
Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ
ቱርክ የፕሬዝደንት ኢርዶጋንን ዋና ተቀናቃኝ አሰረች
የኢስታንቡል ገዥ ቢሮ እስሩን ተከትሎ በከተማዋ ሁሉም ስብሰባዎች እና ተቃውሞዎች እንዳይካሄዱ ለአራት ቀናት የሚቆይ እግድ አስተላልፏል።
https://bit.ly/3FF7NRt
ለ22 ዓመት ሴት መስሎ በሴቶች ገዳም ውስጥ የኖረው ሰው
የሚረዳው አጥቶ ወደ ገዳም የገባው ሰው በመጨረሻም ጾታው ሲታወቅበት ከገዳም መውጣቱ ተገልጿል
በገዳሙ ውስጥ ከሴቶች ጋር በሚኖርበት ወቅት ወንድነቱ እንዳይታወቅበት ከባድ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል
ተጨማሪ ያንብቡ
https://bit.ly/3E1XW7D
ኤርትራ በትግራይ ክልልም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ እንደማትገባ ገለጸች
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያን የወደብ ጥያቄ “ጊዜ ያለፈበት” ሲሉ ተችትዋል። አዲስ አበባ አስመራን ለውስጥ ችግሮቿ ተጠያቂ ከማድረግ እንድትቆጠብም አሳስበዋል።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ-
https://bit.ly/4iCgfit
⭕️
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሼክ ታህኖን ቢን ዛይድን በዋይት ኃውስ ተቀብለው አነጋገሩ
📌
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙትን የአረብ ኢምሬትስ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪና የአቡዳቢ ምክትል አስተዳዳሪ ሼክ ታህኖን ቢን ዛይድ አል ናህያንን በዋይት ኃውስ ተቀብለው አነጋግረዋል።
📌
በዋይት ኃውስ በነበራቸው ቆይታም በሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂካዊ አጋርነት፣ በፀጥታ፣ኢኮኖሚያዊ እና ቴክኖሎጂያዊ ትብብርን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ውይይት አድርገዋል።
📌
ፕሬዝዳንት ትራምፕ "የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ እና በአለም ላይ ሰላም እና ደህንነትን ለማስፈን በጋራ የሚሰሩ የሁልጊዜ አጋር ናቸው" ሲሉም ገልጸዋል።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ-
https://bit.ly/42dav9o
“ከአረብ ኢምሬትስ ጋር ያለን ግንኙነት በታሪክ ጠንካራ ነው”- ትራምፕ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሼክ ታህኖን ቢን ዛይድን በዋይት ኃውስ ተቀብለው አነጋረዋል። የአረብ ኢምሬትስ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪና የአቡዳቢ ም/አስተዳዳሪ ሼክ ታህኖን ቢን ዛይድ በአሜሪካ ጉብኝ እያደረጉ ነው።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ-
https://bit.ly/42dav9o
ፑቲን እና ትራምፕ በተጠባቂው የስልክ ውይይታቸው በምን ጉዳዮች ላይ ተነጋገሩ?
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚ ፑቲን በስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ተነግሯል።
ሁለቱ መሪዎች 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በፈጀ የስልክ ውይይታቸው የዩክሬን ጦርትና የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማደስ የውይይታቸው አካል ነበር።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤
https://bit.ly/4kYMY3n
አቃቢ ህግ በእነ ዮሀንስ ቧያለው መዝገብ ስር በተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ላይ ምስክሮችን ማሰማት ጀመረ
የፍትህ ሚኒስቴር በእነ ዮሀንስ ቧያለው መዝገብ ባሉ 52 ተጠርጣሪዎች ላይ የፖለቲካ ርዕዮትን በሀይል ለማስፈጸም ተንቀሳቅሰዋል፣ በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀል ህግ እንዲሁም የሽብር ወንጀሎችን ለመከላከል የወጣውን ህግ ጥሰዋል በሚል ከአንድ ዓመት በፊት ክስ መመስረቱ ይታወሳል።
ከ52ቱ ተከሳሾች መካከል 16ቱ ተከሳሾች አዲስ አበባ ልደታ በሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህገ መንግስት እና ሽብር ወንጀሎች ችሎት የቀረቡ ሲሆን የአቃቢ ህግ ምስክሮች በተከሳሾች ላይ የምስክርነት ቃላቸውን እንደሰጡ የተከሳሾች ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለአል ዐይን ተናግረዋል።
አቃቢ ህግ ተከሳሾቹ ባስተላለፉት ትዕዛዝ ምክንያት የደረሱ ጉዳቶችን ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮች አቅርቧል።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤
https://bit.ly/4iemZmZ
ኢራን የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ማባረሯን አስታወቀች
የአሜሪካ ጦር ንብረት ነው የተባለው ሰው አልባ አውሮፕላን በቴህራን አቅራቢያ ቅኝት በማድረግ ላይ ነበር ተብሏል።
የኢራኑ ኤፍ-14 የተሰኘው የውጊያ አውሮፕላን የአሜሪካ ሰው አልባ የስለላ አውሮፕላንን እንዳባረረ ተገልጿል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት ጽሁፍ " በየመን ያለው ሁቲ ቡድን ለሚያደርገው እያንዳንዱ ጥቃት ሀላፊነቱን የምትወስደው ኢራን ናት" ብለዋል።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤
https://bit.ly/4kxRVQG
አረብ ኢምሬትስ እስራኤል በጋዝ የፈጸመችውን የአየር ድብደባ በጽኑ አወገዘች
የአረብ ኤሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ ባለፈው ጥር ወር የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ ተጨማሪ ንጹሐን ጉዳትን በማስከተል በጋዛ ሰርጥ የሚታየውን ሰብዓዊ አደጋ የሚያባብስ ነው በማለት ማስጠንቀቁን የኤሚሬትስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሁኔታውን ለማርገብ አስቸኳይ እርምጃዎችን እንዲወስድ እና አፋጣኝ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ እና ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ ሁሉንም ጥረቶችን እንዲያደርጉ ጠይቋል።
ከአረብ ኢምሬትስ በተጨማሪም ግብጽ፣ ቱርክ፣ ቻይና እና ሩሲያ ጨምሮ በርካታ ሀገራት በጋዛ የተፈጸመውን ጥቃት አውግዘዋል።
ጥቃቱን እነማን አወገዙ? በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤
https://bit.ly/3XXqN3K
ሼክ ታህኖን ቢን ዛይድ ከአሜሪካ የግምጃ ቤት ኃላፊ ጋር ተወያዩ
ስለ ቀጣይ ጊዜ ኢንቨስምት፣ ቴክኖሎጂ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በኢነርጂና በንግድ አጋርነት ላይ መክረዋል። የአረብ ኢምሬትስ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪና የአቡዳቢ ም/አስተዳዳሪ ሼክ ታህኖን ቢን ዛይድ በአሜሪካ ጉብኝ እያደረጉ ነው።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤
https://bit.ly/4iclcin