የመጨረሻው ደግሞ ከመተኛት በፊት የሚደረጉ ዚክሮች ናቸው። ከመተኛትህ በፊት እነዚህን ማውሻዎች ሳታደርግ በፍጹም እንዳትተኛ።
> አንዲት ዚክር ብቻ እንኳ ብትሆን፤ ለምሳሌ፦
'አስተግፊሩላሀለዚ ላ ኢላሀ ኢላ ሁወል ሀዩል ቀዩሙ ወአቱቡ ኢለይህ'
(ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን፣ ህያውና ሁሉን ቻይ የሆነውን አላህ ምህረት እለምነዋለሁ፤ ወደ እርሱም እመለሳለሁ) ብትል ምን እንደሚሆን ታውቃለህ?
> ከጦርነት ሜዳ የሸሸህ እንኳ ብትሆን፣ ወይም የወነጀልከው ወንጀል የዚህችን ዓለም አሸዋ ያህል የበዛ ቢሆን እንኳ አላህ ወንጀሎችህን በሙሉ ይምርሃል።
> እና ይሄ ከባድ ነው? እንግዲያውስ ከአላህ ጋር ኑር!"
>

June 10, 03:36

"
ከከሀዲያን እና ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር በአደባባይ ወይም በየቲቪ ቻናሎቹ የሚደረጉ ይፋዊ ክርክሮች፤ ይህ ከሰለፎች  የዳዕዋ መንገድ ነውን? ውጤቱስ ምንድን ነው?!
ይህንን በተመለከተ፤ ከሰለፎች (አላህ ይዘንላቸውና) በሰፊው የተነገረውና የታወቀው መንገድ፡ ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር ከመቀማመጥ፣ እነሱን ከመስማት፣ ከእነሱ ጋር ከመከራከርና ክርክር ከመግጠም መራቅ ነው።
ለዚህም ምክንያቱ፦
*
አንደኛ፦
ክርክር ልብን ያደክማል፣ ቂምና በቀልንም ያወርሳል።
*
ሁለተኛ፦
ሰሚው  (ሰፊው)ማህበረሰብ እውነቱ የትኛው እንደሆነ መለየት ላይችል ይችላል። በተለይም የቢድዓው ባለቤት አቀራረቡ የተዋጣለትና አንደበተ ርቱዕ ከሆነ፣ እንዲሁም የሱናው ባለቤት ደግሞ የማስረዳት አቅሙ ደካማ ከሆነ፤ ይፋዊው ክርክር ለሰፊው ህዝብ ፈተና (ፊተና) መሆን ይጀምራል። ህዝቡም ጥመትን እውነት ነው ብሎ ሊከተል ይችላል።
ስለዚህ ሰለፎች ይከለክሉ የነበሩት ለዚህ ነው።"
"አላህ ይጠብቃችሁና፤ በዚህ ዘመን በሳተላይት የቲቪ ቻናሎች ላይ የሚደረጉ የክርክር መድረኮችን በተመለከተ፦
እነዚህ መድረኮች አብዛኛውን ጊዜ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ያመዝናል። ለምን ቢባል?
*
አንደኛ፦
ጥያቄዎችንና ጥርጣሬዎችን (ሹብሃቶችን) ወደማያውቁትና ንፁህ ወደሆኑት የሰፊው ህዝብ ልቦች ውስጥ ያስርጻሉ። አንድ ተራ ሙስሊም በቤቱ ተቀምጦ ሳለ፣ ከዚህ በፊት ሰምቶት የማያውቀውንና በጭንቅላቱ ውስጥ ጨርሶ ያልነበረን ጥርጣሬ (ሹብሃ) በነዚህ መድረኮች አማካኝነት እንዲሰማ ይደረጋል። ከዚያም ያ ጥርጣሬ ልቡ ውስጥ ይፈጠራል። በክርክሩ ላይ ለቀረበው ጥርጣሬ የተሰጠው ምላሽ በቂ ባይሆን ወይም ግልጽ ባይሆንለትስ?! ያ ሰው ጥርጣሬው ልቡ ውስጥ እንደታተመ ይቀራል ማለት ነው። ይህ ደግሞ ትልቅ አደጋ ነው።
*
ሁለተኛ፦
እነዚህ መድረኮች ለቢድዓ ባለቤቶችና ለጠማሞች የራሳቸውን መርዝና ጥመት የሚረጩበት ሰፊ መድረክና ነፃ ማስታወቂያ ይሆኑላቸዋል። መቼም ቢሆን ሊያገኙት የማይችሉትን ሰፊ ህዝብ በእነዚህ ቻናሎች አማካኝነት ያገኛሉ።
ስለዚህ ትክክለኛውና ጥንቃቄ የተሞላበት መንገድ፡ እውነትንና ሱናን በራሱ ጥራቱና ውበቱ ለህዝቡ ማስተማር ነው። የጠማሞችን ጥርጣሬ ግን ስማቸውን ሳያነሱና መድረክ ሳይሰጧቸው፣ እውነቱን ጠንካራ በሆነ መረጃ በማብራራት ማፍረስ ይገባል።"
ሸይኽ ዶ/ር ሳሊህ አስ-ሰንዲ

June 09, 19:27
Media unavailable
1
Show in Telegram

June 09, 13:12

«አላህ (ሱብሓነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል፦
"ከሥራም ወደሠሩት እንመጣለን፤ የተበተነም ትቢያ እናደርገዋለን።"
*(ሱረቱ አል-ፉርቃን፡ 23)*
ፉደይል የተባሉት ታላቅ ዓሊም ይህንን የቁርዓን አንቀጽ አስመልክተው ሲናገሩ፦
"ከማያስቡትም ከአላህ ዘንድ ለእነሱ ግልጽ ሆነላቸው።"
*(ሱረቱ አዝ-ዙመር፡ 47)* እንዲህ አሉ፦ "መልካም ሥራዎችን የሠሩ መስሏቸው ነበር፤ ነገር ግን (በትንሣኤ ቀን) ሲያዩት ወንጀል ሆኖ አገኙት።"
እነዚህ ሥራዎች (በውስጣቸው ለአአሏህ ብቻ ያልጠሩ) ጉድለት ያለባቸው ሥራዎች ናቸው። ለአላህ ብሎ የሚሠራ ይመስላል፤ ነገር ግን በእውነታው ለራሱ ስምና ዝና (ወይም ለሌላ ምድራዊ ጥቅም) ነው የሠራው። ለአላህ ብሎ በተገቢው መንገድ አላጠራውም።
ይህ ሰው (በቂያማ ቀን) ወንጀል እንጂ መልካም ምንዳ አይኖረውም። እሱ ግን መልካም ሥራ የሠራ መስሎት ነበር። ለምን? ምክንያቱም ቀደም ሲል እንደጠቀስኩት ራሱን በትክክል አያውቅም ነበር።
ራሱን በአግባቡ የሚያውቅና አላህ ከራሱ (ከነፍሱ) ክፋት እንዲጠብቀው የሚለምን ሰው፣ ነፍሱ አታታለውም። ይህ (የተሸወደው) ሰው ግን መልካም ሥራ የሠራ መስሎት ይመጣል፤ ነገር ግን በእውነቱ ለአላህ ብሎ አልሠራም፣ ለራሱ ስሜት ሲል ነው የሠራው። በዚህም ምክንያት የሠራው ሥራ ሁሉ
"የተበተነ ትቢያ"
(ዋጋ ቢስ) ሆኖ ይቀራል።»

June 08, 06:15


"የተባሉትን ቃል ለወጡ" — የሲፋት ማዛባት አደገኝነት
አሰላም ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ
የአላህን ሱብሃነሁ ወተዓላ ባህሪያት (ሲፋት) የሚቀይሩና ትክክለኛ ትርጉማቸውን የሚያዛቡ የብድዓ (የፈጠራ) ሰዎች፤ የአላህ عز وجل የሚከተለው ቃል በእነሱ ላይ ይፈጸማል፦
>
"እነዚያ የበደሉት ሰዎች የተባሉትን ቃል ካልሆነ ሌላ ቃል ለወጡ።"
*(አል-በቀራህ፡ 59)*
>
*
"አር-ራህማን ከዐርሹ በላይ ከፍ አለ (ኢስተዋ)"
ሲባሉ፤ እነሱ ግን፦ "አይደለም፣ ተቆጣጠረ (ኢስተውላ)" አሉ። የተባሉትን ቃል ወደ ሌላ ቃል ለወጡ።
*
"ይልቁንም ሁለት እጆቹ የተዘረጉ ናቸው"
ሲባሉ፤ እነሱ ግን፦ "አይደለም፣ (እጅ ማለት) ጸጋውና ችሮታው ነው" አሉ። የተባሉትን ቃል ወደ ሌላ ቃል ለወጡ።
*
"የጌታህም ፊት (ዛት) ቀሪ ነው"
ሲባሉ፤ እነሱ ግን፦ "አይደለም፣ (ፊት ማለት) የጌታህ ማንነት (ዛት) ብቻ ነው" አሉ። የተባሉትን ቃል ወደ ሌላ ቃል ለወጡ።
*
"ጌታችን ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል፤ ለክብሩና ለግርማ ሞገሱ በሚገባ ሁኔታ"
ሲባሉ፤ እነሱ ግን፦ "አይደለም፣ ትዕዛዙ ወይም እዝነቱ ወይም ከመላእክቱ አንዱ መልአክ ነው የሚወርደው" አሉ። እነዚያ የበደሉት ሰዎች የተባሉትን ቃል ባልሆነ ሌላ ቃል ለወጡ።
*
"ጌታህም (ለመፍረድ) በመጣ ጊዜ"
ሲባሉ፤ እነሱ ግን፦ "አይደለም፣ የጌታህ ትዕዛዝ መጣ" አሉ።
በሌሎችም ማዛባቶቻቸው ሁሉ ላይ የአላህ عز وجل ቃል ይገጥማቸዋል፦
>
"እነዚያ የበደሉት ሰዎች የተባሉትን ቃል ካልሆነ ሌላ ቃል ለወጡ።"
>
ወሰላሙ ዓለይኩም
አሽይኽ ወሊድ አስ–ሱዐይዳን

June 07, 17:47
Media unavailable
1
Show in Telegram

የተከበሩ ዶክተር ሸይኽ
አሕመድ ኢብኑ ጧሊብ
በሸሪዓ እና ኢስላማዊ ጥናቶች ክፍል የዶክትሬት (PhD) ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ማዕረግ ( Excellent) ከመጀመሪያ ደረጃ ክብር (First-Class Honors) ጋር በማግኘታቸው እንኳን ደስ አሎት እንላለን።
​አላህ ይጠብቃቸው፣ በእሳቸው (ዒልም) ሌሎችን ይጠቅም ዘንድ እመኛለሁ።
አላህ ወደ ቀደሞ ኢማምነታቸው በሰላም ይመልሳቸው ዘንድ እንጠይቀዋለን።

June 07, 15:45
Media unavailable
1
Show in Telegram


"ቁርኣን ላይ ያሉ አሻሚ ነጥቦችን (ሙተሻቢሃትን) በመምዘዝ የሚከራከሯችሁ ሰዎች ወደፊት ይመጣሉ። እናንተ ግን በሱና ሞግቷቸው/ያዟቸው፤ ምክንያቱም የሱና ባለቤቶች  የአላህን መጽሐፍ (ቁርኣንን) ይበልጥ አዋቂዎች ናቸውና።"
(ዑመር ኢብኑ አል ኸጧብ)

ዳሪሚይ የዘገቡት

June 07, 09:06


የኸዋሪጆች ፈለግ እና የመገለል አባዜ
"አ’ትተመዩዝ" “አል ኢንዒዛል"
>
ከሙስሊሙ ማህበረሰብ (ጀማዐ) ተለይቶ መውጣትንና 'ልዩ ነኝ' ባይነትን (ኢንዒዛልን) በመጀመርያ የፈጠሩት ኸዋሪጆች ናቸው። ይህን ያደረጉትም በ'ሐሩራእ' የራሳቸውን ማህበረሰብ በመመስረትና ወደ እነሱ መሰደድን ግዴታ በማድረግ ነበር፤ ወደ እነሱ ያልተሰደደውንም በኩፍር ፈረጁት። ታዲያ ከሰዎች ተገልሎና ተለይቶ እየኖረ 'ሰዎችን አስገነዝባለሁ (አስተካክላለሁ)' የሚል ሰው ነገር ግራ የሚያጋባ ነው፤ ከማህበረሰቡ ጋር ሳትቀላቀልና ሳትኖር እንዴትስ ሰዎችን ወደ በጎ መንገድ ልትጣራ ትችላለህ?!"
>
##
#ከሰዎች
መገለል (በአካልም ሆነ በስሜት) እና ራስን እንደ ብቸኛ ትክክለኛ አድርጎ መቁጠር ለጽንፈኝነት የመጀመሪያው በር ነው። መልክተኛው ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«ከሰዎች ጋር የሚቀላቀልና በነርሱ አዛ ላይ የሚታገስ አማኝ፣ ከሰዎች ጋር የማይቀላቀልና በነርሱ እንግልት ላይ ከማይታገሰው ይበልጣል»

ስለሆነም በዳዕዋ ላይ ዋናው መሠረት ሰዎችን መቅረብ፣ መደባለቅና መታገስ እንጂ መገለልና መኮራት አይደለም።

June 07, 08:17

## ልጆችን የመውለድ ጉጉትና ትሩፋት!
ኢብኑል ቀዪም (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
*«ልጅን ለመውለድ ለመውደድና ለመመኘት ካደረጉኝ ነገሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡»*

ሙስሊም በሶሒሃቸው ከአቡ ሐሳን ይዘው እንደዘገቡት እንዲህ ብሏል፦
«ሁለት ወንድ ልጆቼ ሞቱብኝ። ለአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አልኳቸው፡— "ስለ ሙታኖቻችን ልባችንን የሚያረጋጋና የሚያስደስት ከረሱል ﷺ የሰማኸው ሐዲሥ አለህን?"
እሳቸውም፦ "አዎ፤
'ሕጻናቶቻቸው የጀነት ትናንሽ አሳዎች (ደዓሚስ) ናቸው። ከእነርሱ አንዱ አባቱን — ወይም ወላጆቹን — ያገኝና እኔ አሁን ያንተን ልብስ ጫፍ እንደያዝኩት የልብሱን ወይም የእጁን ጫፍ ይይዛል። አላህ እርሱንም አባቱንም ጀነት እስኪያስገባቸው ድረስ በፍጹም አይለቀውም'
አሉ" አሉ።»

ከሙዓዊያህ ኢብኑ ቁ‘ርራህ፣ እርሱም ከአባቱ እንደዘገበው፦
«አንድ ሰው ልጅን አስከትሎ ወደ ነቢዩ ﷺ ይመጣ ነበር።
ነቢዩም ﷺ፦
"ትወደዋለህን?"
አሉት።
ሰውየውም፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ እሱን እንደምወደው ሁሉ አላህም ይውደዳችሁ!" አላቸው።
ከዕለታት አንድ ቀን ነቢዩ ﷺ ሰውየውን አጡትና፦
"የእገሌ ልጅ ምን ሆነ?"
ብለው ጠየቁ።
ሰዎቹም፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ልጁ ሞተበትኮ" አሏቸው።
ነቢዩም ﷺ ለአባቱ እንዲህ አሉት፦
"ከጀነት በሮች ወደ አንዱ ስትመጣ እርሱ በዚያ በር ላይ እየተጠባበቀህ ማግኘትህን አትወድምን?"
አንድ ሰውም፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህ ለእሱ ብቻ የተለየ ነው ወይስ ለሁላችንም?" ሲል ጠየቀ።
እሳቸውም፦
"አይደለም፤ ለሁላችሁም ነው"
አሉ።»

ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፦
«የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ።
"ከኡመቴ (ህዝቦቼ) መካከል ሁለት ልጆች ቀድመውት የሄዱለት ሰው ጀነት ይገባል።"
ዓኢሻም (ረዲየላሁ ዐንሃ)፦ "አባቴና እናቴ ፊዳ ይሁኑልህና፤ አንድ ልጅ ቀድሞት የሄደስ?" ስትል ጠየቀች።
እሳቸውም፦
"አንቺ የተመራሽው (የተባረክሽው) ሆይ! አንድ ልጅ ቀድሞት የሄደም ቢሆን (ያው ነው)"
አሉ።
እሷም፦ "ከኡመትህ መካከል ምንም ልጅ ቀድሞት ያልሄደስ?" ስትል ጠየቀች።
እሳቸውም፦
"እኔ ለኡመቴ ቀዳሚ ነኝ፤ እኔን በማጣት እንደደረሰባቸው ያለ መከራ በፍጹም አይደርሰባቸውም"
አሉ።»
ምንጭ፦
*ቱሕፈቱል መውዱድ ቢአሕካሚል መውሉድ (ገጽ 13 - 15)*

June 06, 10:34

አላህን ከፍጡር ጋር የሚያመሳስለው ማነው?"
(الرَّحْمَنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَى)
«እናንተ መልካም ሰዎች ሆይ! “አላህ በዐርሹ ላይ ከፍ አለ (ኢስተዋ)” የሚለውን የቁርኣን ቃል — ቁርኣን በወረደበትና በዐረብኛ ቋንቋ የታወቀውን “ከፍ አለ፣ ከላይ ሆነ” የሚለውን ትርጉም — ለምን አትቀበሉም? ለምንስ ትክዳላችሁ?
እነርሱም (አሻዒራዎች/ሙዕተዚላዎች) ሲመልሱ፦ “ምክንያቱም ‘ኢስቲዋእ’ (በዐርሽ ላይ መሆን) የፍጡራን ባህሪ ነው፤ እኛ ደግሞ በዐርሽ ላይ የሚሆንን (የሚቀመጥን) አካል ከፍጡር ውጭ አናውቅም፤ ስለዚህ ይህንን ካረጋገጥን አላህን ከፍጡር ጋር አመሳሰልን (ተሽቢህ አደረግን)” ማለት ነው ይላሉ።
እሺ! መልካም፣ ችግር የለውም። ታዲያ ይህንን የቁርኣን አንቀጽ ምን ልታደርጉት ነው? ስንላቸው ምን ይላሉ መሰላችሁ? “በትርጉም እናቆለምመዋለንን (እናውለዋለን)፤ ትርጉሙም ‘ኢስቲላእ’ (በኃይል መቆጣጠር/ማሸነፍ) ነው እንላለን” ይላሉ።
እኛም በነርሱው መመዘኛ (ሎጅክ) እንመልስላቸዋለን፦ እኛም እኮ በኃይል የሚቆጣጠርንና የሚያሸንፍን አካል ከፍጡር ውጭ አናውቅም! (አንድን ነገር በኃይል የሚቆጣጠረው ፍጡር ነው)።
ታዲያ አሁንም እናንተ አላህን ከፍጡር ጋር አላመሳሰላችሁምን? እናንተ ራሳችሁ ፈጣሪን ከፍጡራን ጋር አመሳሳዮች (ሙሸቢሃ) አደላችሁም? ለመሆኑ እናንተ የአንዱን ገጣሚ ስንኝ ጠቅሳችሁ፦
*“ቢሽር የተባለው ሰው ያለ ሰይፍና ደም መፋሰስ በኢራቅ ላይ ‘ኢስተዋ’ (ተቆጣጠረ)”* የምትሉትን አታውቁም? እዚህ ጋ ‘ኢስተዋ’ ማለት በናንተ ትርጉም ‘ኢስቲላእ’ (ተቆጣጠረ) ማለት አይደል? ታዲያ ቢሽር የተባለው ፍጡር እኮ ነው የተቆጣጠረው! ስለዚህ አሁንም እናንተ አላህን ከፍጡር ጋር ወደማሳሰል (ተሽቢህ) ውስጥ ወድቃችኋል።
በዚህ ጊዜ፦ “አይ ወንድማችን! አንተ በስህተት ነው የተረዳኸን፤ እኛ እኮ የፈለግነው ለአላህ ክብርና ልቅና የሚመጥን፣ ከፍጡራን ቁጥጥር ጋር የማይመሳሰል ‘መቆጣጠር’ (ኢስቲላእ) ነው” ካሉን፤
እኛም እንዲህ እንላለን፦
“ሱብሓነላህ! ታላቅና ምስጉን ለሆነው አላህ ጥራት ይገባው!”
እኛስ (አህሉሱናዎች) መጀመሪያውኑ ምን አልን? አላህ ለአምላክነቱና ለታላቅነቱ የሚመጥን፣ ከፍጡራን መሆን ጋር የማይመሳሰል
“በዐርሹ ላይ ከፍ ማለት” (ኢስቲዋእ)
አለው ነው ያለነው።
ስለዚህ በእኛ አቋም ላይ የምትሰጡትን ማንኛውንም (የተሳሳተ) መልስ፣ እኛ በናንተ ቃልና መከራከሪያ ራሳችሁን መልሰን እንረታችኋለን (እንመክትባችኋለን)።»
ታላቁ የዘመናችን የዐቂዳ  ዓሊም ሸይኽ ሷሊሕ አስ-ሰንዲ