Выберите регион
и язык интерфейса
Покажем актуальные для региона
Telegram-каналы и возможности
Регион
avatar

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

sultan_54
ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ♻ : https://api.whatsapp.com/send?phone=
Подписчики
13 493
24 часа
-1
30 дней
-7
Просмотры
1 518
ER
11,25%
Посты (30д)
24
Символов в посте
700
Инсайты от анализа ИИ по постам канала
Категория канала
Религия и духовность
Пол аудитории
Мужской
Возраст аудитории
25-34
Финансовый статус аудитории
Средний
Профессии аудитории
Образование
Краткое описание
July 27, 09:43
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

ኢላሂ!
ወደ መካ የሚያደርሰንን መንገድ የማይቋረጥ አድርግልን፤ ዱንያ ምንም ያህል ብትጠብብን በእሷ ውስጥ ሰፊ እፎይታ የሚያገኝ ልብንም ስጠን።
❤️
ኢላሂ
! ደጋግሜ እንድጎበኛት የሚረዳኝን ሲሳይ (ሪዝቅ) ለግሰኝ...
አሚን አሚን አሚን
#ያ_ረብ
🤍
🤲
🕊
🕋
❤️
"

July 27, 05:16

ዑምራ፡ የመንፈስ ጉዞ ወይስ የዱንያ መዝናኛ?
ዑምራ—የእስልምናን ቅዱሳት ስፍራዎች የመጎብኘት፣ ወንጀልን የማሰሪያ፣ ቀልብን ከዓለማዊ እና ቁሳዊ ሸክም አጥቦ ወደ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ የመመለሻ ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ነው። ነገር ግን ከቅርብ ግዜ ወዲህ የሚስተዋሉ አንዳንድ ልማዶችና የቱር አዘጋጆች ዘይቤ፣ የዚህን ታላቅ ዒባዳ ዋና ዓላማ እያሳቱት ይሆን? የሚል እውነተኛ ስጋት እያስነሳ ይገኛል።
1. የዓለማዊ ነገሮች መጎላትና የመንፈሳዊነቱ መቀጨጭ
በዑምራ ጉዞዎች ላይ አሁን አሁን ዋና ትኩረቱ ከዒባዳ ወደ መዝናናት ሲያደላ ይስተዋላል። ፈረስ ግልቢያ፣ የቀስት ውርወራ፣ የባህር ላይ የጀልባ ሽርሽር እና መሰል መዝናኛዎች የጉዞው ዋና ማእከል እየሆኑ መጥተዋል።
ከሁሉም በላይ ግን አሳዛኙ ነገር፡ በአል-ሐረመይን (በመካው መስጂደል ሐራም እና በነቢያችን መስጂድ) አንድ ሰላት መስገድ እስከ
100,000 ሰላት
እጥፍ በነቢዩ መስጂድ ደግሞ አንድ ሺህ የሚደርስ ታላቅ ምንዳ (አጅር) እንዳለው እየታወቀ፣ ያንን ሁሉ እድል አግኝቶ በጨዋታና በመዝናናት ጊዜን በማሳለፍ በጀማዓ መስገድን ማስመለጥ ትልቅ
ሂርማን (የአጅር ኪሳራ)
ነው።
መዝናናት በራሱ የተከለከለ ባይሆንም፣ ቅዱስ ስፍራ ላይ ቆሞ ጊዜን በእንዲህ አይነት ነገሮች ማሳለፍ ግን የዑምራን ዋና መንፈሳዊ ጥቅም እና የልብ መረጋጋት እያመናመነው ይገኛል።
2. የሱህባ እና የሳሊሆች ሚና መዛባት
አንድ ሰው ለዑምራ ሲነሳ ከጎኑ የሚፈልገው አላህን የሚያስታውሱት፣ አምልኮቱን የሚያስተካክሉለት እና ወደ አኼራ የሚጠቁሙትን
"ሩፍቀት አስ-ሳሊሃ"
(መልካም ጓደኞችን) ነው። አሳዛኙ ነገር ግን፣ የቱር ኤጀንሲዎች ማስታወቂያዎቻቸው ላይ ሸሪዓዊ እውቀት ያላቸውን ረባኒይ መሻይኾች እና ዓሊሞችን መሪ ከማድረግ ይልቅ፣ የቲክቶክ እና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን (Activists) እንደ ዋና ሳቢ ማስታወቂያ ማቅረባቸው ነው።
መንፈሳዊ መሪዎችን በቲክቶክ አክቲቪስቶች መተካት የጉዞውን ሚዛን ያሳስታል። የዑምራ ጉዞ በቪዲዮ እይታና በፎቶ ብዛት ሳይሆን በዕንባ፣ በዱዓ እና በኢኽላስ የሚለካ ተግባር ነው።
የዑምራ አዘጋጆችም ሆኑ ተጓዦች ወደ ህሊናቸው ሊመለሱ ይገባል። ዑምራ የልብ ህክምና እንጂ የካሜራ ትርኢት ወይም የቱሪዝም ሽርሽር አይደለም። የዑምራ ጉዞ እውነተኛ ዓላማውን ሳይስት፣ የአላህን ፍራቻ እና የመንፈስ እድሳትን ማዕከል ያደረገ ይሆን ዘንድ አቀራረባችንን እና አስተሳሰባችንን ልንፈትሽ ይገባል።

July 22, 06:38
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

اللهم يسِّر أمورنا، واشرح صدورنا، وبارك لنا في أرزاقنا وأوقاتنا، واصرف عنا كل همٍّ وغمٍّ وبلاء، واجعل لنا من كل ضيقٍ مخرجًا، ومن كل همٍّ فرجًا، ومن كل بلاءٍ عافية.
ربنا آتنا في الدنيا حسنة، وفي الآخرة حسنة، وقنا عذاب النار

July 21, 08:59

ሪዝቅህ
እንደ ዝናብ ነው! አላህ በሚወስነው ጊዜና ቦታ ይወርዳል። በሩ በፊትህ ቢዘጋብህ አትዘን፣ አንድ ሰው ቢርቅህም አትስጋ፤ ያንን በር በራህራሄው የዘጋው አላህ፣ ከሕልምህ በላይ እጅግ ሰፊና ውብ የሆኑ በሮችን ይከፍትልሃልና።

July 20, 11:00
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

የአላህ መልእክተኛ ﷺ ከተማ ሆይ…
እርምጃዎች ቢርቁም፣ ልብ አሁንም አንቺው ዘንድ ነው..
🤍

July 19, 03:34

﴿إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا﴾
«በእርግጥ ከችግር ጋር ምቾት አለ።»
ቀናቶች ምንም ያህል ቢጠነክሩብህ ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጥ፤ ምክንያቱም ፈረጃው ባሪያው ባላሰበው መንገድ ይመጣል። አላህ በእርሱ ላይ መልካም የጠረጠረውን ሰው መቼም ቢሆን አያሳፍረውም።
አላህ ልባችሁን ደስታን እንዲሞላው፣ ነገሮቻችሁን እንዲያገራልችሁ እና ቁርአንን የልባችሁ ብርሃን እንዲያደርግላችሁ እለምነዋለሁ።

July 18, 11:45

የሸይኽ ዐብዱረዛቅ ኢብኑ ዐብዲልሙሕሲን አል-ዐባድ አል-በድር (አላህ ይጠብቃቸው) የሕይወት ታሪክ
ታላቁ ዓሊም፣ ወሪዕ(ጥንቁቁ ፈቂህ)፣ የመልካም ስብዕና እና የከፍተኛ ስነ-ምግባር ባለቤት የሆኑት
ሸይኽ ዐብዱረዛቅ ኢብኑ ዐብዲልሙሕሲን አል-ዐባድ አል-በድር
(አላህ ይጠብቃቸው)።
እሳቸው ጥልቅ እውቀትን፣ መልካም ስነ-ምግባርን፣ ከፍተኛ ትጋትን እንዲሁም በማስተማርና በዳዕዋ ስራ ላይ ዘወትር በማስተማር በአንድ ላይ ካዋሃዱ ታላላቅ ዑለማኦች (ሊቃውንት) አንዱ ናቸው።  በለስላሳነታቸውና በርህራሄያቸው የሚታወቁ ሲሆን፣ ከጭቅጭቅ የራቁና ሰዎችን ከማንቋሸሽና ሁከት ከመፍጠር የጠሩ ናቸው። ስለ ማንም ሰው መጥፎ ሲናገሩ አይሰማም፤ ይልቁንም መመሪያቸው ስህተትን መሸፈን፣ መምከርና በትክክለኛው መንገድ መምራት ነው።
የዒልም እድገታቸውና መሻይኾቻቸው

እሳቸው (አላህ ይጠብቃቸው) ያደጉት በዒልም እና በዲን  በታነጸ ቤት ውስጥ ሲሆን፣ በታላቁ የመዲና የሐዲሥ ሊቅ በሆኑት በአባታቸው በሸይኽ ዐብደልሙሕሲን አል-ዐባድ ጥላ ስር ነው ያደጉት። ይህም ለስብዕናቸው መገንባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበረው። በመቀጠልም የዘመኑ ታላላቅ ዑለማኦች እውቀትን ቀስመዋል፤ ከእነዚህም መካከል፦
ሸይኽ ዐብደልዐዚዝ ኢብን ባዝ
ሸይኽ ሙሐመድ ኢብን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን
ሸይኽ ዐብደላህ አል-ጉደያን
ሸይኽ ዐብደላህ አል-ጉነይማን
ሸይኽ ዐሊ ናሲር ፈቂሂ እና ሌሎችም።
በዚህም የኢስላሚክ ዩኒቨርሲቲ (መዲና) እውቅ መምህር እና በመዲና መስጂደ ነበዊ ከሚያቀሩ ታዋቂ የዲን ሊቃውንት አንዱ ለመሆን በቅተዋል።
የቅርብም የሩቅም ሰው ለመልካም ስነ-ምግባራቸው፣ በማስተማር ክህሎትና ብቃታቸውና ንግግራቸው ግልጽነት መስክሮላቸዋል። እንዲያውም ሸይኽ ሷሊሕ አስ-ሱሐይሚ ስለ እሳቸው ሲናገሩ፦
"ዐብዱረዛቅ አል-በድር አባቱ ሸይኼ ነው፣ እሱ ደግሞ ተማሪዬ ነው፤ ዛሬ ግን እሱ ከእኔ ይበልጣል" ብለዋል።
የሕይወት ታሪካቸውንና ትምህርቶቻቸውን ያስተዋለ ሰው አላህ የሰጣቸውን የብስለት አእምሮ፣ ጥበብና ቀጥተኛ አካሄድ በግልጽ ይመለከታል። እውቀትን ከተግባር፣ ዐቂዳን  ደግሞ ነፍስን ከማጥራት(ተዝኪየቱ አን ነፍስ) ጋር ለማገናኘት ያላቸው ልዩ ትኩረት ይታያል፤ በዚህም የተነሳ የትምህርት መጃሊሶቻቸው በትህትና እና በሰኪና (በመረጋጋት) የተሞሉ ናቸው። በዒልማቸው በሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ በርካታ ሕዝብ ተጠቃሚ ሆኗል።
ታዋቂ ማብራሪያዎቻቸውና ትምህርቶቻቸው (ሸርሆች)
ሸርሕ አል-ቀዋዒድ አል-ሙሥላ (شرح القواعد المثلى)
ሸርሕ አል-ከሊም አጥ-ጦይብ (شرح الكلم الطيب)
ሸርሕ ቀዋዒድ አል-አስማእ አል-ሑስና (شرح قواعد الأسماء الحسنى)
ሸርሕ ሐሺየት ኢብን አቢ ዳውድ (شرح حاشية ابن أبي داود)
የዋሲጢያህ፣ የሉምዐቱል ኢዕቲቃድ፣ የመሳኢል አል-ጃሂሊያህ እና የሌሎች ሰለፎች የዐቂዳ ኪታቦች ማብራሪያ።
የሪያዱ አስ-ሷሊሒን፣ የተጅሪድ አስ-ሶሪሕ፣ የሙኽተሰር ሶሒሕ ሙስሊም እና የአርበዒን አል-ነወዊያህ ማብራሪያ።
በስነ-ምግባርና በባህሪ ዙሪያ ጠቃሚ ትምህርቶች አሏቸው፤ ከእነዚህም፦ የአድ– ዳእ ወድ-ደዋእ ፣ የአኽላቅ ሐመለቲል ቁርዓን እና የዋቢል አስ-ሰዪብ ማብራሪያዎች።
ታዋቂ መጽሐፎቻቸው

ፊቅህ አል-አድዒያህ ወል-አዝካር (فقه الأدعية والأذكار)
አል-ሐጅ ወተህዚብ አን-ኑፉስ (الحج وتهذيب النفوس)
ተዝኪረቱል ሙእተሲ ሸርሕ ዐቂዳህ ዐብደልገኒ አል-መቅዲሲ (تذكرة المؤتسي)
ዲራሰቱ አሠር አል-ኢማም ማሊክ ፊ ባብ አል-ኢስቲዋእ (دراسة أثر الإمام مالك)
ተዕዚም አስ-ሶላት (تعظيم الصلاة)
በሐዲስ፣ በፊቅህ፣ በዐቂዳና በስነ-ምግባር ዙሪያ የተሰሩ ምርምሮችና ጥናቶች።
ፊቅህ አል-አስማእ አል-ሑስና (فقه الأسماء الحسنى)
እነዚህና ሌሎች ጠቃሚ መጽሐፎች ያሏቸው ሲሆን፣ በቅርቡ መጽሐፎቻቸውና መልዕክቶቻቸው በሙሉ በአንድ ጠቃሚ ጥራዝ ተሰብስበው ታትመዋል።
ማጠቃለያ፦
እሳቸው አላህ እውቀትንና ተግባርን፣ ማስረጃንና ርህራሄን፣ ሱናንና መልካም ስነ-ምግባርን በአንድ ላይ የሰበሰበላቸው ሸይኽ ናቸው። በመሆኑም ለአስተማሪ ዳዒና መካሪ ዓሊም ምርጥ ምሳሌ ናቸው። የእውቀት ፈላጊዎች ወደ መጽሐፎቻቸው እንዲዞሩ፣ ትምህርቶቻቸውን እንዲያዳምጡ እና ዐቂዳን በማረጋገጥ፣ ነፍስን በማጥራትና በመልካም አስተዳደግ ረገድ ካላቸው ጠንካራ አካሄድ እንዲጠቀሙ እንመክራለን።
አላህ ሸይኹን ይጠብቃቸው፣ በእድሜያቸውና በእውቀታቸው ላይ በረከትን ያድርግላቸው፣ እስልምናንና ሙስሊሞችንም በእሳቸው ይጠቅም ዘንድ እንለምነዋለን።

July 18, 11:45
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

July 17, 11:45

ፈትዋ
ጥያቄ፦
ነጋዴው የዚህ ዕቃ ዋጋ በጥሬ ገንዘብ (ካሽ) ከተከፈለ 100 ዲናር ነው፤ በየወሩ እየተከፋፈለ በክሬዲት (በተቅሲጥ) ከሆነ ግን 150 ዲናር ነው ይላል። ታዲያ የዚህ ብይን ምንድን ነው? አላህ ምንዳዎን ይክፈልዎና።
መልስ (በሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን)፦
ይህ አሰራር ይፈቀዳል፣ ምንም ችግር የለውም። አላህ በትዕዛዙ በጥቅሉ እንዲህ ስላለ፦
"አላህ መሸጥን ፈቀደ፤ ወለድን ግን እርም አደረገ።"
(አል-በቀራህ፡ 275)
እንዲሁም አላህ እንዲህ ብሏል፦
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከ ታወቀ ጊዜ ድረስ ባለ እዳ በተዋዋላችሁ ጊዜ ጻፉት።"
(አል-በቀራህ፡ 282)
ይህ ገዥ ዕቃው በሁለት የተለያየ ዋጋ ቀረበለት ማለት ነው፤ በጥሬ ገንዘብ (በካሽ) የሚከፈል ዋጋ እና በጊዜ ገደብ (በክሬዲት) የሚከፈል ዋጋ። ለምሳሌ የጥሬ ገንዘቡ ዋጋ 100 ነው እንበል፤ የጭልፊቱ ዋጋ ደግሞ 150 ነው፤ እሱም በዚያው በተቀመጡበት መጅሊስ ከቦታው ሳይበተኑ የክሬዲቱነረ (የ150ውን) መረጠ። ከዚያም ዕቃውን ይዞ ሄደ። በዚህ ጊዜ በእሱ እዳ ላይ 150 ዲናር በትክክልና በግልጽ ተቀምጦ ጸና።
ይህ ዓይነቱ ሽያጭ ምንም ችግር የሌለበት ትክክለኛ ሽያጭ ነው። ምክንያቱም ገዢው በዚህ ወይም በዚያኛው ዋጋ ለመግዛት ምርጫ ተሰጥቶታል።
ይህ ደግሞ በምንም መልኩ ከወለድ (ሪባ) ጋር አይገናኝም። ምክንያቱም ወለድ ማለት "ብርን በብር" (ገንዘብን በገንዘብ) ላይ ጨምሮ መሸጥ ማለት ነው። እዚህ ጋር ግን እየተሸጠ ያለው ዕቃ ነው፤ ዕቃን ደግሞ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን በዚህ ዋጋ፣ በጊዜ ገደብ ሲሆን ደግሞ በዚያ ዋጋ መሸጥ ሙሉ በሙሉ የተፈቀደ ነው።
እንዲሁም ይህ ሽያጭ ነቢዩ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ከከለከሉት "በአንድ ሽያጭ ውስጥ ሁለት ሽያጭ ማድረግ" (بيعتين في بيعة) ከሚለው ክልከላ ውስጥ አይገባም። ምክንያቱም እዚህ ጋር የተፈጸመው አንድ ሽያጭ ብቻ ነው። ሰውየው በሁለት አማራጮች መካከል ምርጫ ተሰጥቶት አንደኛውን መርጦ በአንዱ ላይ ብቻ ተስማምቶ ወጥቷልና።

July 14, 04:08
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
«የጠራችሁን ሰው ጥሪ ተቀበሉ (እሺ በሉ)፣ ስጦታን አትመልሱ፣ ሙስሊሞችንም አትምቱ።»
(አህመድ ዘግበውታል፣ አልባኒም ሰሂህ ነው ብለውታል)
የሐዲሱ ማብራሪያ (የግርጌ ማስተዋሻ)
«የጠራችሁን ሰው ጥሪ ተቀበሉ»፦
ይህ የሰርግ ድግስም ይሁን ሌላ ማንኛውም ዓይነት ምግብ ላይ እንዲገኝ የጠራውን ሰው ጥሪ ምላሽ እንዲሰጥ የታዘዘበት ነው።
«ስጦታን አትመልሱ»፦
ይህ ደግሞ ሁለተኛው ትዕዛዝ ሲሆን፣ የቀረበን ስጦታ ባለመመለስ መካከል ላይ ፍቅርና መተሳሰር እንዲኖር ያደርጋል።
«ሙስሊሞችንም አትምቱ»፦
ይህ ሦስተኛው ትዕዛዝ ሲሆን፣ ያለ ምንም (ሸሪዓዊ ቅጣት) ወይም ያለ አግባብ ሙስሊሞችን ከመምታትና ከመበደል መቆጠብን ያዛል። መሠረቱ ግን ከእነሱ ጋር በቃልም ሆነ በተግባር በደግነትና በለስላሳነት መኖር ነው።