Select your region
and interface language
We’ll show relevant
Telegram channels and features
Region
avatar

የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

yahyanuhe
﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | ለንግድ፣ ለህክምና ወይም ለጉብኝት ወደ ቱርክ፣ ዱባይ እና የተለያዩ ሀገራት ለመጓዝ ካሰባችሁ ፈሲሩ ትራቭል የትኬት ጉዳያችሁን በኃላፊነት ያጠናቅቃል። እንግልት የሌለበት ጉዞ ለማድረግ ስትፈልጉ በዋትስአፕ አግኙን፦ https://wa.me/qr/5CWCIMYBZLCJB1
Subscribers
22 200
24 hours
-33
30 days
1 026
Post views
2 492
ER
11,23%
Posts (30d)
56
Characters in post
1 002
Insights from AI analysis of channel posts
Channel category
Business & Economy Blog
Audience gender
Female
Audience age
25-34
Audience financial status
Middle
Audience professions
Research & Academia
Summary
October 29, 14:59

ሲያጠምቁ "እልልታ"፣ ሲሰልሙ "ተገደው ነው"?! ይህችን ያረጀች ፕሮፓጋንዳ ተዋት!
በምስሎቹ ላይ እንደምትመለከቱት፣ አንደኛው ወገን በገዛ ገጹ "23,199 ነፍሳት ተጠመቁ" እያለ በኩራት ዜና ሲሰራና ሲያጨበጭብ ይታያል። ይህ ለእነሱ "ጻድቅ" እና "ኖርማል" ተግባር ነው፤ ማኅበራዊ ሚዲያቸውም በ"እልልታ" እና "አሜን" ይሞላል። በሌላ በኩል ደግሞ፣ መቶ እንኳን የማይሞሉ ሰዎች በራሳቸው ፍላጎት እስልምናን ሲቀበሉ ምስሉ ላይ እንደምታዩት አይናቸው ይቀላል፤ "ከሚሞቱ ብለው ነው" ወይም "ተገደው ነው" እያሉ የሃሰት ጩኸታቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ያቀልጡታል።
ይህ ዓይነቱ የተንሸዋረረ አመለካከትና የለቅሶ ፕሮፓጋንዳ በዋናነት ሁለት ዓላማዎችን ያነገበ ነው፦
1ኛ በዳዕዋ መስክ የገጠማቸውን ትልቅ ሽንፈት በሌላው ላይ ለማላከክና እውነታውን ለመሸሸግ የሚደረግ መፍጨርጨር ነው።
2ኛ እስካሁን ባለው የሙስሊሙ እንቅስቃሴ "ዳዕዋ በሰፊው ተሰርቷል" ተብሎ ባይገመትም እንዲሁም ክፍተቶች ቢኖሩትም፤ በአቅማቸው የሚለፉና የሚታገሉ አካላትን መልካም ድካም ጥላሸት በመቀባት፣ ታጋዮቹን ለማሸማቀቅና ሞራል ለመስበር የታለመ ነው።
እጅግ የሚያሳዝነው የዚህ አስተሳሰብ ባለቤቶች ለራሳቸው ያላቸው የተለጠጠ አመለካከት ነው። ሀገረ ስብከቶቻቸው በየዓመቱ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን "አጠመቅን" እያሉ ዜና ሲሰሩ፣ የሙስሊሙ ትግል ግን እጅግ ይረብሻቸዋል፤ ጥቂት ሰዎች ሲሰልሙም ፈጥነው ፍርጃ ውስጥ ይገባሉ።
በእነሱ እምነት "ሰው መቀበል ያለበት እኛን ብቻ ነው፤ እኛ ጋር ሲመጣ ኖርማል ነው፣ ሌላው ጋር ሲሄድ ግን አእምሮውን ስቶ ወይም ተገዶ ነው" የሚል ያረጀና ያፈጀ ትምክህት ነው። የራሳቸው ሲሆን ጽድቅ፣ የሌላው ሲሆን ወንጀል አድርጎ ስያሜ በመስጠት ሌላውን ለማሸማቀቅ ይሞክራሉ።
ነገር ግን አንድ ሊያውቁት የሚገባ እውነት አለ፤ በእንደዚህ አይነት ርካሽ የ"አስገደዱን" ፕሮፓጋንዳ የሚሸወድ ጅል በዚህ ዘመን የለም! የሰዎችን ንቃተ ህሊና ንቆ የፈጠራ ክስ ከመደርደር ይልቅ፣ እውነታውን ተቀብሎ መኖር ይሻላል።
የዳዕዋ ስራችን ይቀጥላል!
https://t.me/Yahyanuhe

October 29, 14:59
Media unavailable
1
Show in Telegram

October 29, 13:35

🎉
ልዩ የበጋ ስልጠና በኢሙዳት(የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዳዕዋና ትምህርት ማህበር)
🎉
ኢሙዳት በየአመቱ በጋ ወቅት አጠቃላይ የንፅፅር እውቀት ብልፅግና ላይ የሚያተኩሩ ስልጠናዎችን ያለ ምንም ክፍያ በታዋቂ ኡስታዞች እና አሰልጣኞች በመስጠት ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅ ይታወቃል። በመሆኑም በዘንድሮ በጋ ልዩ የሆነ ስልጠና
በዋነኝነት
በአዲስ አባባ
እና ዙርያዋ ለሚገኙ  2ኛ ደረጃ ት/ት ተማሪዎችና ለዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ  በተጨማሪም በማንኛውም ዘርፍ ላይ ያሉ በሃይማኖት ንጽጽር  ዘርፍ ለኢስላም መስራት የሚፈልጉ ወጣቶችን
ለይቶ ስልጠናዎችን ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል።
ስልጠናው የሚያጠነጥነው
የንፅፅር እውቀት፣ ኢማንን ማጎልበት፣ የሊደርሽፕ ፣ አርት እና ኢስላማዊ ስልጣኔ፣ የማህበረሰባዊ አይዲዮሎጂዎች እና መሰል የወጣቶችን ንቃተ ሕሊናን የሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ
ሲሆን ስልጠናውም
ቅዳሜ እና እሁድ ለግማሽ ቀ
ን ከህዳር እስከ ሰኔ መጨረሻ የሚቆይ ይሆናል
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ ትምህርቱን በቋሚነት መከታተል የምትችሉ ወጣቶች (ወንድ እና ሴት) ይህንን ቅፅ በመሙላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
🏢
ኢሙዳት(የኢትዮጵያ ሙስሊም ዳእዋና ትምህርት ማህበር)
🕹
ቶታል 3ቁጥር ማዞሪያ ወደ ብስራተ ገብርኤል በሚወስደው መንገድ ገባ ብሎ
⏰
02:30-06:00LT
ለበለጠ መረጃ
☎️
0904199399
0960281050
0963262856
ይደውሉ።
✨
ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ
።
🛑
ምዝገባ ህዳር 1 የሚጠናቀቅ ይሆናል።
🙌
ማሰራጨት አይርሱ
🙌
የመመዝገቢያ Link
👇
https://forms.gle/a2ETk8Fm3GG4MCRi6

October 27, 18:41

በቅርቡ በምዕራቡ ዓለም፣ በተለይም በአሜሪካ በሚገኙ አብያተ-ክርስቲያናትና የሃይማኖት መሪዎች ዘንድ የተከሰተ አንድ ያልተጠበቀ ሁነታ በማኅበራዊ ሚዲያና በታወቁ የመገናኛ ብዙኃን ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።
በኦሃዮ ስቴት በሚገኘው LifeWorks Church የተሰኘ ቤተ ክርስቲያን መሪና "ነቢይ" ነኝ የሚለው እስራኤል ፎርድ፣ ከአንድ በላይ ማግባት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንደሆነና በተግባርም እየኖሩበት እንደሚገኙ በይፋ ለአማኞቻቸው አስታውቀዋል።
በቪዲዮው ላይ እንደሚታየው፣ የፓስተሩ የመጀመሪያ ሚስት ሊዲያ በቤተ ክርስቲያኑ መድረክ ላይ በመቆም ማይክሮፎን በመያዝ፣ የባሏን ሁለተኛ ሚስት ሚኒስተር ሻካይላን ለምዕመናኑ በደስታና በፍቅር ታስተዋውቃለች። ሁለቱ ሚስቶች በመድረክ ላይ ተቃቅፈው ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ፣ ሁለተኛዋ ሚስት ደግሞ ይህንን የብዙ ሚስት አምልኮና ሕይወት "የእግዚአብሔር ፈቃድ" እንደሆነና ለ3 ዓመታት ያህል በዚሁ መርህ አብረው ሲኖሩ መቆየታቸውን ለአማኙ ታስረዳለች።
ይህ "ነቢይ" ነኝ ባይ ፓስተር በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹና በትምህርቱ ላይ ባሰፈረው ጽሑፍ "አንድ ሚስት ብቻ ማግባት ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ውጭ ነው" ሲል ይሞግታል።
አስተዋይ ህሊና የሚታዘበው እውነታ፦
ለዘመናት ምዕራባውያንና አብዛኞቹ የክርስትና ተሟጋቾች፣ በእስልምና አስተምህሮ ውስጥ ያለውን ከአንድ በላይ የማግባት ፈቃድ እንደ ትልቅ የአቋም ስህተትና የትችት መነሻ አድርገው ሲያቀርቡት ቆይተዋል።
ነገር ግን ታሪክና ጊዜ የራሳቸውን ፍርድ መስጠታቸው አልቀረም። ዛሬ በራሳቸው በምዕራባውያኑ ቤተ-ክርስቲያናት ውስጥ፣ የራሳቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ዋቢ በማድረግ ከአንድ በላይ ማግባት ተፈጥሮአዊ፣ ምክንያታዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑን አምነው በአደባባይ መተግበር ጀምረዋል።
እስልምና ከአንድ በላይ ማግባትን በግልጽ፣ ደንግጎ ያስቀመጠው ከ1400 ዓመታት በፊት ቢሆንም፤ ዛሬ ላይ የምዕራቡ ዓለም ቤተ-ክርስቲያን መሪዎች የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ፍላጎትና ማኅበራዊ እውነታን መካድ አቅቷቸው፣ በዘልማድ ሲቃወሙት የነበረውንና ከመጽሀፍ ቅዱስ ጋር ግን ተቃርኖ ያልነበረውን ተግባር ተቀብለው በራሳቸው መድረክ ላይ ሁለተኛ ሚስቶቻቸውን ለአማኙ እስከ ማስተዋወቅ ደርሰዋል።
https://t.me/Yahyanuhe

October 27, 18:41
Media unavailable
1
Show in Telegram

October 27, 16:19
Media unavailable
2
Show in Telegram

በቪዲዮው ላይ በካሜራ ፊት ቀርቦ እኛ ያቀረብንለትን በማስረጃ የተደገፈ ምላሽ ሲያጣጥልና ሲዘባበት ታይቷል፦ «ማነው የተጠቀሰው? ኢብኑ ሐጀር አል-አስቀላኒ? ፈትሑል ባሪ? በ15ኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ሰውዬ ተረት ተረት ለምን እንቀበላለን?» በማለት ታላቁን የእስልምና ሊቅና የምርምር ሥራቸውን ለማቃለል ሞክሯል።
ነገር ግን እውነታው ሲገለጥ አስደንጋጭ ነው! ግለሰቡ በገዛ እጁ ባሳተመው "የጽልመቱ ጥላ" በተሰኘው መጽሐፉ ገጽ 36 (ማስታወሻ 30) እና ገጽ 214 (ማስታወሻ 138) ላይ ይኸው በካሜራ ፊት ያፌዘበትን ሊቅ «አል-ሓፊዝ ኢብኑ ሐጀር፣ ፈትሑል ባሪ» እያለ በታላቅ ክብር ዋቢ አድርጎ አቅርቦታል!
ለመሆኑ አንድ ጸሐፊ ራሱ በመጽሐፉ ውስጥ ደጋግሞ የተጠቀመውን ዋነኛ ምንጭ በካሜራ ፊት እንዴት ሊረሳውና "ተረት ተረት" ብሎ ሊያንቋሽሸው ይችላል? እውነታው ከሁለት ነጥቦች ሊወጣ አይችልም፦
ወይ መጽሐፉን ራሱ አልጻፈውም፦ በውስጡ ያለውን እንኳን የማያውቅ፣ ከሌሎች ገጾች ኮፒ-ፔስት ተደርጎ የተሰጠውን ጽሑፍ በስሙ ብቻ ያተመ ሰው ነው፤
ወይም ደብል ስታንደርድ የሚጠቀም አጭበርባሪ ነው፦ ለራሱ የሐሰት ትርክትና ጥቃት ሲመቸው "አል-ሓፊዝ" እያለ የሚያከብረውን ሊቅ፣ ሙስሊሞች ስህተቱን ሲያጋልጡበትና ሲያፈርሱበት "ተረት ተረት" ብሎ የሚሸሽ ፍጹም እምነት የማይጣልበት ግለሰብ ነው!
የገዛ መጽሐፉን ገጾችና የራሱን ንግግር እንኳ ማስታረቅ የማይችል አካል፣ እንዴት ሆኖ ነው በዕውቀትና በሐቅ ላይ የተመሠረተ ሞገት አቀረብኩ ሊል የሚችለው?
ህሊና ያለው አስተዋይ አንባቢ ይፍረደው!
https://t.me/Yahyanuhe

October 27, 14:35

የእፎይ መጽሐፍ የፕሮቴስታንት ነገረ-መለኮትን በኦርቶዶክስ ስም ሲሰብክ... (ከገጽ 353 የተወሰደ) በምስሉ ላይ እንደሚታየው፣ ጸሐፊው "የጽልመቱ ጥላ" በተሰኘው መጽሐፉ ገጽ 353 ላይ እንዲህ ሲል ይጽፋል፦ “ኢየሱስ የአይሁዶች መድኃኒትና ንጉሥ ነው። ምንም እንኳ በክርስቶስ የማያምኑ አይሁዶች ቢኖሩም ኢየሱስ ግን የአይሁድ ንጉሥ እና መድኃኒት ነው” ለመሆኑ ይህ አስተምህሮ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነገረ…

October 27, 13:41

የእፎይ መጽሐፍ የፕሮቴስታንት ነገረ-መለኮትን በኦርቶዶክስ ስም ሲሰብክ... (ከገጽ 353 የተወሰደ)
በምስሉ ላይ እንደሚታየው፣ ጸሐፊው "የጽልመቱ ጥላ" በተሰኘው መጽሐፉ ገጽ 353 ላይ እንዲህ ሲል ይጽፋል፦
“ኢየሱስ የአይሁዶች መድኃኒትና ንጉሥ ነው። ምንም እንኳ በክርስቶስ የማያምኑ አይሁዶች ቢኖሩም ኢየሱስ ግን የአይሁድ ንጉሥ እና መድኃኒት ነው”
ለመሆኑ ይህ አስተምህሮ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነገረ-መለኮት ነውን?
በፍጹም አይደለም!
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትምህርት፣ ከክርስቶስ ስቅለትና ትንሣኤ በኋላ "የእግዚአብሔር ሕዝብ" ወይም "እስራኤል ዘነፍስ" የተባለችው በክርስቶስ ያመነችው ቤተ ክርስቲያን እንጂ በሥጋ የተወለዱት አይሁዶች አይደሉም። ጳውሎስ በሮሜ 9፡6-8 እና በገላትያ 3፡28-29 ላይ በግልጽ እንደሚያስተምረው፣ በክርስቶስ የማያምኑ የሥጋ አይሁዶች በሥጋ አብርሃማዊ ስለሆኑ ብቻ ልዩ የቃል ኪዳን ሕዝብ ወይም "ኢየሱስ መድኃኒታቸው የሆነላቸው" ሊባሉ አይችሉም።
ታዲያ እፎይ ይህንን የፕሮቴስታንት ትምህርት እንዴት ወደ መጽሐፉ አስገባው?
መልሱ እጅግ ቀላል ነው! ጸሐፊው የራሱ ቤተ ክርስቲያን የሆነችውን የኦርቶዶክስ ነገረ-መለኮት እንኳን በቅጡ የሚያውቅ ዕውቀት የለውም። ይልቁንም፣ መጽሐፉን ለመጻፍ የተጠቀማቸው ዋና ዋና ምንጮች የምዕራባውያን የኢቫንጀሊካል ወይንም የፕሮቴስታንት ፀረ-እስልምና ድረ-ገጾች ናቸው።
በምዕራቡ ዓለም ያሉ የፕሮቴስታንት "Christian Zionists" ወይንም ዲስፔንሴሽናሊስቶች በክርስቶስ የማያምኑ አይሁዶች አሁንም "ልዩ የአምላክ ሕዝብ ናቸው" የሚል እሳቤ አላቸው። እፎይ ደግሞ የነገረ-መለኮት ዕውቀት ስለሌለው፣ የእነዚያን የፕሮቴስታንት ጸሐፊዎች ጽሑፍ ያለ ምንም ማጣሪያ በቀጥታ ኮፒ-ፔስት በማድረግ፣ የፕሮቴስታንቱን ዶክትሪን እንደ ትክክለኛ ትምህርት አድርጎ አስቀምጦታል።
የገዛ ሃይማኖቱን ነገረ-መለኮት ከሌላ ሃይማኖት መለየት የማይችል አካል፣ እንዴት ሆኖ ነው የሌላውን ሃይማኖት (እስልምናን) ሊሞግት የሚነሳው?
ህሊና ያለው አስተዋይ አንባቢ ይፍረደው!
https://t.me/Yahyanuhe

October 27, 13:41
Media unavailable
1
Show in Telegram

October 26, 19:41

ዐይን ያወጣ ማጭበርበር በገዛ መጽሐፉ ሲጋለጥ... (ከገጽ 209 የተወሰደ)
በተያያዘው ምስል ላይ እንደምትመለከቱት፣ ጸሐፊው "የጽልመቱ ጥላ" በተሰኘው መጽሐፉ ገጽ 209 ላይ፣ ሱረቱል ፋጢርን (35:1) ሲተረጉም የፈጸመው ዐይን ያወጣ ማጭበርበር እጅግ አስገራሚና እጅ በአፍ የሚያስጭን ነው!
ግለሰቡ የመላእክትን የክንፍ ብዛት በሁለት፣ በሦስትና በአራት ብቻ እንደተገደበ ለማስመሰል እና ከሐዲስ (ሰሒሕ ሙስሊም 174b) ጋር ይጋጫል ለማለት የተጠቀመበት ተንኮል ስለማንነቱና አካሔዱ ብዙ ትምህርት ይሰጠናል። ምስሉ ላይ በግልጽ እንደሚታየው፤ ዐረብኛውን ሙሉ ለሙሉ አስቀምጦ፣ በአማርኛው ትርጉም ላይ ግን ሆን ብሎ በነጠብጣብ (...) ትርጉሙን ቆርጦ አስቀርቶታል።
ለመሆኑ ጸሐፊው በነጠብጣቡ (...) ውስጥ ሆን ብሎ የደበቀው ቃል ምንድን ነው? ከተባለ
ጸሐፊው ሆን ብሎ የደበቀውና የቆረጠው ቀጣዩ የቁርኣን ቃል «በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል» (يَزِيدُ فِي الْخَلْقِ مَا يَشَاءُ) የሚለውን ታላቅ መልእክት ነው!
ይህ አንቀጽ አላህ በመላእክት ክንፍ ላይ የፈለገውን ያህል ገደብ የለሽ ጭማሪ እንደሚያደርግ በግልጽ እያሳየ ሳለ፣ እውነታውን ሸሽጎ፣ የቁርኣኑን ሰፊ መልእክት በማጥበብ አንባቢን በሐሰት ለማደናገር መሞከሩ አሳፋሪ ነው።
ጸሐፊው ይህንን ሐቅ ሆን ብሎ በመደበቅ፣ "በግልፅ ቁርኣን ላይ ስለ መላእክት ክንፎች ሲናገር... አራት አራት እንደሆነ ነው" በማለት፣ ቁርኣን ከመላእክት ክንፍ ብዛት ጋር ተያይዞ ጅብሪል 600 ክንፍ እንዳለው ከሚናገረው ሐዲስ ጋር እንደሚጋጭ አድርጎ የፈጠራ ሞኝነቱን አቅርቧል።
አየህ እፎይ... ቃሉን ሳትቆርጥ፣ ማጭበርበርህን ትተህ ሙሉውን ዐረብኛ (በቢጫ ያቀለምኩትን) ፊደል በፊደል ብትተረጉመው ኖሮ፤ አላህ ለጅብሪል 600 ክንፍ የመስጠት ሙሉ ችሎታ ("በፍጥረቱ የሚሻውን ይጨምራልና") እንዳለው፣ በገዛ ራስህ መጽሐፍ ላይ ባሰፈርከው የቁርኣን አንቀጽ ውስጥ መልሱን ታገኘው ነበር! ግን እሱን ከጨመርክ ያመጣሀው አርጊውመንት እርባና ቢስ እንደሚሆን ስላወቅክ ቆርጠህ አስቀራሀት።
ውድ አንባቢዎች (በተለይ ክርስቲያን ወገኖቻችን)... ይህ ሰው የራሱን የጥላቻ ትርክት በቅጥፈት ለመሸጥ ሲል ምን ያህል መረጃን እያጣመመና እየቆረጠ እንደሚያደናግራችሁ ከዚህ በላይ ተግባራዊ ማሳያ የለም። እውነታው ይህ ነው! መመዘኑን ለህሊናችሁ ትተነዋል።
https://t.me/Abuyusra3