Выберите регион
и язык интерфейса
Покажем актуальные для региона
Telegram-каналы и возможности
Регион
avatar

የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

yahyanuhe
﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student |
Подписчики
21 000
24 часа
30 дней
400
Просмотры
3 383
ER
16,11%
Посты (30д)
30
Символов в посте
803
Инсайты от анализа ИИ по постам канала
Категория канала
Блог о бизнесе и экономике
Пол аудитории
Женский
Возраст аудитории
25-34
Финансовый статус аудитории
Средний
Профессии аудитории
Исследования и академия
Краткое описание
June 14, 19:06

የቁርኣን አንጸባራቂ ቃላት
​"በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡" (بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ) (ቁርኣን 1፡1)
​"ቢስሚላህ" በመጠኑ አጭር ቢመስልም፣ በውስጡ እጅግ ሰፊ ትርጉምን እና ጥልቅ የቋንቋ አወቃቀርን ያዘለ መለኮታዊ ቃል ነው። ይህችን አንቀጽ በቋንቋ፣ በታሪክ እና በተፍሲር መነጽር የተደረጉ እይታዎችን ስንመለከት አእምሮን የሚያስደምም ጥበብ እናገኛለን።
​በዓረብኛ ሰዋስው "ቢ" (بِ) የሚለው ፊደል መስተዋድድ ነው። በቋንቋው ህግ መሰረት፣ ማንኛውም መስተዋድድ ከእርሱ በፊት ወይም በኋላ የሚመጣ "አድራጊ ግስ" ያስፈልገዋል። ነገር ግን ቁርኣን "በአላህ ስም..." አለ እንጂ፣ በአላህ ስም ምን እንደምናደርግ (እበላለሁ፣ አነባለሁ፣ እጓዛለሁ) የሚለውን ግስ አልገለጸም። ይህ ለምን ሆነ?
​የተፍሲር ሊቃውንት ይህንን ሲያብራሩ፤ ግሱ ሆን ተብሎ የተደበቀው ቃሉ ለሁሉም ሁኔታዎች አገልጋይ እንዲሆን ነው ይላሉ። አንባቢው የሚያደርገውን ማንኛውንም በጎ ተግባር በዚያ ባዶ ቦታ ላይ መሙላት ይችላል። በተጨማሪም፣ ሐሳቡን ቀጥታ በ"አላህ ስም" በማስጀመር ሌላ ማንኛውም ነገር ከእርሱ ስም እንዳይቀድም እና በረካው ሙሉ እንዲሆን የተደረገበት እጅግ ውብ የቋንቋ ስልት ነው።
​በአንቀጹ ውስጥ ሶስት ታላላቅ የአላህ ስሞች በተከታታይ መጥተዋል፦ አላህ፣ በመቀጠል አር-ረሕማን፣ ከዚያም አር-ረሒም። ይህ ቅደም ተከተል ድንገተኛ አይደለም።
• ​መጀመሪያ "አላህ" (اللَّه) የሚለው የባህሪያቱ ሁሉ ሰብሳቢ የሆነው እና የፈጣሪነት ምንነቱ ተገለጸ።
• ​ቀጥሎ "አር-ረሕማን" (الرَّحْمَٰن) የሚለው፣ አላህ ለፍጡራኑ ሁሉ ያካተተውን እጅግ ሰፊ እና አጠቃላይ የሆነውን እዝነቱን የሚያሳየው ስም መጣ።
• ​በመጨረሻም "አር-ረሒም" (الرَّحِيم) የሚለው፣ አላህ በተለየ ሁኔታ ዘላቂ፣ ቀጣይነት ያለው እና ለምእመናን የሚያደርገውን ልዩ እዝነት የሚያሳየው ስም ተከተለ። ይህ ከጠቅላላው ወደ ዝርዝሩ፣ ከሰፊው ወደ ቋሚው የሚሄድ ማራኪ የቋንቋ አገላለጽን ይፈጥራል።
​ቁርኣን "ቢስሚላህ"ን ሲገልጽ አዲስ ቃል ተፈጥሮ ሳይሆን፣ ከእርሱ በፊት በነበሩት ነቢያት ሲወርድ የነበረውን መለኮታዊ እውነት ማረጋገጡን እናያለን።
• ​ነቢዩ ኑህ (ዐ.ሰ) መርከቢቱን ሲያሽከረክሩ፦ "መሄዷም መቆሟም በአላህ ስም ነው..." (بِسْمِ اللَّهِ مَجْرَاهَا) (ቁርኣን 11፡41) በማለት ተጠቅመውታል።
• ​ነቢዩ ሱለይማንም ለንግስት ቢልቂስ በላኩት ደብዳቤ ላይ፦ "እርሱም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡... (بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ)" (ቁርኣን 27፡30) በማለት ጀምረዋል።
​ከዚህም ባሻገር፣ ዕብራይስጥ፣ አራማይክ እና ዓረብኛ ሁሉም የሴማዊ ቋንቋ ቤተሰቦች ናቸው። ‹ር-ሕ-ም› (ر ح م) የሚለው የስርወ-ቃል በነዚህ ሁሉ ቋንቋዎች ውስጥ ለፈጣሪ እዝነት መግለጫነት ያገለግላል። ይህም ይህ ቃል በነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) እና በሌሎችም ነቢያት በኩል ሲወራረስ የመጣ ጥንታዊ እና መለኮታዊ ሀረግ መሆኑን በታሪክ ያረጋግጥልናል።
ቢስሚላህ በሐዲስ
​የቢስሚላህን ታላቅነት በተመለከተ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በተለያዩ ሐዲሶቻቸው አስተምረውናል። ከነዚህም ውስጥ የሰው ልጅ ይህንን ቃል ሲጠቀም የሚኖረውን መለኮታዊ ጥበቃ በተመለከተ ጃቢር ኢብኑ አብዲላህ (ረ.ዐ) ባስተላለፉት ሶሒሕ ሐዲስ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦
​"አንድ ሰው ወደ ቤቱ ሲገባ እና ምግቡን ሲበላ የአላህን ስም (ቢስሚላህ) ካወሳ፤ ሸይጧን (ለተከታዮቹ)፡- ‹ለእናንተ እዚህ ቤት ማደሪያም ሆነ እራት የላችሁም› ይላቸዋል።" (ሶሒሕ ሙስሊም፥ 2018)
​ይህ የሚያሳየን "ቢስሚላህ" ሸይጧንን ጭምር የሚያግድ ትልቅ ጋሻ መሆኑን ነው!
⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
https://t.me/Yahyanuhe

June 14, 19:06
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

June 14, 18:30
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

ከቴሌግራምና ከፌስቡክ በተሻለ ዋትስአፕ ላይ መልዕክት መከታተል ለሚቀላችሁ ይህ አማራጭ ለእናንተ ነው። በብዛት በቴሌግራም የሚለቀቁ ኢስላማዊና ንጽጽራዊ የጹሁፍ ትምህርቶችን ለማሰራጨት በማሰብ የዋትስአፕ ቻናል ተከፍቷል። በአላህ ፍቃድ ከዛሬ ጀምሮ ትምህርቶች ይለቀቁበታል።
https://whatsapp.com/channel/0029Vb8AsW52UPB7oGE0mw1d

June 12, 13:06

የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
pinned a photo

June 12, 13:06
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

የድርጅትዎን ገጽታ በዲዳት ያድምቁ!

​ጥራት ያለው የህትመት እና የማስታወቂያ ስራ ፈልገዋል? ዲዳት ህትመትና ማስታወቂያ የደንበኞቹን አደራ (አማና) በታማኝነት በመጠበቅ ፈጣንና ፕሮፌሽናል አገልግሎት ይሰጣል! ጊዜዎንና ገንዘብዎን በአስተማማኝ ቦታ ላይ በማዋል የንግድዎን ስኬት ያፋጥኑ።
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች፦
• ​ባነር
• ስቲከር
• ላይት ቦክስ
• የቲሸርት ህትመት
• ​የደረሰኝ እና የማስታወሻ ደብተር ህትመት
• ማግ (ኩባያ) ህትመት
• ​የቢዝነስ፣ የመታወቂያ እና የጥሪ ካርዶች ህትመት
​ጥራትን ከታማኝነት ጋር አዋህደን እንጠብቅዎታለን!

📍
አድራሻችን፦
ቤቴል፣ አዲሱ ህንፃ፣ 3ኛ ፎቅ

📞
ስልክ፦ 0946-4599-45
📱
@Dedatprinting1

June 05, 08:35
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

በአክሱም "ጳጳሳት" ሳይቀሩ በውሳኔ ሰጪነት ለተሳተፉበት ግፍና ለፈሰሰው ደም፣ አንድም ሙስሊም ክርስቲያኑን ወገኑን በጅምላ ሲወቅስ አላየንም። በጎንደር ያ ሁሉ ሙስሊም ሲገደልና መስጊዶች ሲወድሙ፣ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሳይቀር ከማውገዝ ይልቅ የተግባሩ ደጋፊ ሆነው እያየን እንኳን፤ መጽሐፍ ቅዱስን እያጣቀስን "እንስሳትን ሳይቀር ግደሉ የሚል መጽሐፍ ነው ያላችሁ፤ ስለዚህ ሁላችሁም ተጠያቂ ናችሁ" ብለን የጅምላ ፍርድ አልሰጠንም።
​የአርሲውን አሳዛኝ ክስተት በተመለከተ ግን፣ ገዳዮቹን ከሟቾች መገደል በፊት ቀድመው ያወቋቸው በሚመስሉ አካላት፣ በሙስሊሙ ላይ የተቀነባበረ ዘመቻ ሲከፈት እያየን ነው። ሙስሊሙ ድርጊቱን በጽኑ እያወገዘና አምርሮ እየተጸየፈው እንኳን፣ አጥቂዎቹ ከመጀመሪያው ከተነሱበት የተዘጋጀ ዓላማ ላለመራቅ በሚመስል መልኩ ዘመቻቸውን ይበልጥ አጧጡፈውታል። ይህንን ሒደት በውል ለታዘበ ሰው፣ በእነዚህ ንጹሐን ዜጎች ደም ለመነገድ ያሰፈሰፈ የተደራጀ አካል ከጀርባ እንዳለ በቀላሉ ማስተዋል ይችላል።
​ጭራሽ አሁንማ ክስተቱን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም፣ ቁርኣንን ከዐውዱ ውጭ እያጣቀሱ እስልምናን በይፋ ወደ መስደብ ተገብቷል። እንዲህ ዓይነቱን የትርክት ብልጣብልጥነት ለመተግበር አሁን ዘመኑ እንዳልሆነ ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል። ይህንን የጥላቻ ስም ማጥፋት ለማካሄድ ቀድማችሁ ተዘጋጅታችሁ ስትጠብቁ እንደነበር በሚያሳብቅ መልኩ፣ እባካችሁ ራሳችሁን አታጋልጡ።
​ቢያንስ ይህንን ሴራ መረዳትና ማስተዋል የሚያቅተን ቂሎች አይደለንም!
⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
https://t.me/Yahyanuhe

June 03, 18:05
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

በአርሲ የተፈጸመውን አሰቃቂ የንጹሐን ግድያ ሁሉም ወገን በጋራ እያወገዘው ይገኛል። በእርግጥም የንጹሐን ዜጎች ግድያ እጅግ አሳዛኝና አስነዋሪ ድርጊት ነው። ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ መሞትን ክፉኛ ተላምደነው፣ የንጹሐን ሞት ከተራ የዜና ማሟያነት ማለፍ ያቃተበት አሳዛኝ ዘመን ላይ ደርሰናል።
​በዚህ መሃል፣ ያለምንም የዘርና የእምነት ልዩነት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ግድያውን እያወገዘ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ የአንዳንዶች አካሄድ ግን እጅግ እንግዳና አስገራሚ ሆኖ እናገኘዋለን። "ለምን አላወገዛችሁም?" ብለው ሲወርፉ የነበሩ ሰዎች፣ ተገቢውን ውግዘት ሲሰሙ ደግሞ መልሰው "እናንተ ራሳችሁ ናችሁ ገዳዮቹ!" በማለት፣ ማኅበራዊ ሚዲያውን በንጹሐን ደም በሚነግድ ጸያፍ የፖለቲካ ትርክት ሊሞሉት ይሞክራሉ። በእርግጥ የእነዚህ ሰዎች ዋና ዓላማና ፍላጎት ምንድን ነው?
​በእነዚህ ንጹሐን ዜጎች ደም እና መከራ የፌስቡክ ላይክ እና ሼር ለመሰብሰብ ስትሽቀዳደሙ ጥቂት እንኳ አታፍሩም? አንድ ሰው ለወገኑ ያለውን ልባዊ ሐዘኔታ ለመግለጽ የእናንተን ፈቃድና ይሁንታ የሚጠብቅ የሚመስላችሁ፣ ራሳችሁን በምን ዓይነት የሥነ-ልቦና ልዕልና ውስጥ አስቀምጣችሁት ነው? እውነታው ሲፈተሽ፣ ስለሟቾች ጉዳይ "በእምነት ይመስሉናል" ከማለት ባለፈ፣ መሞታቸው ትዝ የሚላችሁ ፌስቡክ ላይ ስትገቡ ብቻ መሆኑን ሕሊናችሁ ጠንቅቆ ያውቀዋል።
​እባካችሁ በንጹሐን ደም መነገድ ነውር ነውና ከዚህ እኩይ ምግባራችሁ ታቀቡ! በዚህ የሐዘን ወቅት ሆን ብለው በንጹሐን ሞት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘትና መከፋፈልን ለመፍጠር የሚጥሩ አካላትን "ተው!" ማለትና ማውገዝ፣ ከጤናማና ሰላም ወዳድ ዜጎች ሁሉ የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው።
⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻
https://t.me/Yahyanuhe

June 02, 18:35
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram

በዚህ ፈታኝ ወቅት ለዳዕዋ ሥራችን የቴክኒክ ባለሙያዎች እገዛ እንሻለን!
​በቅርቡ ሁላችንም እንደምንታዘበው፣ በክርስቲያን ወገኖቻችን በኩል እስልምናን በተመለከተ የሚነሳው ውዝግብ፣ ትችትና ያልተገባ ንግግር ከምንጊዜውም በላይ ጨምሯል። በዚህ ወሳኝ ሰዓት እምነታችንን በዕውቀት መከላከልና ለሚነሱት ማደናገሪያዎች ትክክለኛውን መረጃ ምላሽ ማድረስ እጅግ አስፈላጊ ነው።
​ይህን ታላቅ የዳዕዋ ሥራ በሰፊው ለማድረስ ደግሞ፣ ከፍተኛ ተደራሽነት ያለው መድረክ የግድ ይለናል። እንደምታውቁት ከ100 ሺህ በላይ Followers የነበሩትና፣ በሶስት ወራት ውስጥ ብቻ ከ20 ሚሊዮን በላይ ተደራሽነት ወይንም Reach የነበረው ዋነኛው የፌስቡክ ገጼ ከተዘጋ አሁን ከ3 እስከ 4 ወራት አልፈውታል። ይህ ገጽ በነበረን የዳዕዋ እና የንጽጽር ሥራ ላይ ትልቅ ምሽግ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን በተለይ በዚህ ጫና በበዛበት ወቅት መዘጋቱ የራሱን ክፍተት ፈጥሯል።
​ስለዚህ፣ ይህንን ገጽ በማስመለስ በኩል ሊያግዘኝ የሚችል የቴክኒክ ባለሙያ እፈልጋለሁ። በተለይም የፌስቡክ 'ብሉ ባጅ' (Meta Verification) ያለው እና ከፌስቡክ ኮንታክት ሴንተር ጋር በቀጥታ በመነጋገር ገጹን ማስከፈት የሚችል አቅም ያለው ወንድም ወይም እህት ካለ፣ እባካችሁ አግዙኝ። ይህን በማድረግዎ በግልዎ ለዚህ የዳዕዋ መስመር ትልቅ አሻራዎን እያኖሩ ነው።
​ይህንን ማድረግ የምትችሉ ባለሙያዎች፣ እባካችሁ በውስጥ መስመር ወይም በዚህ የቴሌግራም አድራሻ አናግሩኝ፦
@Yahyanuhe1
​አላህ ለዲኑ የምንለፋበትን አቅም ይስጠን። ሼር በማድረግ ትክክለኛው ሰው ዘንድ እንዲደርስ ተባበሩኝ!

June 02, 10:09

እስልምናን ለተቀበሉ ሙስሊም ወንድምና እህቶች የተዘጋጀ መሠረታዊ ዲን ሥልጠና!
​ወደ ውቡ የኢስላም ጎዳና በቅርቡ ለተቀላቀሉ (ለሰለሙ) ወንድሞች እና እህቶች በሙሉ፤ እነሆ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ፣ ብቁ በሆኑ አሰልጣኞች የሚሰጥ ልዩ እና ነፃ የሁለት ወራት የአካል ሥልጠና ተዘጋጅቷል።
ቦታ፡ አዲስ አበባ፣ ጦር ኃይሎች አካባቢ
የሥልጠና ጊዜ፡ ለሁለት ወራት (በአካል የሚሰጥ)
​በዚህ ሥልጠና የሚዳሰሱ ዋና ዋና የትምህርት ዘርፎች፦
• ​ የቁርኣን ትምህርት፦ መሠረታዊ የቁርኣን አቀራር እና ትርጉም
• ​ ፊቅህ፦ የዕለት ተዕለት ኢስላማዊ ሕግጋት እና አፈጻጸም
• ​ ዐቂዳ፦ መሠረታዊ የሃይማኖቱ እምነት እና ምሰሶዎች
• ​ ሲራ፦ የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አርአያነት ያለው የሕይወት ታሪክ
• ​ሹቡሃት፦ በእስልምና ዙሪያ ለሚነሱ ብዥታዎችና ጥያቄዎች የሚሰጡ ምላሾች
• ​ሕይወትን በእስልምና፦ እምነትን በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ መተግበር (ከቅርብ ክትትልና ሥነ-ልቦናዊ ድጋፍ ጋር የተዋሃደ)
​ሥልጠናው ሙሉ በሙሉ ነፃ ሲሆን፣ ቦታው ሳይሞላ ፈጥነው ይመዝገቡ። ይህንን መልእክት ለሌሎች በማካፈልና ሼር በማድረግ አዳዲስ ሙስሊም ወንድምና እህቶቻችን መረጃው እንዲደርሳቸው የበኩልዎን አስተዋጽኦ ያድርጉ!

🔗
ለመመዝገብ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ፦
https://forms.gle/ugsXL6MM2QR1T1k99

June 02, 10:08
Файлы недоступны
1
Открыть в Telegram